Site icon ETHIO12.COM

የዲፕሎማሲ ብቃትና ክህሎትና የአገር ፍቅር ለዲፕሎማት ምደባ ቅድሚያ ትኩረት ሆኑ

ወቅቱ የሚጠይቀውን የዲፕሎማሲ ብቃትና ክህሎት የታጠቀና የአገር ፍቅር ያለው ዲፕሎማት ማሰማራት ትኩረት ይሰጠዋል – አቶ ደመቀ መኮንን “ወቅቱ የሚጠይቀውን የዲፕሎማሲ ብቃትና ክህሎት የታጠቀና የአገር ፍቅር ያለው የሰው ኃይልን በዲፕሎማሲው መስክ ማሰማራት ትኩረት ይሰጠዋል” ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሂዷል።የግምገማ መድረኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንን ጨምሮ የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ትናንት ተካሂዷል።በግምገማ መድረኩ ከዋናው መሥሪያ ቤት በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት ማለትም የስትራቴጂክ ጥናት ተቋምና የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጄንሲ ሪፖርት ቀርቦ ተገምግሟል።

በውይይቱ ማጠቃለያ አቶ ደመቀ መኮንን ለሰራተኞች በሰጡት ማሳሰቢያ “ወቅቱ የሚጠይቀውን የዲፕሎማሲ ብቃትና ክህሎት የታጠቀና የአገር ፍቅር ያለው የሰው ኃይልን በዲፕሎማሲው መስክ ማሰማራት ትኩረት የሚሰጠው ነው” ብለዋል።በተጨማሪም ለዲፕሎማሲ ሥራ ዜጎችን በአጋርነት በማሰለፍ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ መሥራት እንደሚያስፈልግ አጽዕኖት ሰጥተው መናገራቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

Exit mobile version