የአፍሪካ ህብረት ተጨማሪ 400 ሚሊየን የኮሮና ቫይረስ ክትባት እንደሚያቀርብ አስታወቀ

የአፍሪካ ህብረት ለአባል ሃገራቱ የሚሆን ተጨማሪ 400 ሚሊየን መጠን ያለው የኮሮና ቫይረስ ክትባት እንደሚያቀርብ የአፍሪካ በሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል /ሲዲሲ/ አስታወቀ፡፡

የማዕከሉ ዳይሬክተር ጆን ንከንጋሶንግ ክትባቱ የሚገኘው የኦክስፎርዱን አስትራዜኒካ ቀመር በመጠቀም ክትባት ከሚያመርተው ሴረም ከተሰኘ የህንድ ተቋም ነው ብለዋል፡፡

ህብረቱ ከዚህ ቀደም 270 ሚሊየን መጠን ያለው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለአባል ሃገራቱ እንደሚያቀርብ መግለጹ ይታወሳል፡፡ የአሁኑ 400 ሚሊየን መጠን ያለው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ሲታከልበት ለአባል ሃገራቱ መልካም ዜና መሆኑን ነው ዳይሬክተሩ የገለጹት፡፡

አፍሪካ 60 በመቶ የሚሆነው ህዝቧን የመከላከል አቅም ለማዳበር 1 ነጥብ 5 ቢሊየን መጠን ክትባት እንደምትፈልግ የተገለጸ ሲሆን ለዚህም ከ7 እስከ 10 ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ከዚህ ቀደም አፍሪካውያን ከሚያዝያ እስከ ሰኔ ባለው ጊዜ ውስጥ ቢያንስ 50 ሚሊየን መጠን ያለው ክትባት እንደሚያገኙ መግለጹ ይታወሳል፡ እስካሁን ከአባል ሃገራት መካከል ሞሮኮ፣ ግብጽ፣ ሲይሼልስ እና ጊኒ ዜጎቻቸውን መከተብ ጀምረዋል፡፡

(ኤፍቢሲ)


See also  ጥቂት የዘይት ነጋዴዎች ምርታቸውን ያሸሻሉ፤ መንግስት አርምጃ መውሰድ ጀምሯል

Leave a Reply