Site icon ETHIO12.COM

በእነ ጃዋር የህክምና ጥያቄ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሁሉንም ተከራካሪዎች ጥያቄ ውድቅ አደረገ፤ ቃሊቲ ሆነው ይታከማሉ፤

በእነ ጃዋር ጉዳይ ይግባኝ የቀረበለት የየቅላይ ፍርድ ቤት የክፍተኛውን ፍርድቤትና የአቃቤ ህግ ይግባኝ ውድቅ አድርጎ አዲስ ውሳኔ አሳለፈ። የፌደራል ማረሚያ ቢት ምክትል አስተዳዳሪ ታስረርው እንዲቀርቡ ታዘዘ።

“ሁከት በመቀስቀስና  ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት በመሞከር” በሚል ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸው የኦፌኮ አመራሮች  አዲስ በሚቋቋም የሐኪሞች ቡድን ቃሊቲ ሆነው እንዲታከሙ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መወሰኑ ተሰማ።

አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባና በተመሳሳይ ጭብጥ የተከሰሱት የረሃብ አድማ ማድረግ ጫና ለመፍጠር መሞከራቸውና የጤናቸውን ሁኔታ ደግሞ በግል ሃኪሞቻቸው መከታተል እንዲችሉ እንዲደረግ መጠየቃቸው የሚታወስ ነው። 

እነ ጃዋር በግል ሐኪሞቻቸዉ ይታከሙ ወይስ በመንግስት ሐኪሞች የሚለዉ ልዩነት ሰፊ መከራከሪያ ሆኖ ቆይቶ ነበር። ዛሬ ይፋ እንደሆነው በጉዳዩ ይግባኝ የቀረበለት ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትን ዉሳኔና ዉሳኔዉን የተቃወመዉን የጠቅላይ አቃቤ ሕግን ይግባኝ ዉድቅ አድርጎ አዲስ ዉሳኔ አሳልፏል።

በዉሳኔዉ መሠረት የሐኪሞች ቡድን ተቃቁሞ፣ ቡድኑ ተከሳሾችን እታሰሩበት ቃሊቲ ወሕኒ ቤት ድረስ እየሔደ ያክማል።በሌላ በኩል ከተከሳሾች ጠበቆች አንዱ እንዳስታወቁት የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እስካሁን የሰጠውን ውሳኔ ወሕኒ ቤት ባለማክበሩ የፊታችን ሃሙስ የፌዴራሉ ማረሚያ ቤት ምክትል አስተዳዳሪ ታስረው እንዲቀርቡ አዟል።


Exit mobile version