Site icon ETHIO12.COM

የእናት አገር ጥሪ አዋጅ ታወጀ

የዱባይ ጸሃይ እንዳትሞቅ ተለክታ በመስፈሪያ ቤቱ ትፈሳለች። ባህር ላይ ተንጣሎ የሰፈረው ቤት የአረብ ንጉሳዊያን መኖሪያ መቅደስ እንጂ የአንድ ለማኝ አገር ዜጋ አይመስልም። ለጊዜው ፓላስ እንበለው። ፓላሱ በበረሃዋ ዱባይ የተከመረ ገነት ምሳሌ ነው። የክፍሎቹን ብዛት የቀን ሰራተኞቹ እንኳን የሚያውቁት አይመስልም።

እንደ ጸሃይ የሚየበራው ፓላስ ዳንኪራ ቤት፣ ማሳጅ ማድረጊያ፣ ቁማር ቤት፣ ዝግና ክፍት መዋኛ፣ ዘመናዊ የቢዝነስ ቢሮዎች፣ የሚስጢር መደራደሪያ ሳሎኖች፣ የመጎንጫ ባንኮኒ… ተዘርዝሮ አያልቅም። የተውሰነ አካሉ ከላይ በሪሞት የሚከፈት መቀናጫ ያለው ፓላስ። አንድ ኢትዮጵያዊ የተባለ የሚኖርበት … እምዬ አገሬ እንዴት እንዴት ስትታለቢ ኖርሽ?

ከፓላሱ ግርጌ ባህሩ ዳር ዝግጁ የሆነው የግል ጀላባው ለማመን ይከብዳል። ለስሙ የመዝናኛ ጀልባ ተባለ እንጂ መለስተኛ መረከብ ነው። ከነሙሉ መስተንግዶ እንግዶች እየተዝናኑ ይፈራረሙበታል። ባህር ላይ እየተንሳፈፉ አሻግረው የኢትዮጵያን ቆዳ እንዴት እንደሚገፉ ያሰላሉ። ከግል የንግድ መረከብ ጀምሮ በሪል ስቴትና ወደብ ማስተላለፍ ስራ ኢትዮጵያ ትገብረዋለች።

አንድ ቀን – ከአንድ እናት ጋር

በፍጹም ልጄ 20 ዓመት አለፈኝ

አለቀሱ ሶሰት ልጆቻቸውን ቀይሽብርና ነጭ ሽብር ተባብረው በልተውባቸዋል። ያበደው እኚህን ሴት በተደጋጋሚ ይጎበኛቸው ነበር። አንድ ጉልበተኛ ባለ ጊዜ እግቢያቸው ውስጥ ያለች አንድ ደሳሳ የተወረሰች ቢታቸውን ወደ ግሉ አዙሮ ሞታቸውን ይለማመን ነበር።

አይ ደርግ ከኚህና እኚህን መስል አዛውንት ላይ አንድ ክፍል የጭቃ ቤት ነጥቆ ሶሰት ብር አበላ ይከፍላል። እያስፈረመ … ያበደው እምባው መጣ። አሮጊቷን አሰበ። ብዙ ጊዜ አግኝቷቸዋል… ያ ክፉ ጎረቢታቸው ጸሎቱ ስምሮለታል። ባለ ጊቢ ሆኖ እሳቸው ቤት አልይ ሌላ ገንብቷል። ሃያ ሰባት ዓመት ምን ያልሆነ አለ? የዱባዩ ቀብራራም የሃያ ሰባቱ ዓመት ውጤት ነው።Related stories   “ አንገት ቆረጣ ” የ – ሰለጠነው የ- እርስ በርስ መበላላት!Powered by Inline Related Posts

ያበደው ሁለቱን መዘነ። ውሃ ላይ ቤተ መንግስት ገንብቶ ኢትዮጵያን የሚገፍ፣ ደሳሳ ቤታቸው ውስጥ መኖር ያልቻሉ ጡርተኛ እናት። ሁለቱም ዜጎች ናቸው። ሁለቱም ይማልባቸዋል። ያበደው ድንገት ዘለለ። እንደለመደው ቁልቁል ቸርቸልን አስነካው። አስከሬን ሳጥን መሸጫው ጋር ቆመ። ሰዎች ይመርጣሉ። ስፖንጅ ፍላራሽ ያለው ሳጥን.. ትራሱ ከፍ ያለ፣ ነጭ ቀለም፣ ምን አልባትም መጸዳጃ ቤት ያለው ብለው ይሆናል።

ያላቸው ማሰብ አቅቷቸዋል። የሌላቸውም ማሰብ አልቻሉም። ልዩነቱ እንዲህ ነው። ያበደው ድንገት መከከላቸው ገባና ” አስከሬኖች” አላቸውና ተፈተለከ። ሽጉጥ ያቀባበለ ነበር።

ለውጡ በዚህ አለመግባባት ውስጥ መጣ። አለመግባባቱ ወዲያው ጠለፈው። አካለበው። ወገን እስኪ አይንህ ይሸቅል። ጆሮህም የሰማውን ያጣጥም። አያያዙ እንደዚያ አይመስልም? የግል ጀት ያለው ወይም የሚከራይና የውስጥ ሱሪ የሌላቸው ዜጎች ተፋጠው እያለ ለውጥ መጣ!!

ቦሰና ይህን ጉዳይ በድንብ ትገልጸዋለች። ” ተፋጠዋል” ትላለች። ወደ “ሰዎቹ” ሰፈር ስትሄድ ይታዘበችውን ታፈሰዋለች። ቪላ፣ የግንብ አጥር፣ የኤሌክትሪክ ሽቦ፣ የጀርመን ውሻ፣ ዘበኛ ወይም ጥበቃ፣ ክላሽ፣ መትረየስና ሽጉጦሽች፣ ከዛም በላይ ፈንዲሻ … ቦሰና ” የከፋው ሲመጣ ሰው በርዥም አጥር ሊሸሸግ፣ ስንቱን ገሎ ሊያስቆም” ሰው ጅል ነው። ሃብት ሲበዛ አንጎል ማሰብ ያቆማል። የራበውም፣ የጠገበውም ማሰብ ያቆመበት አገር … ቦሰና ” እንዴት መግባባት ይቻላል? ሰውየው እዚህ መሃል ሆነው ነፈሩ” ብላ እንባዋን አቆረዘዘች፤

“ሰውየው ይበላሉ፣ ይጠጣሉ፣ ግብር መክፈያ ሄደው ወገባቸውን ይፈትሻሉ…” ተብሏልና ደስ ላላቹህ ” እንኳን አብሮ ደስ ያለን” ይላል ያበደው። ግን ግን ጠዋት ጠዋት የጠቅላይ ሚኒስትር ” እንደምን አደራቹህ ” የሚናፍቀው ቡድን ማበቡ … ያበደው ፈገግ አለና መሬቱን በግሩ እየመታ አላገጠ። ግን ቁልቁል እየበረረ ነው። ድንገት መከላከያ ጥፈት ቤት ሲደርስ ቆመ።Related stories   “ አንገት ቆረጣ ” የ – ሰለጠነው የ- እርስ በርስ መበላላት!Powered by Inline Related Posts

ትልቁን ፖስተር አየው። በዛናው በኩል አምባሳደር ፊልም ሊያዩ የተኮለኮሉ አሉ። ያበደው በመከላከያው ፖስተር ውስጥ ኢትዮጵያን ስለሚያይ ምርጫው መከላከያ ሆኗል። የመከላከያ ደሞሽ ከፋዮችን በልቡ ሰላም አላቸው። ገበያቸው የደራላቸው አጋግሰሶች እንደሆኑ ያውቃል።

በምስሉ አገሩን ሊጠብቅ የቆመውን ጀግና እጅ አየ። መሳሪያ ይዟል። ይህኔ ያበደው አዞረው። በ”ጥርስ ሃኪም ነን”ሽፋን መሳሪያ ይቸረችራሉ፤ ሌሎችም በስጋ ተመርጠው መሳሪያ ይደልላሉ። ኢትዮጵያ ለመሳሪያውና ለአቀባባዮቹ ትከፍላለች። ተበድራ የምትከፍለው ለአምራቾቹ ብቻ ሳይሆን እንዲገፏት ለተመደቡት ነው። እንደዚህ ነው የምትታለበው። ታልባ ታልባ ታልባ ….

ያበደው እማማን አስታወሰ። አማማ የሉም። ሌሎች ማሰብ ያልቻሉም የሉም። ሁሉም አፈር ሆነዋል። እማማ ያረፉት አንድ ቀን ሳያማቸው ነው። እዛው ምድጃቸው ስር ሲርመጠመጡ፣ አሹቅ ሲቀቅሉ አምሽተው በዛው … ሌሎቹ ገደል ለገደል… ማሰብ ማቆም እንዲህ ነው።

ፓላስ ያልቹህ ንቁ፣ ተማሩበት፣ ጊዜውን ዋጁ … ያበደው መከላከያ በር ላይ ካለው ታፔላ ላይ አይኑንን የነቀለው ቦታውን እንዲለቅ ሲነገረው ነው። አሁን ጉዞ ወደ ቦሰና ነው። ቦሰና የተወለደችበትን ቀን በትክክል አታውቅም። ግን በግምቷ ዛሬ ተወልዳለች። ዛሬ ሞትን ሳይሆን መወለድን እያሰብች ነው። ግን አንድ ዜና እንዳላት ተናግራለች።

ቡና፣ ፈንዲሻ ዳቦ… ቃል የግባቸውን ቦሰና ተናገረች። “አሁን ወዶ ዘማች እሆናለሁ” አለች። “በቁሜ ግብጽ አገሬን ስትበላ አላይም” ስትል እንደመፎከር አደረጋት። ደጎል ው ው ው … እያለ ዘለለ። ” ይህ ነው ምኞቴ እኔ ለአገሬ … ” አዝማች አወረደች። ግብጽ መጥታላች። ሲነጋ እናት አገር ጥሪዋን በይፋ አወጀች!! መንግስት ብቻውን አይችልማ። እነንሳ !! እንነቃ!! በረባ ባልረባ የምታላዝኑ አቁሙ!! የኢትዮጵያን ባንዲራ ለብሳቹህ የምትጫወቱ በቃ!! ሰላም ይብዛላቹህ !!

Exit mobile version