ወቅቱ የሚጠይቀውን የዲፕሎማሲ ብቃትና ክህሎት የታጠቀና የአገር ፍቅር ያለው ዲፕሎማት ማሰማራት ትኩረት ይሰጠዋል – አቶ ደመቀ መኮንን “ወቅቱ የሚጠይቀውን የዲፕሎማሲ ብቃትና ክህሎት የታጠቀና የአገር ፍቅር ያለው የሰው ኃይልን በዲፕሎማሲው መስክ ማሰማራት ትኩረት ይሰጠዋል” ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሂዷል።የግምገማ መድረኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንን ጨምሮ የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ትናንት ተካሂዷል።በግምገማ መድረኩ ከዋናው መሥሪያ ቤት በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት ማለትም የስትራቴጂክ ጥናት ተቋምና የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጄንሲ ሪፖርት ቀርቦ ተገምግሟል።
በውይይቱ ማጠቃለያ አቶ ደመቀ መኮንን ለሰራተኞች በሰጡት ማሳሰቢያ “ወቅቱ የሚጠይቀውን የዲፕሎማሲ ብቃትና ክህሎት የታጠቀና የአገር ፍቅር ያለው የሰው ኃይልን በዲፕሎማሲው መስክ ማሰማራት ትኩረት የሚሰጠው ነው” ብለዋል።በተጨማሪም ለዲፕሎማሲ ሥራ ዜጎችን በአጋርነት በማሰለፍ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ መሥራት እንደሚያስፈልግ አጽዕኖት ሰጥተው መናገራቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
- የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
by topzena1
“ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ የሆኗት ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው።…
Read more: የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
- አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ
by topzena1
“ወገኖቼ እንማርና እናስተምር፣ ወንጀልን እንጸየፈው፣ እንጥላው፣ ወንጀልን ተጸይፈን ወንጌልን እንውደደው፣ በወንጌል እንኑር፣ ወንጌል ሕጓም ስርዓቷም ያማረች ናት፤…
Read more: አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ
- ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው
by topzena1
ቤት የተባለች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች፦ “ደም ማነስ የያዘኝ በአሥራዎቹ ዕድሜ ሳለሁ ነው። ቶሎ ይደክመኝ፣ አጥንቶቼን ይቆረጥመኝ፣…
Read more: ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
by topzena1
ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ ከሃምሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ገለልተኛ ወገኖች…
Read more: የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?