Site icon ETHIO12.COM

ማዕከላዊ ዕዝ ሙሉ በሙሉ መደምሰሱ፣ መከላከያ ሰራዊት ጻድቃንና ደብረጽዮን አሉበት ደጅ መድረሱ ተሰማ

የትህነግ ክንፍ የሆነውንና በውጭ አገር የሚንቀሳቀሰው ሃይል ከመንግስት ጋር ለመደራደርና በዋቅሻ ውስጥ ያሉትን አመራሮች ለማስለቀቅ በሚቀርባቸው ዲፕሎማቶችና ተከፋይ ወስዋሾች እንቅስቃሴ መጀመሩን በዘገብንበት ወቅት በቅርቡ መንግስት የዘመቻውን ሁለተኛ ክፍል ኦፕሬሽን እንደሚጀምር  በማርች ስምንት መረጃ አብረን መጠቆማችን ይታወሳል።

የዚሁ አካል ስለመሆኑ በውል ያልተነገረለት ጥቃት በደቡብ ትግራይ በደቡባዊ ትግራይ ኦፍላ ወረዳ አውሸራ በተባል ስፍራ  ከ80 በላይ የሚሆኑ የሕወሓት ታጣቂዎች  መደምሰሳቸው ተሰምቷል። የአካባቢው ነዋሪዎችም አረጋግጠዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በአንድ ቀን ልዩነት ” ማዕከላዊ እዝ” በሚል የሚጠራው የትህነግ ሰራዊት መመታቱ ተገልጿል።

በተደጋጋሚ ወታደራዊ መረጃዎችን በመጠቆም የሚታወቀው አርአያ ተስፋማሪያም የመረጃ ምንጮቹን ጠቅሶ  ” በማይጨው ቦራ በተባለ ቦታ የመከላከያ ሰራዊት በወሰደው የማጥቃት ዘመቻ ‘ማዕከላዊ እዝ’ ተብሎ የተሰየመውን የጁንታው ሀይል ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን ከመከላከያ ከፍተኛ የጦር አዛዦች የተገኘው መረጃ አረጋግጧል ” ሲል አስታውቋል።” ከተከዜ ሸሽቶ ወደ ተጠቀሰው ቦራ ተራራ የመጣው ይህ የጁንታ ሀይል ደብረፂዬን እና የቀድሞ ኢታማዦር ሹም ጄ/ል ፃድቃን ይመሩት እንደነበረ የጠቆሙት ምንጮቹ አያይዘውም ‘ማዕከላዊ እዝ’  ብለው የሰየሙት ሀይል ሙሉ በሙሉ ከተደመሰሰ በኃላ በዛሬው እለት ደብረፂዬን፣ ፃድቃንና ሌሎች የጁንታው መሪዎች የመሸጉበት ቦታ ደርሶ የመከላከያ ሰራዊታችን እንደከበባቸው አስታውቀዋል።

በዚህ ኦፕሬሽን የተከበቡት ጄኔራሎችና ሌሎች መሪዎች እጣ ፈንታ ብዙ ጊዜ ሳይወስድ እንደሚታወቅ ከፍተኛ የጦር አዛዦች ገልፀውልኛል” ሲልም ጨምሮ አስታውቋል።ይህ መረጃ በመንግስት አካላት በይፋ ባይገለጽም ኢትዮ12 ኦፕሬሽኑ እንደሚጀመር መረጃ ነበራት። በዚሁ መነሻ የቀደመውን መረጃ የሰጡንን ወገኖች ጠይቀን ” ዘመቻው የሚጠበቅ ነው።

የተለሳለሰ አቋም የነበራቸውን ለመያዝና የሚከፈለውን ዋጋ ለመቀነስ ሲባል፤ እንዲሁም የተበተነው ሃይል እንደ ቡጉንጀ አንድ ላይ ተሰባስቦ ለከበባ እንዲመች ሲሰራ ነበር” ሲሉ ዝርዝር መረጃ ለጊዜው እንዳልደረሳቸው  ተናግረዋል።ከትናንት ጀምሮ በትህነግ ሰራዊት ላይ ደረሰ ስለተባለው ጥቃት ከትህነግ የውጭ ክንፍም ሆነ አልፎ አልፎ ” ከበረሃ” ነው የሚባለው አካል እስካሁን ማስተባበያ አልሰጠም። ይልቁኑም የተባበሩት መንግስታት ትግራይ በቅርቡ እንደሚገባና ትግራይ ራስዋን እንድታስተዳድር ድጋፍ እንደሚሰጣቸው ደጋፊዎች አዲስ አበባ ሆነው በማህበራዊ ገጻቸው እያስታወቁ ነው።


Exit mobile version