የአፍሪካ ህብረት ለአባል ሃገራቱ የሚሆን ተጨማሪ 400 ሚሊየን መጠን ያለው የኮሮና ቫይረስ ክትባት እንደሚያቀርብ የአፍሪካ በሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል /ሲዲሲ/ አስታወቀ፡፡
የማዕከሉ ዳይሬክተር ጆን ንከንጋሶንግ ክትባቱ የሚገኘው የኦክስፎርዱን አስትራዜኒካ ቀመር በመጠቀም ክትባት ከሚያመርተው ሴረም ከተሰኘ የህንድ ተቋም ነው ብለዋል፡፡
ህብረቱ ከዚህ ቀደም 270 ሚሊየን መጠን ያለው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለአባል ሃገራቱ እንደሚያቀርብ መግለጹ ይታወሳል፡፡ የአሁኑ 400 ሚሊየን መጠን ያለው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ሲታከልበት ለአባል ሃገራቱ መልካም ዜና መሆኑን ነው ዳይሬክተሩ የገለጹት፡፡
አፍሪካ 60 በመቶ የሚሆነው ህዝቧን የመከላከል አቅም ለማዳበር 1 ነጥብ 5 ቢሊየን መጠን ክትባት እንደምትፈልግ የተገለጸ ሲሆን ለዚህም ከ7 እስከ 10 ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል ተብሏል፡፡
የአፍሪካ ህብረት ከዚህ ቀደም አፍሪካውያን ከሚያዝያ እስከ ሰኔ ባለው ጊዜ ውስጥ ቢያንስ 50 ሚሊየን መጠን ያለው ክትባት እንደሚያገኙ መግለጹ ይታወሳል፡ እስካሁን ከአባል ሃገራት መካከል ሞሮኮ፣ ግብጽ፣ ሲይሼልስ እና ጊኒ ዜጎቻቸውን መከተብ ጀምረዋል፡፡
(ኤፍቢሲ)
- የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
by topzena1
“ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ የሆኗት ግን ጥቂቶች ብቻ…
Read more: የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
- አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ
by topzena1
“ወገኖቼ እንማርና እናስተምር፣ ወንጀልን እንጸየፈው፣ እንጥላው፣ ወንጀልን ተጸይፈን ወንጌልን እንውደደው፣ በወንጌል እንኑር፣ ወንጌል ሕጓም ስርዓቷም ያማረች…
Read more: አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ
- ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው
by topzena1
ቤት የተባለች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች፦ “ደም ማነስ የያዘኝ በአሥራዎቹ ዕድሜ ሳለሁ ነው። ቶሎ ይደክመኝ፣ አጥንቶቼን…
Read more: ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
by topzena1
ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ ከሃምሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ገለልተኛ…
Read more: የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?