Site icon ETHIO12.COM

በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የሰሜን ምዕራብ ዞን የሽሬ እንዳስላሴ ምክትል አስተዳዳሪ ሙሉብርሃን ሀይለ ይናገራሉ፡-

👉ከትላንት ተምረን ነጋችንን ለማሳመር መደራጀት፣ መደማመጥና
መሥራት አለብን፣

👉ህወሓት በተፈጥሮው በድርድር በሽምግልና የማያምን፣ እስከ አሁን
የገጠሙትን ችግሮች በሙሉ በጉልበት እየፈታ የመጣ፤ አሁንም ይህ
አመሉ መጥቶበት የገጠመውን የመሸነፍ ስሜት በጉልበት ለመፍታት
ብሎ በሰሜን እዝ ላይ ያንን ጥቃት ፈጸመ፣

👉የተለያዩ ሴራዎችን በመሸረብ እንዲሁም የማያቋርጡ የፕሮፓጋንዳ
ሥራዎችን ሲሰራ ነበር፣

👉ማዕከላዊ መንግሥቱም ሕገ ወጥ በሕዝብ ያልተመረጠ እንደሆነ፤
ከዚህ ጎን ለጎንም እነሱ ያካሄዱትን ሕገ ወጥ ምርጫ ህጋዊ በማስመሰል
ዓላማቸውን ለማሳካት ከፍተኛ ጥረትም አድርገዋል፣

👉ይህም በትግራይ ክልል ላይ ከፍተኛ የሆነ ውድመት
አስከትሏል፣ሥርዓት አልበኝነትም ተፈጥሯል፣

👉በነገራችን ላይ ይህ የጁንታ ቡድን ህዝቡን በተለያየ ጫፍ ላይ ወስዶት
ስለነበር እውነታውን ማስረዳትም ከባድ ነበር፣

👉የሥልጣን እድሜያቸውን ለማራዘም እያደረጉ ያሉት ጦርነት ሆኖ ሳለ
ሕዝባዊ እንደሆነ የማስመሰል እንዲሁም ትግራይን ለማንበርከክና
በማንነቱ ለማጥፋት እንደሆነ አድርጎ በመናገር ሕዝቡን ለጦርነት
የመቀስቀስ ሥራም ተሰርቷል፣

👉የታሰሩ ሌቦችን ፈትቶ ሕዝቡን እንዲዘረፍ አድርጓል፤ እድሜያቸው
ትንሽ የሆኑና ወደ ሥራ ያልገቡ በየአካባቢው ያሉ ወጣቶችን
በየስታዲየሙ በመጥራት በሰሜን እዝ ውስጥ የነበረውን ትጥቅ ለወጣቱ
ነው ያስታጠቁት፣

👉ህገ መንግስትዊ ስርዓቱን በናዱ አካላት መካከል የሚደረግ ቢሆንም
የሕዝብ ለማስመሰል በከፍተኛ ሁኔታ ስራዎችን ሰርተዋል፣ በርካታ
ውድመቶች ደርሰዋል፤ የሰው ሕይወትም ጠፍቷል፣

👉በወቅቱ የሚመለከተውም የማይመለከተውም የሆቴል ጥበቃ ሳይቀር
መሳሪያ ስለታጠቀ ብቻ እገደላለሁ በሚል ስጋት ዘሎ ጫካ ነው የገባው፤
አብዛኛው አደረጃጀት፣ የመንግስት ተቋማት ዳኛ አቃቤ ሕግ የፖሊስ
ሠራዊት ሳይቀር በጠቅላላው ሁሉም ነገር ፈርሶ ነበር፣

👉ፓርቲው ሲጠፋ እነዚህ ተቋማት ሁሉ አብረው ነው የጠፉት፤ እነዚህን
አስተካክሎና እንደገና አዋቅሮ ለሕዝቡ አገልግሎት መስጠት በጣም
ፈታኝ ነው የነበረው፣

👉እዚህ ላይ ለሁለት ነገሮች ትኩረት ሰጥተን ነው የሰራነው፤ አንዱ
ሕዝቡ በረሃብ እንዳይሞት ማድረግ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በዞኑ
የተንሰራፋውን ሥርዓት አልበኝነት በቁጥጥር ስር ማዋል ነው፣

👉አሁን ላይ ግን ፖሊሶችም ዳኞችና አቃቤያነ ሕግም ደመወዝ
እየተከፈላቸው ሕዝባዊ አገልግሎታቸውን እንዲሰጡ ተነግሯቸዋል፤

👉በአጭር ጊዜ ውስጥም ወንጀል የሰሩ ሰዎች የሚያዙበትና ለፍርድ
የሚቀርቡበት ሁኔታም ይመቻቻል፣

👉የትግራይ ሕዝብ አንደኛ ጠላት ህወሓት ነው፤ አሁን ይህ ጠላት
ተወግዷል፤ በዚህ ደግሞ በግሌ ደስታ ይሰማኛል፤ የትግራይ ሕዝብም
ተጠቅሟል ነው የምለው፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ ግን ሕዝቡ ያለምንም
ኃጥያቱ የእነሱን አበሳ በመክፈሉ በጣም አዝናለሁ፣

👉የትግራይን ሕዝብ ላለፉት በርካታ አመታት አፍነውታል፤ በኑሮውም
ከሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች በባሰ ሁኔታ በድህነት የተሰቃየ ነው፤
ለሳምንት የሚያቆየው ቀለብ መያዝ የማይችል ሕዝብ አድርገውታል፣

👉በተቃራኒው ከወርቅ ጀምሮ ሌሎች አካባቢው ላይ የሚገኙ የከበሩ
ማዕድኖችን በህወሓት ሲዘረፍ፤ ጀግኖቹን ቢገብርም እንደ ሕዝብ
ተገፍቶ ሌቦች መካከል ገብተው ትግሉን ጠልፈው ለራሳቸው ጥቅም
አውለውታል፣

👉እያንዳንዱ የሚደረጉ ነገሮችን በእውቀትና በጥንቃቄ ከዘላቂ ሰላም
አንጻር ማየት፤ ከውሸት ፕሮፖጋንዳ መራቅ ያስፈልጋል፣

👉ከመላው ሕዝብም ይሁን ከጎረቤት አገሮች የሚያጋጨንን አካል
ማስወገዳችንን በማመን በአዲስ ምዕራፍ ወደፊት በመገስገስ በተለይም
ወጣቱ የራሱን ታሪካዊ ኃላፊነት መወጣት መቻል አለበት፣
👉በትግራይ ክልል የወደመው ንብረት የኢትዮጵያ ነው፤ የረገፈው
ሕይወት የእኛው ነው፤ በመሆኑም ባለመደማመጣችንና
ባለመግባባታችን የፈጠርነው ኪሳራ እንደሆነ በመረዳት አሁንም
በመልሶ ግንባታው ላይ የዳር ተመልካች ከመሆን ተላቀን መተባበር
ያስፈልጋል፤
በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የሰሜን ምዕራብ ዞን የሽሬ እንዳስላሴ ምክትል አስተዳዳሪ ሙሉብርሃን ሀይለ የትግራይን ወቅታዊ ሁኔታን በማስመልክት ያነሷቸውን ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/Ama/?p=4279

Exit mobile version