Site icon ETHIO12.COM

“ አንገት ቆረጣ ” የ – ሰለጠነው የ- እርስ በርስ መበላላት!

ሃኪሙ የተረኛ ስም ጠራ፤ አስናቀ “ አቤት” ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳ፡፡ ሃኪሙ አስናቀን በምልክት “ የት አለ” ሲል ጠየቀው፡፡ አስናቀ መዘናጋቱን አስታወቆ የተጠየቀውን ሊያመጣ ላፍታ ወደ ውጭ ተመለሰ፡፡ ከሃኪሙ ቢሮ ወጣ !

ብዙ የተቆረጡ አንገቶች ኮሪደሩ መግቢያ ላይ ተደርድረዋል፡፡ አንገቶቹ በላስቲክ ተደርገው ተቋጥረዋል፡፡ እያንዳንዱ ቁራጭ ጭንቅላት ባለቤት አለው፡፡ ባለቤቱ ብቻ ነው ቁራጭ አንገቱን የሚያውቀው፡፡ ብዙ የተቆረጠ ጭንቅላት፡፡ አስናቀ እሱ ያመጣውን ጭንቅላት ቁራጭ ዘነጋው፡፡መለየት አልቻለም።

ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ አስናቀ ዛሬ በሕይወት የለም፡፡ አስናቀ እጅግ ቆጆ የቀይዳማ፣ ተሞላቆ ያደገ፣ ለቤቱ አንድ ወንድ፣ ሁሉም የቤተሰቡ አባላት አይን አይኑንን የሚያዩት፣ በኮሚክነቱ ፈቃድ የተጠው ልጅ፤ ምን ያደርጋል በልጅነቱ “ነበር” ሆነ፡፡ አስናቀ ሳያድግ ራሱን ጠላ ቤት ቀርቅሮ እንደ ቦለተ አተላ በላው።

ያበደው አስናቀን በደንብ ስለሚያውቀው እንባውን አቀረረ፡፡ አባት፣ እናት፣እህት … ታወሱት። አስኔ መኖር እየቻለ አምቡላ እንደ አገዳ ቀስ ብሎ ቦርቡሮ ወሰደው፡፡ አስኔ የምሰየምበት ብቅል የምታምር ክብ ፊቱን አወየባት። እሱ ብቅል ዛሬ ድረስ ስለመኖሩ ያበደው መረጃ የለውም። ቤተሰብ የማይመርጥ ብቅልና ጌሾ!!

እንደምን ከረማቹህ፡፡ ሰሞኑንን ዛሬ ወሬው ሁሉ ስለ ተቆረጠ አንገት ነው፡፡ ድሮ በሃላሉ ዘመን “ታጋይ ለአጋሩ ሲል ቀድሞ ተሰዋ፤ ታጋይ ለትግሉ ሲል ዋጋ ከፈለ” የሚለው ትርክት “ ሲያልቅ ታጋይ የባልደረባ ታጋይን አንገቱን ቆረጦ ፈረጠጠ” ወደሚለው ተቀየረ፡፡ ድሮ ታጋይ … ያበደው ወደሁዋላ አሰበ። ያን ክፉ ዘመን ጎተተው። ድንገት ብድግ አለና አጓራ።

ግማሽ ምዕተ ዓመት፣ ግማሽ ዘመን፣ የአንድ ሰው ዘመን፣ ሃምሳ ዓመት፣ ሰው ተወልዶ፣ ከብዶ በሚድርበትና የልጅ ለጅ በሚያይበት ዘመን… ስትጋደሉ ትኖራላቹህ? እናንተ የስልሳዎቹ ጉዶች፣ እናንተ በ “አቸነፈና አሸነፈ” ውስጥ “ ቸ”ና “ ሸ” ን መርጣችሁ የምትቧቀሱ። የምትጋደሉ… ያበደው ጮኸ ውጡ፣ ጥፉ፣ እልም በሉ፤

ደሞ እንደ ትልቅ ገድል “ ያ – ትውልድ” ይሉናል። “ያ ትውልድ” ብለው ድንጋይ ከምረው ያመልካሉ። ለዛ ትውልድ ማፈሪያ ታሪክ ህንጻ ገንብተው ሃፍረታቸውን ይሰብካሉ። ለመጪው ትውልድ ክፋታቸው ሊግቱበት!! “ ለመሆኑ የቱ ነው ያ ትውልድ? ” ያበደ ጮኸ… የነጭ ሽብር ወይፈን ደራሲዎች፣ የቀይ ሽብር ጋጋኖዎች፣ አርፎ የኖረን ሕዝብ የብሄር ፖለቲካ ግተው ዛሬ ድረስ አጽማቸው የሚያጫርስ ትውልድ?Related stories   የስምንተኛው ጉዞ አድዋ የሽኝት መርኃግብር እየተካሄደ ነው።Powered by Inline Related Posts

ደሞ እንደ ትልቅ ገድል “ ያ – ትውልድ” ይሉናል። “ያ ትውልድ” ብለው ድንጋይ ከምረው ያመልካሉ። ለዛ ትውልድ ማፈሪያ ታሪክ ህንጻ ገንብተው ሃፍረታቸውን ይሰብካሉ። ለመጪው ትውልድ ክፋታቸው ሊግቱበት!! “ ለመሆኑ የቱ ነው ያ ትውልድ? ” ያበደ ጮኸ… የነጭ ሽብር ወይፈን ደራሲዎች፣ የቀይ ሽብር ጋጋኖዎች፣ አርፎ የኖረን ሕዝብ የብሄር ፖለቲካ ግተው ዛሬ ድረስ አጽማቸው የሚያጫርስ ትውልድ? ” እኮ የቱ ትውልድ?” ያበደው ደግሞ ጮኸ ኢህአፓ? መኢሶ? ሰደድ? ኢጭሃት? ህወሃት፣ ሻእቢያ፣ እኮ እነማ? ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ሸኔ፣ ቶርቤ፣ አይ ኤፍ ኤል ኦ፣ ኢድዩ፣ … “ የለምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም ” ብሎ ጀምሮ የስልሳ ሚኒስትሮች ደም ሳይነጋ የጠጣው ወታደራዊ ጁንታ? ያበደው እየተንቆራጠጠ ጠየቀ? መልስ የለም? መልሱ የሃዘን ጎርፍ፣ ተስፋቸውን የተነጠቁ እናቶች ብቻ!! ሃዘን የበላው ጣራና ግድግዳ!! ይቀጥላል… ክፉ ከፉ ደራሲዎች ግርግም ውስጥም ከግርግምም ውጭ አሉ። የጥላቻ ስብከት ላይ የተሰለፉ ክሱዎች አሉ። አክትቪስት በሚል ማዕረግ ከጀራ የሚያሰራጩ አሉ። ያበደው ዞረበት … ድግሱ ሰውየው እንዳሉት ተቋማዊ ነው… ከዛም በላይ ነው … “ተነዳላቸው ” የበደው ተቆናደፈ !!

ያበደው ድንገት ቦሰና ያለችው ትዝ አለው። ቦሰና “ መግደል ውለታ ሆኖ ሃውልት ያስተክላል፤ ያሸልማል፤ ወይ እብደት… የስይፍዬ እናት ቀና ብለው ቢያዩት” ብላዋለች። ጎረቤቶቿ እለቅሶ ላይ ያወሩትን ቀድታ አሰምታለች።

ስማ ጆሮ ያለህ፣ አንገት ያለህ ዞረህ እይ፤ አይናማ ተመልከት፣ ጭንቅላት ያላህ አስብ …. ተራረዱ፣ ተሞሻለቁ፣ ብለህ አትገልፍጥ፡፡ ያገርህ ፖለቲካ መተራረድ እንጂ ሌላ አያውቅም!! መጫረስ እንጂ መነጋገር አያውቅም። የአገርህ ፖለቲካ ነዳጁ ደም ብቻ ነው። “ ገና ብዙ ብዙ… ብዙ ይቀራናል … እግር ተራመድ” አለች የጊዮን ልጅ!! አዎ በድም ውስጥ መርመጥመጥ…Related stories   ጭካኔ ኩያሳ ሲሰራና ጥላቻ አናት ላይ ሲቀነዝር …Powered by Inline Related Posts

አስናቀ ከሃኪሙ ቢሮ ወጣ ያለው የተቆረጠ አንገት ሊያመጣ ነበር፡፡ ብዙ አንገቶች ተደርድረዋል፡፡ አስናቀ የሱን ቁራጭ አንገት መለየት አልቻለም፡፡ ያበደው የዛሬ መረጃ ባይኖረውም አስናቀን ውሻ በነከሰው ጊዜ፣ ውሻው ባለቤት ከሌለው አስገድሎ አንገቱን ባማስቆረጥ ፓስተር መሄድ ግድ ነው፡፡

አስናቀን የነከሰው ጅላጅል ውሻ የሰፈሩ ጸሐይ ሟቂዎች ተከፍሏቸው አንቀው ገደሉትና አንገቱን ቆርጠው ለአስናቀ አስረከቡት፡፡ አስኔ አንገቱን ይዞ ፓስተር ሄደ፡፡ ፓስተር ሄዶ እንደሱ አንገት ቆርጠው ከመጡ ሰዎች ተርታ እሱን የነከሰውን ውሻ አንገት ኮለኮለ፡፡ አስናቀ ላስቲኩ ላይ ምልክት አላደረገም ነበርና መለየት አቃተው፡፡ ሲቆይ ሃኪሙ ከቢሮው ወጣ ብሎ መቆየቱን ነገረው፡፡

አስኔ መለየት እንዳቃተው ገለጸ፡፡ አስከትሎም “ዶክቶር እንደ በግ ቀንድ የለው፣ ላት የለው በምን ልለየው” አለና ሳቅ ፈጠረ። የተሳቀው ግን ራሱ ላይ ነበር።

የዘመኑ አንገት ቆረጣ ማንነት ለመደበቅ ነው አሉ። ቦሰና ዜናውን ስትሰማ “ አፈር በበላሁት” ስትል አነባች። ድርጊቱ ያማል? ድርጊቱ ይቀፋል። ድርጊቱ ይሰብራል። እነማን አንገታቸው ተበጥሶ… ቦሰና አልጨረሰችውም አንዘረዘራት።

ያበደው ከበደው። የሚለውን አጣ። ዘገነነው። ዛሬ አቃተው። የሰይፍዬ እናት ዓየቶች ብዙ ናቸው። ዓለም ሲሰለጥን አዲስ ነገር ሲሰራ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ አገዳደል ጭካኔውን እያበዛ ነው። ሰውን በቁም መተርተር፣ ማረድ፣ አርዶ አንገቱን ሜዳ ላይ ወርውሮ ማሽካካት… ለፖለቲካ ማቀጣጠያ ሲባል የምስኪን ቤት አቃጥሎ፣ ነዋሪዎችን ጭፍጭፎ ቪዲዮ ማስቀረጽ… “ እኔም ገዳይ ነኝ” ብሎ ማቅራራት!!

ከተቆረጠው ይልቅ የኛ አንገት አናት ተሸክሞ ከመዞር ይልቅ ምን ሰራ? ምን ፈየደ? … የበደው በፍጥነት እየበረረ አንገትም ያለው? አንገት ያለው እያለ ሲበር ድንገት አንድ ክስተት ፊቱ ተገተረ።

97 ሱናሚ … ሕዝብ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይን አጥለቀለቀ። “ የፍየል ቆዳ ያለው? የፈየል ቆዳ ያለው?” ተባለ። የዛኔ ህወሃትም ሆን ኢህአዴግ በሕዝብ አቆጣጠር ሞተዋል። … በክብር ያንን ጊዜ ማለፍ ተሳናቸው። ልደቱና አየለ ጫሚሶ አዳዲስ የጓሮ ጀግና ሆነው ወጡ!! ዛሬ ላይ ሰርጥ ውስጥ ከመግባትና የባልደረባን አንገት ከመበጠስ… ዛሬ ሌላ ቀን ነው። አየለ ጫሚሶ አስከሬን መውጫ ቆመዋል። አባታቸው መንፈስ እንኳን መሆን አልቻለም። ልደቱ አለ። አዲስ ማሊያ ደርቷል። ብሄር … ደም አልባ ፖለቲካ ናፈቀን!! ቤት ያላችሁ ግቡ። ያበደው ወደ ቦሰና እያቀና ነው። ቦሰና ቀልብ ተሰበስባላች። ቦሰና እርጎ ናት። ቦሰና ጣፋጭ ናት። ቦሰና የማር ወለላ ናት። ቦሰና አንገቷ ይሰራል። የሚሰራ አንጎል ተሸክማበታለች። አንገት ቆረጣ ያዋጣል ያላችሁ ግፉበት። የዘመኑ ደግነት ነውና!! ስለም!! አንድ ነገር አትርሱ ” የጡት ቆረጣ እድገት መሆኑ ነው። አንገት ቆረጣ” ቦሰና ንች ያለቸው!!

Exit mobile version