ETHIO12.COM

“አማራ እና ኦሮሞን በካራ ሌላውን ብሄር በጥይት”

ምንም እንኳን ሰልፍ ባይወጣላችሁ፣ ፈረንጅ ባይጮህላችሁም ከሌሊት አውሬ የተረፈ አስክሬናችሁን አሞራ ሲራኮትበት፣ ደማችሁን ውሻ ሲልሰው አይቻለሁ እና መቼም ልረሳችሁ አልችልም። ሲል ይጀምራል እማኙ ወታደረ ዘርዩን ኑሪ አቦቴ።

“አማራ እና ኦሮሞን በካራ ሌላውን ብሄር በጥይት”

እንደ ወንጀለኛ የፊጥኝ ታስረው በጥይት ተደብድበው ተረሽነዋል። ለሀገሬው ነዋሪ ክብር እና ሉአላዊነት ልጅነታቸውን በቀበሮ ጉድጓድ በእንፉቅቅ ያሳለፉ ወንድሞቻችን ከመኖሪያ ቤቶቻቸው እያወጡ በልጆቻቸው ፊት ልብሳቸውን አስወልቀው በእንብርክክ ሀድጊ(አህያ)እያሉ ነድተዋቸዋል።

በሽራሮ በአደሀገራይ በመሳሰሉት ከተሞች የሰራዊቱ አባላት በድንጋይ ጭምር ተወግረው ተግድለዋል። ሴት የሰራዊቱ አባላት ጡታቸው ተቆርጧል በቡድን ተደፍረዋል። ሁለ ነገሩን ለህዝብ የሰጠው ወታደር ለውለታው የአፀፋ ምላሽ ካራ እና ጥይትም ሆኗል!! “አማራ እና ኦሮሞን በካራ ሌላውን ብሄር በጥይት” በሚል መፈክር ወታደር ከመሆናቸው ባለፈ ኦሮሞ እና አማራ በመሆናቸው ብቻ ታርደው አደባባይ ተጥለዋል።

ደማቸውን ውሻ ልሶታል።አስክሬናቸውን ሌሊት አውሬ ቀን አሞራ እያራኮተ ተሻምቶታል።በጦርነት እና በጥድፊያ ውስጥ ሆነንም ቢሆን በየበረሀው በየከተማው ወዳድቆ ከአሞራ ከአውሬ ከውሻው ከድመቱ ከዶሮ(ዶሮ አስክሬን ሲበላ ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት እዚ ነው!)የተረፈውን የጓዶቻችንን አፅም እንደ ነገሩ መሬት ጭረን አፈር ለማልበስ ሞክረናል።

ይህ የወታደር Zerihun Nuri Abote ሰሜን ዕዝ ላይ የተፈፀመውን ግፍ ከቦታው ሆኖ በአይኑ አይቶ የጻፈውና እንደወረደ የተቀዳ ነው። እዚህ ሸፍጥና ክህደት፣ እዚህ የግፍ ማማ ፣ እንዲህ ያለው የርኩሰት ጫፍ፣ እንዲህ ያለው የወንጀል ቁልል ተራራ ላይ ቆመው ነው እንግዲህ ” ፍትህ” እያሉ የሚያላዝኑት።

በዚህ ሁሉ ነብስን በሚያርድና ህሊናን በሚፈታተን ተግባራቸው ኮርተው ስለ ሰብአዊ መብት ይሞግታሉ። ከነዚሁ አብራክ የወጡ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ተሰግስገው ጥብቅና ሊቆሙ ይዳዳሉ። ከዚህ የአውሬ ቡድን የወጡ የሉሲፈር ሽንቶች ዓለም አቀፍ ተቋሞች ላይ በኢትዮጵያ ስም ተወትፈው እንዲህ ያለው በደል እንዲድበሰበስ የዘረፉትን ይረጫሉ። እነዚህ የሞራልና የህሊና መንፈስ የሌላቸው ድንጋይ ልቦች በዚህ ሁሉ ወንጀል ተተብትበው ሲያበቁ እኛን፣ ከካራቸው የተረፈውን ሰራዊታችንን እየከሰሱ ነው።

በእርም ሽንት ተፈጥሮ፣ በጭነገፈ ሽል ደረጃ ተወልዶ፣ የራሱንና የሰላማዊ ዜጎችን ደም እየጠጣ የኖረውና የፋፋው ትህነግ እዚህ የግፍ አረንቋ ውስጥ ለመግባት እንደ ሰው የሚያስቡትን አስቀድሞ ስጋቸውን በላ። አጥንታቸውን ከስክሶ ጠጣው። የሰውነት ሞራሉን በጠጣው ስፍር አልባ ደም አገልምቶ የትግራይ ምስኪን ወታቶችንና ሰላማዊ ህዝብ ክፋት ሲግት ኖረ። ከዚህ የገለማ ስብዕናው እየተጋሩ ያደጉትን ተጠቃሚዎች ይዞ የመርዝ አዝመራውን አስፋፋ። ህዝብ አጫረሰ። ነጹሃንን ገደል አስከተተ። አገሪቱን በጥላቻ አሳረራት። ህዝቡን አደህይቶ ለማኝ አደረገው። ዘርፈ። ሰብሰበ። አከማቸው። የሚጠግብና የሚሞላ ጉሮሮ ስለሌለው ” በቃህ ” ሲባል የሰበሰበውን እየረጨ መላው አገሪቱን አደማ። ተላልኪ አሰማርቶ ነብስ አስነጠቀ።

በሴራ ተሞክሮ አልሳካ ሲል የአገር መከላከያችንን ከላይ በተገለጸው መልኩ ወንጀልና ግፍ ፈጽሞ ዳግም ወደ ስልጣን ለመግስገስ ተነሳ። በመጨረሻም ያሰበው ሳይሆን ቀርቶ ተነነ። የእብሪት አምራቾቹ ዋጋቸውን አግኝተው የውሻ ሞት ሞቱ። የተቀሩትን በየስርቻው ተበተኑ። እንደ ፍልፈል ስራስር እየበሉ ቀናቸውን ጠባቂ ሆኑ። እላያቸው ላይ ከምድር በታች ስርቻ ውስጥ እየተጸዳዱ የቁም ሸተቱ። ሁሉን የሚያይ የፍትህ አምላክ ፈረደ!!

ከላይ በተገለጸው መሰረት ላይ ሆኜ አስተያየቴን ለመሳፍ ያስገድደኝ ትናት በዚሁ ሚዲያ ያየሁት የሰብአዊ መብት ተከራካሪ አቶ ፍስሃ ተክሌን ጠቅሶ የቀረበውን አስተያየት ለማተናከር ነው።

Exit mobile version