Site icon ETHIO12.COM

ጀነራል ዮሐንስ ገ/መስቀል የሚዲያ ገበያ ሆነዋል፤ ኦፕሬሽኑ ቀጥሏል

በትግራይ የተቋቋመውን አስቸኳይ ጊዜ ግብረሃይል እንዲመሩ የተመደቡት ጀነራል ዮሐንስ ገ/መስቀል ጦረንቱን ” አጸያፊ ” በማለት ትግራይ ላመሩ ዲፕሎማቶች መናገራቸውን የነጮቹ ሚዲያዎች በቅብብል አራብተውታል። ኤፒ ጀነራሉ ይህንን ሲሉ ድምጽ ቀርጾ ማስቀመጡን እንደ አስረጂ በማስታወስ ዜናው መንግስትን የሚቃወም ሆኖ መሰራጨቱ ደግሞ በትህነግ ደጋፊዎች ዘንድ ሌላ ድል ሆኖ ተወስዷል። የባለስልጣኑ መረጃ ድል ሆኖ በሚዘገብበት በተመሳሳይ ሰዓት የህግ ማስከበሩ ዘመቻ አካል የሆነው የክፍል ሁለት ኦፕሬሽን ተጠናክሮ መቀጠሉ ተረጋግጧል;

This is a dirty war because it’s affecting everything. You don’t see fronts. The cost is immediately to those who are defenseless,” ባጭሩ መነጋገሪያ የሆነው ” አጸያፊ ጦርነት ነው። ምክንያቱም ሁሉንም ነገር ጎድቷል። ጦርነቱ በቀጥታ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉትን ዋጋ አስከፍሏቸዋል” ሲሉ ሰብአዊ ቀውሱን በማሳየት የተነገሩት ነው። ይህንኑ ዜና በስፋት የተቀባበሉት ” ጄነራሉ ካሁን በሁዋላ አይቀጥሉም፣ አብቅቶላቸዋል” ሲሉም አስተያየት እየሰጡ ነው።

እኚህ ጀነራል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኢንሳን ለማቋቋም ሃሳብ ባቀረቡበት ወቅት ” አይሆንም” በማለት የመከላከያ ደህንነት ስልጣናቸውን በመጠቀም የከለከሉ፣ ፍጹም የሆነ አቋም በመያዝ ኢንሳ እንዳይቋቋም በሩን የዘጉባቸው ነበሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ስልጣን ሲመጡ ግን በሱዳን የሰላም አስከባሪ ሆነው እንዲሾሙ አድርገዋቸዋል። ከዛም በፊት በተመሳሳይ እሳቸው ያልጠበቁትን ድጋፍ እንዳደረጉላቸው በቅርብ የሚያውቁ ይናገራሉ።

የህግ ማስከበሩን ዘመቻ በአደባባይ የደገፉና አግባብ መሆኑንን የመሰከሩት ጄነራል ዮሀንስ፣ አስገድዶ መድፈር ስለመፈጸሙ ከመስማት ውጭ ማስረጃ ማቅረብ እንደማይችሉ፣ “ግፍ ፈጽመዋል” በሚል የትኛውንም ወገን በስም እንዳልጠሩ ዘገባው ጠቁሟል። በጦርነት ሰላም የማምጣት እድል ጠባብ መሆኑንን ልምዳቸውን በማንሳት አመልክተው ሰላም እዲሰፍን የተኩስ ማቆምና ድርድር የመሳሰሉ አማራጮች ሊታዩ እንደሚገባ ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ ጄነራሉ በግል “በተለይ” ብለው ያቀረቡት አማራጭ ግን እንደሌለ ዘገባው ጠቅሷል። ” he did not put forward a specific proposal himself”

“I know very few and exceptional conflicts or violence — or fightings, let me say — that have ended only by gun. Very few,” said Yohannes, who formerly commanded UN peacekeeping forces in South Sudan. He said other “mechanisms” would need to be considered, potentially including negotiations and calls for a ceasefire, though he did not put forward a specific proposal himself.

” የትግራይ ተወላጅ” መሆናቸው እየተጠቀሰ ይህንን ማለታቸው ከመንግስት የተለየ አቋም እንደያዙ ተደርጎ ቢገለጽም ፣ይህ እስከታተመ ድረስ ከመደባቸው አካልም ሆነ ከለኤሎች የመንግስት ሃላፊዎች የተባለ ነገር የለም። ጦረነቱን ” አጸያፊ” ማለታቸውን ጠቅሰው እያደነቁዋቸው ያሉት ክፍሎች ከወራት በፊት ዳግም ወደ መከላከያ ሲመለሱ ” ባንዳ” ብለዋቸው እንደነበር ይታወሳል። በትግራይ ለተቋቋመውን አስቸኳይ ጊዜ ግብረሃይል መሪ ሆነው መመደባቸው ይፋ ሲደረግም በተከታታይ ሲዘለፉ መክረማቸው አይዘነጋም።

ይህ በእንዲህ eepa ትላንት ይፋ እንዳደረገው Northern, South-Eastern and Southern fronts. በሰሜን፣ ደቡብና ምስራቅ ጫፍ አካባቢዎች የመከላከያ ሰራዊት ጥቃት እየፈጸመ መሆኑንን አመልክቷል። ዘገባው የአንድ ወገን ሆኖ አስራ ሶስት ኦራል የኤርትራ ሰራዊት አባላት የተሳተፉበት እንደሆነ አክሎ ጠቅሷል። ይህ ተቀማጭነቱ ቢልጂየም የሆን ሪፖርት አቅራቢ ተቋም ስለ ደረሰ ጉዳት ያለው ነገር የለም።

በደቡባዊ ትግራይ ኦፍላ ወረዳ አውሸራ በተባል ስፍራ በትናንትናው እለትና ዛሬ ከ80 በላይ የሚሆኑ የሕወሓት ታጣቂዎች በመከላከያ ሰራዊት እና በአማራ ክልል ልዩ ሀይል ጥምረት መደምሰሳቸውን ተከትሎ የትህነግ ደጋፊ አክቲቪስቶች ” እልቂት እየተፈጸመ ነው” ሲሉ ድምጻቸውን ማሰማታቸውና የኤርትራ ሰራዊት ሃይሉን እያጓጓዘ መሆኑን በተለያዩ አውታሮች ሲያስተጋቡ ነበር።

ኢትዮ 13 ከሳምንት በፊት የትህነግ የውጭ ክንፍ ድርድር እንዲደረግ እየገፋ መሆኑንን በጠቆምንበት ዜና መንግስት ሁለተኛ የሚለውን ኦፕሬሽን ለመጀመር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ጠቁመን ነበር። የመረጃ ምንጮቹ እንደሚሉት አሁን የተጀመረው የሁለተኛው ዙር ኦፕሬሽን ውጤቱ በቅርቡ ይፋ ይሆናል። eepa ይህንን ተረድቶ ነው መስለ በዛሬው እለታዊ ሪፖርቱ ጄነራል ዮሐንስ ስለ ድርድር የተናገሩትን አጉልቶ አቅርቧል። ተኩስ ማቆም የሚል ሃሳብ መሰንዘራቸውንም በሪፖርቱ አካቷል። ሪፖርቱ በየቀኑ ለተመድ የሚቀርብ ነው።

አይሁድ መሆናቸው የሚነገርላቸው አዲሱ የአሜሪካ ይወጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድርድር አስፈላጊ መሆኑንን አንስተው በተደጋጋሚ መናገራቸውን ያነሱ አካሎች መንግስት በጫና ብዛት ወደ ንግግር ቢገባ እንኳን ነግግሩ የሚሆነው ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ሲሆን፣ ከዛ በፊት ግን አሁን ተጎርዶ የቀረውን ሃይል ለአንዴና ለመቸረሻ ጊዜ ማስወገድ ወይም መያዝ የአዲሱ ዘመቻ እቅድ ነው። በዚሁ ዘመቻ በማይጨው ቦራ በተባለ ቦታ የመከላከያ ሰራዊት በወሰደው የማጥቃት ዘመቻ ‘ማዕከላዊ እዝ’ ተብሎ የተሰየመውን የጁንታው ሀይል ሙሉ በሙሉ መደምሰሱና ጄነራል ሳድቃንና ዶ/ር ደብረጽዮን አሉበት የሚባለው ስፍራ ከበባ ውስጥ መውደቁ ተጠቁማያል።

የትግራይ ሚዲያ ሀውሰን እንዳለው የጀት ድብደባ ሲደረግ የትህነግ ሰራዊት አንዷን መቶ ጥሏል። ይህ ከገልለተኛ አካላት ማረጋገጫ ያልቀረበበት ዘመቻው ተጠናክሮ መካሄዱን አማለካች ነው። ማርቲን ፕላውትም በቲውተር ገጹ በተመሳሳይ እሮሮ እያሰማ ሲሆን፣ ዓለም ፕሬዚዳንት ኢሳያስን እንዲነሳባቸው ” የምስራቅ አፍሪቃ ስጋት” ሲል በተደጋጋሚ እየደበደባቸው ነው። በዘመቻ ኢሳያስ አፉውርቂን ግንባር ላይ አነጣጥው ዘመቻ የከፈቱት ሃይሎች የኤርትራ ሕዝብ ሁሉንም መረዳቱና አንድነቱን መጠበቁ አልተመቻቸውም።

Exit mobile version