Site icon ETHIO12.COM

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህገ መንግስት እንደሚሻሻል ፍንጭ ሰጡ፤ መንግስት የማጥራት እርምጃውን እንደሚያጠናክር ገለጸ

አወዛጋቢው የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ሊሻሻል እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ፍንጭ ሰጡ። ጠቅላይ ሚኒስትር አህመድ ለሁለተኛ ጊዜ ለመልካም አስተዳደር ችግር መፈጠር መንስኤ የሚሆኑ አካላትን የማጥራት ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቁ።

የአማራ ክልል መሰረታዊ ጥያቄዎች ሶስት መሆናቸውን ያወሱት አብይ አሕመድ ህገ መንግስቱ እንደሚሻሻ ፍንጭ የሰጡት በማብራሪያ አስደግፈው ነው።

የአማራ ክልል ህዝብ ጥያቄዎች ሲጠቃለሉ ሶስት መሆናቸውን ያመልከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነሱም የህገመንግስት፣ የልማትና የወሰን ጥያቄዎች እንደሆኑ አመልክተዋል።

ስለህገ መንግስት አንስተው የአማራ ህዝብ የሚያነሳው ጥያቄ ምላሽ እንደሚያገኝ፣ የአገራዊ እርቅ ኮሚቴው እየሰራበት እንደሆነ አመልከተዋል። ከቀን በፊት የገንዘብ ሚኒስትሩን አቶ አሕመድ ሺዴን የጠቀሰው የማራ ክልል ሚዲያ በህዝብ ውሳኔ ሊቀየር እንደሚችል፣ በዚህም ላይ እየተሰራ መሆኑንን ጠቁሞ ነበር።

የትኛው ክፍል እንደሚቀየር ይፋ ያላደረጉት አብይ አህመድ የወሰንና የባለቤትነት ችግር ባለባቸው የአማራና የትግራይ ክልል ዘላቂ ሰላም የሚያወርድ የህዝብን ወሳኝነት የሚያረጋግጥ ዴሞክራሲያዊ መፍትሄ እንደሚሰጥ ደግመው ገልጸዋል። የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ወልቃይት ጠገዴና ራያ ሙሉ በሙሉ ካልተመለሱ በአገሪቱም ሆነ በትግራይ ሰላምማስፈን ስራ ተባባሪ እንደማይሆን ጠቅሶ መግለጫ ባወጣ ማግስት ነው ይህን ያሉት።

በሌላ ዜና በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ሆነው ለመልካም አስተዳደር ችግር መፈጠር መንስኤ የሚሆኑ አካላትን የማጥራት ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልየተገለጸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባውን ሲያኬሂድ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሲሰጡ ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል አንዱ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ሆነው የመልካም አስተዳደር ችግር የሚፈጥሩ አካላት ጉዳይ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉ አገልጋዮች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ግንዛቤ የመፍጠርና አቅም የመገንባት ሥራዎች ላይ ትኩረት ተደርጓል ብለዋል። አስተሳሰብ መቀየር ቅድሚያ እንደሚሰጠው ጠቁመዋል። እንዲያም ሆኖ ከሕግ ውጭ የሚንቀሳቀሱ ሕገ-ወጦች መኖራቸውን አስታውሰው ይሄንን የማጥራት ጉዳይ እንደሚቀጥል አስረግጠው ተናግረዋል።

ለአብነትም በ2016 ዓ.ም ባለፉት ስድስት ወራት በየደረጃው ካሉ አመራሮች ውስጥ 8 በመቶ ያህሉ ላይ እርምጃዎች መወሰዱን ገልጸዋል።

በዚህም ከ4 በመቶ በላይ አመራር ከሥራ እንዲሰናበቱ የተደረገ ሲሆን ከ4 በመቶ በላይ ደግሞ ከደረጃ ዝቅ እንዲሉ መደረጉን ነው የተናገሩት።

Exit mobile version