Site icon ETHIO12.COM

“ፍትህ ለትግራይ! ሞት ለመከላከያ ሰራዊትና … በትግራይ ሕዝብ ስም ትህነግ የመዘዙ ምንጭ ላይሆን?

ድሮ ገና በፊት የወደፊቱ የታያቸው ” በስሜ አታድርጉት በሉዋቸው” ሲሉ እያለቀሱ ለምነዋል። ጀርመኖች አይሁዶችን ሲጨፈጭፉ ነበር የወደፊቱ የታያቸው ጀርመኖች ” do not do it by my name” ያሉትና ገዢዎቹን የተቃወሙት ወይም ስትጨፈጭፉ በራሳችሁ ስም ጨፍጭፉ እንደማለት ነበር። በአገራችን ብሂል ” ራሳችሁን ቻሉና በወንጀሉ ተጨማለቁ” እንደማለት ነው።

ትህነግ ገና ከጅምሩ የትግራይን ህዝብ ነጻ ለማውጣት አቅዶ ጫካ ገባ። በችሎታም ይሁን በደርግ ችግር ትግራይን “ነጻ” አወጣ። ወይም አስር አለቃ ለገሰ አስፋው ትግራይን ለቆ ወጣ። ከዛ ትህነግ ግዛቱን አስፍቶ ኢትዮጵያ ላይ ተቀመጠ። ለምን ወቅቱ በውስጣዊ ብሶትና ዓለም አቀፋዊ የርዕተ ዓለም ለውጥ አመቺ ስለነበር። ከዛ መንግስት ሆኖ ሃያ ሰባት ዓመት ኢህአዴግ ሆኖ ” ታላቋን ትግራይ” እያለመ ኢትዮጵያን ገዛት። ይህ ሚስጢር አይደለም። የምንወዳቸው ባልደረቦቻችን ቢራ ላይ፣ መሪዎቻችን በመማኒፌስቶ፣ ትህነግን የተለዩ በምስክርነት እየነገሩን ኖርን።

የታሰበው የገር ምስረታ ጊዜ አርባ ዓመት እንደሚፈጅ ነበር በዕቅዱ የተቀመጠው። አርባ ዓመት የሚጋለብ ኦህዴድ፣ ኢህዴን፣ ድህዴን ሊኖር ባለመቻሉ ትህነግ በሃያ ሰባት ዓመቱ ወይም ከዕቅዱ አስራ ሶስት ዓመት በፊት ተገፈተረ። ሲገፈተር አማራጭ ስላልነበረው ለውጡን ተቀብሎ በፕሮፓጋንዳ ሊወተረተር ሞከረ። የለውጡ ባህሪ ግን አልመች እያለው በቀን ለተደጋጋሚ ጊዜ ያስተፋው ጀመር።

በትህነግ ባህል አንድ ጉዳይ በወራት ግምገማና የግምገማ ውጤት ምናምን የሚል ኮተት የተላበሰ አሰራር ባህል ስለነበር አዲሱ ለውጥ በነጋና በጠባ ቁጥር አዳዲስ ነገር እየወሰነ ሲበር አብሮ መሄድ ችግር ሆነበት። ትህነግ ወደ ትግራይ በፈቃዱ ከተሰደደ በሁዋላ ” የአብይን ፍጥነት አልቻልነውም” በሚል እርስ በርስ ይነታረኩ ነበር። ፍጥነቱ በአጀንዳ ላይ አጀንዳ እየደረበባቸው ከለውጡ ጋር መሄድ ባለመቻላቸው አዲሱን ብልጽግና ተለይተው በቀደመው ቆዳቸው ለመቀየር ወሰኑ።

የክበበው ጨውታና አዲስ መንግስት ምስረታ

ወደ ትግራይ ያቀናው የትህነግ ሃይል በትግራይ ቅቡል ለመሆን ሕዝቡን ” ተከበሃል” በሚል ስብከት በማሸማቀቅና ጠላቶቹ የተደረጉትን ክፍሎች እለት እለት በማሳየት የትግራይን ህዝብ አሳመመ። ከዛ መልሶ ትህነግ ብቸኛው አስፕሪን ሆነ። ዲጂታል ወያኔ የሚባለው ጦሩ ይህንኑ ሃሳብ እያጋመ ህዝቡ ሲነጋና ሲመሽ አስፕሪኑን እንዳይረሳ ማሳሰቡን ተያያዘ። ጎን ለጎን ዘመቻ ” እረኛውን ምታ መንጋው ይበተናል” ተጀመረ።

ዘመቻው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ለማጥፋት የወሰነ ሆኖ ተቀጣጠለ። ለውጡን ተከትሎ ለስራ አዲስ አበባ አቅንቶ የነበረ የዚህ ዘጋቢ ባልደረባ በመረጃ እንዳረጋገጠው ትህነግ ለዘመቻ ” እረኛውን ምታ” ዘጠኝ ቢሊዮን ብር ድረስ መድቦ ነበር። ይኽ የመረጃው ምንጭ አዲስ አበባ እያለ በጥቅሉ ለተያዙት እቅዶች ከተመደበው በጀት ጥቅም ላይ የዋለው 17 በመቶ ነበር። ይህ እንግዲህ ከልወጡ አንድ ዓመት ተኩል በሁዋላ የተሰላ ስሌት ነበር።

ዲጂታል ወያኔ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ አነጣጥሮ ዘመቻውን ሲያፋፍም ሌሎች ተከፋይና ተለጣፊ ሚዲያዎችና ፖለቲከኞች መንግስት እንዲመሰረት ይሰሩ ነበር። ትህነግ ከብልጽግና ፓርቲ በይፋ ሲለይ የፌደራል ሃይሎች ተብለው በገሃድና በህቡዕ ወደ መቀሌ ለሚዘምቱት የአዲስ መንግስት ምስረታ ልዑካኖች በሶስት ወር ብቻ የባከነው ሃብት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ነበር። ይህንን ሃቅ እነ ባይቶና ያውቁታል። ነገሩ ” እልህ ምላጭ ያስውጣል” ነውና አያነሱትም። ለነገሩ ምርጫ ሲሸነፉ ማስተዛዘኛ አንድና ሁለት ሚሊዮን እንደ ደረጃቸው ቀምሰዋል። ከዛ የፌደራል ሃይሎች ቅዠቱ ሲገባቸውና የመሃል መንግስት አቅሙን እያጠነከረ ሲመጣ ነቅለው አዲስ አበባ ገቡ። በዛው ነገሩም በጀቱም አብረው ወደሙ።

ይህ ሲከሽፍ ሚሊሻና ልዩ ሃይል ማስመረቅ፣ ኮማንዶ ማዘጋጀት፣ ኮማንዶ ትርኢት ሲያሳይ ማሳየት ተጀመረ። እነ ዳንኤል ብርሃኔ ” ግዜ ሳንፈጅ፣ ቶሎ ቶሎ ብለን” እያሉ ለሃጫቸውን ይተፉ ጀመር። እነ አቶ ስዬ “ጦርነት ባህላችን” እያሉ የትግራይ ህዝብ ባዮሎጂካሊ የጦርነት የልቀት ደረጃ ህዋስ እንዳለው ሰበኩ። ድብረጽዮን ታበዩ። ሁሉም እየተነሳ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ዓይን ላይ አዋራ መርጨት ስራቸው ሆነ። ይህንን ትምክህት የሚሰሙ ቡቃያዎችና ህሊናቸው የላሸ የመሃል አገር ፖለቲከኞች ለውጡ አናቱ ሲበጠስ ታያቸው። ሃብታሞች ሳይቀሩ ንግዳቸውን፣ ንብረታቸውን ጥለው ወደ ቅዠቱ ዓለም አቀኑ። ድህነቱን ችሎ፣ ስንዴ እየተሰፈረለት ሲኖር የነበረው የትግራይ ህዝብ አፍታም ሳይቆይ ጩኸቱ ዓለምን አዳረሰ። ርሃብ፣ እልቂት፣ ስቃይ … ከትግራይ እየተቀዳ ለዓለም ይዘራ ጀመር። የተባለው ሁል እንዳልሆነ ሆነ

የማይናቅ ሃይልና ግንባታ – ያልተደረመሰው ጉልበት

“ጥጋበኛ ጦጣ የተኛ አንበሳ ቆለጥ ነካች – ከፈር ተደባለቀች ” እንደተባለው በእብሪት የተነፋው ትህነግ መንግስትን ለማዛል የሄደበት መንገድ ሙሉ በሙሉ ባለመሳካቱ የምርጫ ዘፈን ጀመረ። ህግና ደንብ ከሚፈቅደው ውጭ ምርጫ አካሄደ። ትህነግ ምርጫ ለማካሄድ የውሰነው ለራሱ ፈልጎት ሳይሆን ቢያንስ ኦሮሚያ ላይ የሱን ፈለግ ተከትለው በማስገደድ ምርጫ ሊያስደርጉ የሚችሉ ጉልበተኞች ቃል ስለገቡለት እንደሆነ አሁን እስር ላይ ያሉትና የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ እኩል መረጃ አለን። ምላሽ ካለ ማስረጃ መጥቀስ ውስጥ እንገባለን። ከዛም ካለፈ ሹመቱና ስልጣኑ እንዴት እንደተከፋፈለ አቀርባለሁ።

ምርጫ አስገድዶ ማካሄዱ ሳይሳካ ሲቀር ” መንግስት የለም” የሚለው አዲስ ድራማ ቀነ ገደብ ቆርጦ ተዘጋጀ። ፍርድ ቤት ያሉት ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው፤ መንግስት ምርጫ ያራዘመበት መንገድ አግባብነትን ትተነው ” ምርጫ አያስፈልግም” ሲሉ የነነሩት ሁሉ በአንድ ጀንበር ተነስተው እጅ ጠምዛዥ ሆኑ። አዲስ አበባን የማተራመሱ የተቀናበረ ዘመቻ የመንግስት የፕሮፕጋንዳው ክፍል የላሸቀ መሆኑ እንጂ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ዘግናኝ ነበር። ምን አባትም በቁጥጥር ስር በመዋሉ ዝምታ ይሻላል ተብል ካልሆነ ቸውታው የሻሞላ እንዲሆን ነበር የታሰበው።

ይህ ሲከሽፍ ነው እንግዲህ ሃያ ዓመት ጉድጓድ ውስጥ የኖረውን፣ የትግራይ ህዝብ ዘበኛ የነበረውን፣ በየወሩ ከሚያገኛት ደመወዙ እያዋጣ ትምህርት ቤትና ጤና ጣቢያ ሲገነባ መንገድ ሲያስገነባ የኖረውን፣ ወልዶና ክብዶ የቆየውን፣ የህይወቱን ምርጥ እድሜ እዛው በረሃ ውስጥ የጨረሰውን ታማኝ ሃይል በተኛበት መቸፍቸፍ የተጀመረው። ማረድና አስከሬናቸው ላይ መዝፈን፣ አስከሬን ልብስ አውልቆ ለአውሬ ማስበላት፣ እንዳይቀበር አድርጎ አሞራ ሲነጫቸው እያዩ እስክስታ መውረድ፣ የተቀሩትን ጫማ አስወልቆ፣ ትጥቅ አስፈትቶ / የሚሰድቧቸውን መድገም/ አያስፈልግም በሰልፍ ሲነዷቸውና በሲኖ ትራክ ሲጨፍልቋቸው እያዩ አላዩም። እየሰሙ አልሰሙም። አድርገው አልተጸጸቱም። በጥቅሉ ድርጊቱን በገሃድ ለማውገዝ አልወደዱም። ይህ የተገነባውና ያልተደረመሰው ሃይላቸው ነው። ምክንያቱም ሚዛናቸውን እንዲያጡ ተደርገው ተሰርተዋል። ሁሉም እንደ ፋብሪካ ምርት እንዲያስቡ ሆነዋል። ወይም ማሰቢያ ቺፕስ ጎርሰዋል።

ዛሬ – ሽንፈትን በሳይበርና በንክኪ

ያለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ትህነግ ከዋናው መሪነት ቀጥሎ የውሽ ጉዳይ ሚኒስትር ቦታን፣ ከዛም በላይ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለባቸው ቦታዎች የራሳቸውን ሰዎች ከመደብ አልፎ ከፍተኛ ሃብት የሚያፈሱባቸው ወስዋሽና ሚዲያዎችን አደራጅተዋል። ከዛም አልፎ ምን እንዳደረገች በውል ጥፋቷ የማይነገራት ኢትዮጵያ ላይ ለተያዘው እቅድ ታማኝ አስፈጻሚ በመሆን የተወዳጇቸው አገራት ባላመኑትና ባልጠበቁት ፍጥነት ትህነግ ሲመታ በፍጥነት የተጀመረው የሚዲያና የዓለም ዓቀፉ ተቋማት የተቀናጀ ዘመቻ ነው።

ዘመቻው በየደቂቃው በሚናበብ መልኩ የሚሳለጥ ሲሆን ለማይክድራ ጭፍጨፋ ጆሮ ዳባ ብሏል። ይባስ ብሎ ማይካድራ የጨፈጨፉ ነብሰ በላዎችን ምስክር አድርጎ ይፈርዳል። ፈራጁ አቶ ፍስሃ ተክሌ የአድዋ ጅል የስብሃት ሚስት የሚያገባ ትግሬ ነው። መስክሩ ያላቸው እነሱ ራሳቸው ናቸው። ውሳኔ የሚሰጡትም በዚሁ አሰራር ነው። እንዴት ይህ ሰው የማይክራን ጭፍጨፋ ያምናል?

ሲጀመር አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሃቀኛ እና ገለልተኛ ቢሆን ኖሮ አንበጣ ሲያባርር እና የገበሬውን እህል ሲሰበስብ ውሎ ደክሞት በተኛበት የተጨፈጨፈውን ሰሜን ዕዝ፣ጡታቸው የተቆረጡ ሴት የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ በሲኖ ትራክ የተደፈጠጡ የኢትዮጵያ ወታደሮች፣ ሬሳቸው ላይ እምበር ተጋዳላይ ስለ ተጨፈረባቸው ድንበር ጠባቂ የሰራዊት አባላት፣ ራቁታቸውን በባዶ እግር ስለተሰደዱ፣ ስለታፈኑና ስለተሰቃዩት የሰሜን ዕዝ አባላት አጣርቶ ጥሬ አውነቱን በዘገበ ነበር። ዳሩ ግን አምነስቲ ዋናው አልቃሽ በመሆኑ ስለዚህ ግፍ ትንፍሽ አይልም!!! ምክንያቱም ይህንን ሪፖርት ቢያደርግ ለተፈጠረው ምስቅልቅል ቀውስ ዋና ተጠያቂው ትህነግ/TPLF እንደሚሆን ያውቃልና፤ ሲል ደጀኔ አሰፋ ፌስቡኩ ላይ ጽፏል

ባለጥጎቹ አገራት አንድ ወታደር ሲመታባቸው፣ ወይም ምክንያት ፈልገው የሚወስዱት እርምጃ እየታወቀ ኢትዮጵያ ተገዳ የገባችበትን ጦርነት ወደ ጄኖሳይድ ለመውሰድ መረባረቡ ዛሬ የታሰበ እንዳልሆነ ማውቁ አግባብ ስለሆን ኢትዮጵያዊያን በሁዋላ ከምታፍሩ ካሁኑ ለጠቁማችሁ እወዳለሁ። ከላይ በተገለጸው መሰረት በንክኪና በገንዘብ ሃይል፣ እንዲሁም በልዩ ፍላጎት እየተካሄደ ያለው ዘመቻ የኢትዮጵያን ህልውና የሚያናጋ ነው።

የአገሩ ድንበር ጠባቂ ሰራዊት የተጨፈጨፈበት መንግስት፣ ባልደረቦቹ ከጎኑ ሲታረዱ ያያ ሰራዊት ያካሄዱት ጦርነት የፍትህ መሰረቱና የእልሁ ገደብ ከፍተኛ በመሆኑ ከዚህም የዘለለ ጥፋት አለማድረሱ ሊያስመሰግነው በተገባ ነበር። የትህነግን አንጋፋ ባለስልታን እግር ሲያጥብ ያየነውን ወታደር ሸልመንና አድነቀን ችግሩን በስላም መፍታት ሲገባን ሌላ ሴራ ውስጥ መገባቱ በግል የሚያሳዝነኝ ጉዳይ ቢሆንም ዛሬ ነገሩ ከከንፈር መጠጣ የዘለለ ሆኗል።

ትህነግ ጦርነቱ ሲጀመር ባህር ዳርን በቅጽበት ሊቆጣጠር፣ ኦሮሚያ ላይ ኦነግ ሸኔን እያገዘ መንግስት ለመገልበጥ ወይም አብዛኛውን ኦሮሚያን ይዞ ሊደራደር ነበር። ኦሮሚያ በገነባው ሃይል እቅዱን አመከን። መከላከያ ከአማራ ልዩ ሃይልና ፋኖ፣ ሚሊሻ ጋር ሆኖ የሳሳውን ሃይሉን አጠናክሮ በአየርና በምድር ተቀናጅቶ ዘመናዊ ጥቃት በመፈጸም የትህነግን ሃይ አበራየ።

ትህነግ ጉድጓድ ውስጥ ትወለደ፣ መንግስት ሆነ፣ ዓለምን ዞረ። ከመንግስትነት ዝቅ ሲደረግ ክልል የሚባለው ኬክ አይመቸኝም ብሎ ትግራይ ገባ። ከትግራይ ወደ በረሃ አመራ። ከበረሃ ወደ ጉድጓዷ አቀና። የተወለደበት ጉድጓድ ውስጥ ተቀረቀረ። የቀረው አንድ ሃይ ቀድሞ የተከለው ምላስና ሚዲያ እንዲሁም ተከፋይ ምስለኔዎቹ ናቸው። አለቀ!! አምነስቲ አንዱ ምስለኔ ነው። በሪፖርቱ የዓለም አቀፉ የተባበሩት መንግስታት ገለልተኛ አጣሪ የቀረቡትን ግብአቶች አይቶ ፍርድ ይስጥ ብሏል። ፍርዱ እንደሚፈለገው ከሆነ ገና ስለ ጦርነት ሽታ ሳይኖር ” አብይ አሕመድ የጦር ወንጀለኛ ሆነው ሄግ ይቀርባሉ” በሚል በተደጋጋሚ ሲነገር ነበር። ጨውታው ይህ ነው።

ሳጠቃልለው

በትግራይ የተጎዱ ንጹሃን ሊኖሩ እንደሚችሉ እሙን ነው። መቼም ጦርነት ነውና። ትህነግም ሲቪሎችን አግቶና እነሱ ስር ሆኖ፣ ቤተ ክርስቲያንና መስጊድ ውስጥ ተድብቀው ወይም ተከልለው ውጊያ ያካሂዱ እንደነበር፣ ሰምተናል። በወጉ በጥንቃቄ መመርመር አለበት። ግን ግን ሰሞኑንን የአማራ ቴሌቪዥን የሚያቀርበው ዶክመንተሪ በሰብአዊ መብት ጥሰት ሊታይና ሊያስወንጅል አይችልም? እንዳየነውና እንደሰማነው ምን የቀረ ወንጀል አለ? እነ አምነስቲ አሻፈረኝ ካሉ ኦባንግ ሜቶ የሚመራው ድርጅት ምነው ተኛበት? አገር ቤት እንዲገቡ የተፈቀደላቸውን ሚዲያዎች እነዚህ አካባቢዎች ወስዶ ማሳየት የችግሩን ምንጭና ዋና ምክንያት ያመላክታልና ለነገ ባይባል። ከዚ ውጭ አምነስቲ ላይ ወገኖች ወደ ቀልቡ እንዲመለስ ነዝንዙ። ዝምታ ሃፍረትን ታከናንባለች!! አገርህ ላይ እየተበየነ ዝምታ!!

Exit mobile version