Site icon ETHIO12.COM

ባለቤት አልባ ሕንጻዎች በግልጽ ጨረታ እንዲሸጡ ተወሰነ፣ ኮንዶሚኔም ቢቶቹ ለተጠቃሚዎች በህግ አግብባ ይሰጣሉ

የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ባካሄደው ስብሰባ ህገ ወጥ የመሬት ወረራ፤ ባለቤት አልባ ህንፃዎች፤ የኮንደሚኒየም ቤቶች፤ የቀበሌ መኖርያና ንግድ ቤቶችን አስመልክቶ በጥናት የተገኙ ግኝትቶች ላይ የውሳኔ ሃሳብ አስተላለፈ፡፡ባለቤት አልባ ህንጻዎች ይሸጣሉ።

የከተማው ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የከተማው አመራር በሪፎርሙ በገባው ቃል መሰረት ምንም እንኳ ቢዘገይም የነዋሪው ቅሬታ መነሻ የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት እና በተጨባጭ ጥናት በመመርኮዝ ለማጣራት እና ለመለየት የተደረገውን ጥረት ያመሰገኑ ሲሆን ወደፊት መወሰድ አለበት ባሉት እርምጃ ላይ አፅንኦት ሰጥተው ተወያይተዋል፡፡

በመሆኑም በጥናቱ የተገኙ 322 ባለቤት አልባ ህንጻዎች በግልፅ ጨረታ ተሸጠው ገንዘቡ ወደ መንግስት ካዝና ገቢ እንዲሆን፤ በጥናቱ የተገኘው ህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ፤ ባዶ ሆነው የተገኙ በድምሩ 21,695 የኮንዶሚኒየም ቤቶችን በማስለቀቅ ለተጠቃሚዎች እንዲታደል፤ በዋናነት በ1997 ተመዝጋቢ የሆኑና በቋሚነት እየቆጠቡ ላሉ ነዋሪዎች በእጣ እንዲተላለፍ፤ የቀበሌ ቤቶችን አስመልክቶ በህገ-ወጦች የተያዙ የመኖርያ ቤቶች ግልፅ የሆነ መስፈርት ወቶላቸው ለደሆች፤ ለአቅመ ደካሞችና ለተለያየ ችግር ለተጋለጡ ነዋሪዎች እንዲሰጥ፤ የቀበሌ የንግድ ቤቶች በህገ-ወጥነት ከያዙት ሰዎች ተነጥቆ ለስራ አጥ ወጣቶች በእጣ እንሰጥ ሲሉ ወስኗል፡፡

ካቢኔው በቀረቡት አጀንዳዎች ላይ በሰፊው የተወያየ ሲሆን ይህ ችግርና ስርዓት አልበኝነት 1997 ጀምሮ እየተንከባለለ የመጣ መሆኑን እና ወደፊት እንዳይደገም በፅናት እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያሰራቸው መረጃ ያመለክታል ፡፡

Exit mobile version