Site icon ETHIO12.COM

እነ ዶክተር አሸብር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ፤ ደራርቱ የተቃውሞ ሰልፍ አደረገች

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሪዜዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስና አብረዋቸው ምርጫ ሲያከናውኑ የነበሩ አመራሮች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ። የአዲስ አበባ ተባባሪያችን እንዳስታወቀው ኮማንደር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተቃውሞ ሲያሰሙ ነበር።

ትናትን የእውቅናና የሽልማት ሰነስርዓት የተደረገላት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሊቲክስ ፕሪዚዳንትና የኦሊምፒክ ኮሚቴ ምክትል ነች። ዛሬ ወሎ ሰፈር በሚገኘው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ድንኳን ተተክሎ ምርጫ በሚካሄድበት ውቅት ነበር ተቃውሞ የተጀመረው። በምርጫው የማራቶን ጀግናዋ ፋጡማ ሮባና ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ እንዲመረጡ ተደርጎ ነበር።

ምርጫው ለኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የአራት ዓመት ዘመን ይሁን ለመጪው የቶኮዮ ኦሊምፒክ በዙ ባይታወቅም፤ ምርጫው መካሄድ የለበትም የሚሉ ወገኖች ደራርቱን ጨመሮ ባሰሙት ተቃውሞ ፖሊስ ረብሻውን ተከትሎ እንደ ዶክተር አሸብርን ለጊዜው መውሰዱ ተመልክቷል። ይህ እስከታተመ ድረስ ስለመፈታታቸው አልተሰማም። ዶክተር አሸበር ፖሊስ ለጥያቄ እንደሚፈልጋቸው ጠቅሶ እነደወሰዳቸው መንገድ ላይ እያሉ ተናግረዋል። በመጨረሻ ባገኘነው ዜና ፖሊስ ቃላቸውን ተቀብሎ ለቋቸዋል።

የዶክተር አሸብርና የኮማንደር ደራርቱ ውዝግብ የቆየ ነው። በሁለቱ ውዝግብ ጉዳይ ጥርት ያለ ዘገባ ወይም ማስረጃ የሚያቀርብ ገልለተኛ ወገንም የለም። ደራቱ ተጽዕኖ ፈጣሪና ተወዳጅ መሆኗ፣ ዶክተር አሸብር ደግም እጃቸው ረዥም መሆኑ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሊያርፍ አልቻለም። በተባራሪ የሚወጡ የተልፈሰፈሱ ቃለ ምልልሶች ላይ ለመረዳት እንደተቻለው በደራቱ በኩል የግንዛቤ ችግር፣ በዶክተሩ በኩል በህግ ለመደበቅ በብልጠት የመሄድ አዝማሚያ ይታያል።

ህግ ማሻሻልም ሆነ መቀየር የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ መብት መሆኑንን ያለመቀበል ችግር አለ። በደፈናው የመቃወምም አባዜ አለ። ከሁሉም በላይ ኦሊምፒክ ከፈተኛ ጥቅም ያለበት ቦታ በመሆኑ ከጀርባ ሆነው የሚወሰውሱ አካላትም ጥቂት አይደሉም። በተመሳሳይ ዶክተር አሸብር ህግ እስከመቀየር ወይም ማሻሻል የሚሄዱበት ምክንያት ድብቅ አይደለም።

ዛሬ እንደተሰማው አትሌት ሃይሌና ብረሃኔ አደሬ ተመርጠዋል። በተለይ ሃይሌ ሳያውቀው ሊመረጥ አይችልም። ምንም እንኳን በሌለበት ቢመረጥም ስምምነቱ እንዳለው መረጃ አለ። ሃይሌ ህጉንም ስለሚያውቀው በስህትት ውስጥ ገብቶ የማይቻልና የማይነካ ጉዳይ ይነካል ብሎ ማስብ አይቻልም። ብርሃኔ አደሬ ከቀድሞ ጀምሮ የአትሌቲክስ ፌዴሪሽን በተደጋጋሚ የገፋት፣ ብራስልስ ትጥቅ ለብሳ ልትሮጥ ስትል እንድትወጣ የተደረገች፣ ይህ ሁሉ ሲሆን ደራርቱ በአትሌት ወኪልነት ከዱቤ ጁሎ ጋር የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ነበረች። በውቅቱ ዱቤም ሆነ ደራርቱ ይህንና ሌሎች በርካታ ያልተገቡ ወንጀሎች ሲፈጸሙ አለመቃወማቸው በአትሌቶች ዘንድ አድማ እስኬታ ድረስ ልዩነት ፈጥሮ ነበር። ዛሬ ዶክተር አሸብር ይህንን የቆየ ጉዳይ ተጠቅመው ይሁን በሌላ ለምርጫ የሄዱበት አካሄድ ጸብ አስነስቷል።

ሃዋሳ፣ ደበረዘይት፣ አዲስ አበባ ሆቴል የተከለከሉት እነ ዶክተር ድንኳን ጥለው ምርጫ ማካሄዳቸው እንደተሰማ እነ ደርቱና ተመሳሳይ ተቃውሞ ያላቸው ግቢው ውስጥ ስብሰባ እየተካሄደ ተቃውሞ አሰምተዋል። የሰላማዊ ሰልፍ ይዘት ያለው ጩኸት ነበር። ምርጫው ተጠናቆ ሲወጡ ፖሊስ ደርሷል። ብርሃኔ አደሬ ” እኔም ፖሊስ ነኝ” በሚል ከፖሊሶች ጋር መጋጨቷ ተስምቷል።

በመጨረሻ እንደታወቀው ደራርቱም ፖሊስ ዘነድ አብራ ቀርባ ቃሏን ሰጥታለች። ጉዳዩ ወደ ክስ ካመራ ኢትዮጵያን ከኦሊምፒክ የሚያሳግድ ስለሚሆን ጥንቃቄ እንደሚያሻው ባለሙያዎች ይመክራሉ። ቀደም ሲል አቶ አብነትና ዶክተር አሸብር በፈጠሩት አለመግባባት ሁለት ጎራ አሰልፈው አገር ስትደረፈርና መሳቂያ ስትሆን የታየው ዓይነት ጉዳይ እንዳይመጣ የሚሰጉ አሉ። ዶክተር አሸብር ዓለም ዓቀፍ አካሄዷን ስለሚያውቋት የሚወሰዱ እርምጃዎችና ጣልቃ ገብነቶች የተጠኑና ህጋዊ እንዲሆኑ ማድረግ ይበጃል። ዝርዝር ጉዳዩን እንመለስበታለን


Exit mobile version