የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን የደህንነት ተቋማት በአካባቢያዊ ጉዳዮች እና በአቅም ግንባታ መስኮች በትብብር ለመስራት ተስማሙ አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን የደህንነት ተቋማት በአካባቢያዊ ጉዳዮች እና በአቅም ግንባታ መስኮች በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከደቡብ ሱዳን የውስጥ መረጃ ቢሮ ዳይሬክተር ጀነራል አኮል ኮር ኩክ ጋር በዛሬው ዕለት በሁለትዮሽ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ለኤፍቢሲ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤
የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን የደህንነት ተቋማት በአካባቢያዊ የጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ የነበራቸውን ትብብር አጠናክረው ለመቀጠል ተስማምተዋል።በተለይ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን፣ ሽብርተኝነትንና በድንበር አካባቢ የሚታዩ ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ የመረጃ ልውውጥ በማድረግ ቀጣናዊ ሰላምንና ደህንነትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን የደህንነት ተቋማት በአቅም ግንባታ መስኮች በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን የጠቆመው መግለጫው፤
በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ስር በሚገኘው ብሄራዊ የመረጃ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ አማካኝነት ለደቡብ ሱዳን ባለሙያዎች ስልጠናዎች ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጿል።
- የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
by topzena1
“ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ የሆኗት ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው። አንዳንዶች በስሟ…
Read more: የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
- አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ
by topzena1
“ወገኖቼ እንማርና እናስተምር፣ ወንጀልን እንጸየፈው፣ እንጥላው፣ ወንጀልን ተጸይፈን ወንጌልን እንውደደው፣ በወንጌል እንኑር፣ ወንጌል ሕጓም ስርዓቷም ያማረች ናት፤ ወንጌላዊ መኾን…
Read more: አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ
- ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው
by topzena1
ቤት የተባለች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች፦ “ደም ማነስ የያዘኝ በአሥራዎቹ ዕድሜ ሳለሁ ነው። ቶሎ ይደክመኝ፣ አጥንቶቼን ይቆረጥመኝ፣ እንዲሁም ትኩረቴ…
Read more: ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
by topzena1
ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ ከሃምሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ገለልተኛ ወገኖች አስታውቀዋል። ጎን…
Read more: የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?