Site icon ETHIO12.COM

ዘ- ኢኮኖሚስት “መንግስት ረሃቡን መጠቀሚያ አድርጎታል” ማለቱ አነጋጋሪ ሆነ

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ አለ የተባለውን ረሃብ እንደመሳሪያ ይጠቀመዋል በሚል ዘ ኢኮኖሚስት ያወጣው ዘገባ አነጋጋሪ ሆኗል። በርካታ የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ጋዜጠኖችና ሚዲያዎች የህግ ማስከበር የተባለው ዘመቻ ከተጀመረ አንስቶ ሚዛን የሳተና ለአንድ ወገን ያደላ ሪፖርት እንደሚያቀርቡ በተደጋጋሚ እየተነገረ ነው።

ስለ ዘመቻውም ሆነ አስቀድሞ ከዘመቻው በፊት በመላው አገሪቱ ሲካሄድ የነበረውን መተራመስ፣ መፈናቀል፣ ግድያና ግጭት ማን እንደሚያስተባብረው እየታወቀ ዝምታን መርጠው የነበሩት ሚዲያዎች አሁን ዘመቻ የጀመሩበት አግባብ አስገራሚ እንደሆነባቸው የሚገልጹ ያሉትን ያህል ” በጥቅም የሚደለሉ” የሚሏቸው ምሁራኖችም አሉ።

ላለፉት 28 ዓመታት ትህነግ በስልታን ላይ ሆኖ በርካታ የማይገቡ ተገባራትን ሲፈጽም እነዚህ ወገኖች ዝም ብለው እንደነበር ማስረጃ እየጠቀሱ የሚሞግቱ፣ በአብዛኞቹ ሚዲያዎች ተሰላችተዋል። በአገር ውስጥ ያለውን እውነታውን ሕዝብ ስለሚረዳው ዓላማው የበለጸጉ አገራትን ለማነሳሳት በመሆኑ ዜጎች ስር ስር እየተከተሉ ሚዲያዎቹን መሞገትና ማጋለጥ እንዳለባቸው አስተያየት እየተሰተ ነው። መንግስትም ዝምታ ሊመርጥ እንደማይገባው ሲገለጽ ነበር። ለዚሁ ነው መሰለ ፋክት ቼክ ተቋቁሞ መልስ በመስጠትና ሃሰተኛ መረጃዎችን በማስተባባል እየሰራ ነው። ይኸው መንግስት ያቋቋመው ፋክት ቼክ ለዘ ኢኮኖሚስት ከታች ያለውን ምላሽ ሰጥቷል። ትርጉሙን ፋና እንደሚከተለው አቅርቦታል።

“የኢትዮጵያ መንግስት ርሃብን እንደመሳሪያ ተጠቅሟል” በሚል ዘ ኢኮኖሚስት ያወጣውን ዘገባ መንግስት በፅኑ እንደሚያወግዝ አስታወቀ፡፡ መፅሄቱ በትግራይ ክልል ከተካሄደው የህግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻ ጋር በተያያዘ ባወጣው ዘገባ በኢትዮጵያ መንግስት እየተሰራ ያለውን ስራ በተመለከተ የተሳሳተና የተዛባ ፅሁፍ መጻፉን አስታውሷል፡፡ በሰራው ዘገባም “መንግስት በትግራይ ክልል ርሃብን እንደመሳሪያ እየተጠቀመ ነው” ማለቱ ተጠቅሷል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም መንግስት ለመፅሄቱ ግልጽ ደብዳቤ ጽፏል፡፡

በደብዳቤውም የኢትዮጵያ መንግስት ባለፉት ወራት ከ31 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ምግብና መድሃኒቶችን በዘመቻው ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ በማሰባሰብ ወደ ትግራይ ክልል መላኩን አስታውሷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በአካባቢው የዜጎችን ደህንነትና ሰላም ለማስጠበቅ ስራዎች መስራቱንም አንስቷል፡፡

ይሁን እንጅ መፅሄቱ በዘገባው የተወሰኑ ምዕራባውያንን እማኝ በማድረግ እርግጠኛ ያልሆነና የተዛባ መረጃ ማውጣቱንም ጠቅሷል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም በፅሁፉ “የመንግስትን ህገ መንግስታዊ ግዴታ ማጣጣሉን” በመጥቀስ፥ ጽሁፉ “መንግስት አቅመ ቢስ ነው ወደሚል ስድብ ያዘነበለ” መሆኑንም አውስቷል፡፡

በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ማሻሻያዎች እየተደረጉ መሆናቸውን ያነሳው ደብዳቤው በትግራይ ክልል የተካሄደው ህግን የማስከበር ዘመቻ ዋጋ የሚያስከፍል ቢሆንም አስፈላጊ ስለመሆኑም ገልጿል፡፡

ዘ ኢኮኖሚስት ከዚህ ቀደምም አፍሪካውያን መሪዎች “መጥፎ እና አቅመ ቢስ” ናቸው የሚል አመለካከት እንዳለው በመጥቀስም፥ ለአፍሪካውያን መሪዎች ያለው አመለካከትም እንደሚቆጨው አስታውቋል፡፡

fact check

Exit mobile version