አትለቲክስ ፌዴሬሽ በሙስና ተነክሯል፤ የ30 ሚሊዮን ብር ቼክ ተያዘበት- ባለሪኮርዱ አትሌት በውዝግብ ተመዘገበ

አትሌቲክስና ኦሊምፒክ ውስጥ ያለው ምዝበራ በውጤት እየተደገፈና ታዋቂ ህዝብ የሚያከብራቸውን አትሌቶች ተገን እያደረገ የሚፈጸም ነው። ከፊት ለፊት የሚታዩት “ህዝብ የሚያከብራቸው” የሚባሉትን ደፍሮ የሚናገር አለመኖሩ ደግሞ ቁማሩን፣ ሌበነቱንና ህገወጥነቱን ይበልጥ እንዲሰፋ አድርጎታል። ” ስመ ጥር” የሚባሉትን የነካ በደቦ የሚዲያ እሩምታ ስለሚወርድበት ዝምታን ይመርጣል። ቀደም ባሉት ዓመታት ኦሊምፒክ የዶላር መገበያያና መመንዘሪያ የግለሰቦች ሱቅ በደረቴ እንደነበር ያታወቃል። ለማስቆም ሲሞከር “ለምን አልዘርፍንም” በሚል ፍርድ ቤት ሄደው ሙግት የገቡም አይን አውጣዎችም አሉ። ወደ ዛሬው ሃሳብ እንለፍ።

ቼክና ክፍያው

ዛሬ የደረሰን መረጃ ማንኛውም አካል ሊያስተባብለው የማይችለው እውነት ነው። ሊመረመር የሚገባው ሃቅ ነው። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለመነሻ ተብሎ የቀረበ. ሌላ ተጨማሪ ክፍያ የሚቀርብበት የአትሌቶች የሆቴል ወጪ ለጊዜው ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲከፍል ጥያቄ ቀርቦለት ” አልፈርምም” ሲል ቼኩን ይዞታል።

ቀደም ሲል አትሌቶች ያረፉት በጥሩነሽ ዲባባና ስለሺ ስህን ሆቴል በቀን 17 ዶላር ሂሳብ ነበር። በኮቪድ ምክንያት አትሌቶች ከልምምድ ስለራቁ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ትዕዛዝ አስቀድመው ሆቴል የገቡት አትሌቶች ምንጩና በውል ባልታወቀ ምክንያት ወደ ኔክሰስ ሆቴል እንዲዛወሩ ተደርጓል።

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር /ትህነግ ከፈጠራቸው ልማታዊ ባለሃብቶች መካከል እንደሆኑ የሚነገርልቃቸው ትልቅ ሰው ከአቶ ዳዊት ላይ በ850 ሚሊዮን እንደገዙት የሚነገርለት ኔክሰስ ሆቴል በምን ዓይነት ጨረታ፣ ውልና የተለየ ድርድር አትሌቶቹን ለማሳደር እንደተስማማ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አያውቅም። አልተጠየቀም። በሃስብ ደረጃም አልተነገረውም። ነገር ግን ሆቴሉን በቅርብ ጊዜ የገዙት ወ/ሮ ትልቅ ሰው የአትሌቲክስ ፌዴሬሽ ስራ አስፈሳሚ ናቸው። ይህ ድንግዝግዝ ውል እሳቸው ሆቴሉን ከምግዛታቸው በፊት የተፈጸመ ቢሆንም፣ ከአቶ ዳዊት ላይ ሆቴሉን ለመግዛት ረዥም ጊዜ ግንኙነት ያደርጉና ይደራደሩ ስለነበር በአትሌቲክስ ስራ አስፈጻሚነታቸው አትሌቶቹ ከእነ ስለሺ ሆቴል እንዲወጡ እንደ ደራርቱን ከጸሃፊው ጋር ሆነው እንደተመዘዙ የሚናገሩ አሉ።

አትሌቶቹ በቀን በሰው 17 ዶላር ሂሳብእየተከፈለ ልምምዳቸውን ሲያደርጉበት ከነበረው ሆቴል፣ ለነጠላ 40፣ ለሁለት አልጋ 60 ዶላር እንዲከፈል ተደርጎ የተደረሰው ስምምነት ማን፣ እንዴትና ለምን እንዳደረገው አይታወቅም። ማብራሪያም አልቀረበበትም። ማብራሪያ ሲጠየቅ ወደ ሚቀርቧቸው ሚዲያዎች በመሮጥ ከጉዳዩ ጋር ያልተያያዘ ለቅሶ ለማሰማት መታቀዱን ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ ነግረውናል።

በኦሊምፒክ ወቅት አትሌቶችን ማዘጋጀትና ለኦሊምፒክ ኮሚቴ ማሳውቅ፣ ለኦሊምፒክ ኮሚቴ አሳውቆ ቴክኒክ ስራውን በጋር መስራት ከትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሚጠበቅ ቢሆንም፣ ፌዴሬሽኑ ከተሰጠው ማንዴት እላፊ ሄዶ ውል መፈጸሙ ከአሰራር አንጻር ህገወጥ ብቻ ሳይሆን የሚያስጠይቅ ነው። የፌዴሬሽኑ ሊቀመንበር ሻለቃ ደራርቱ ቱሉ ከመንግስት አሰራር ውጪ ይህ ውስኔ ማሳለፏ ያስጠይቃታል። ተጠቅመውባት ከሆነም ግልጽ ምላሽ ልትሰጥበት ይገባል።

ለዚህም ይመስላል ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከኔክሰስ ሆቴል የቀረበለትን ከሰላሳ ሚሊዮን ብር በላይ የመጀመሪያ ክፍያ ቼክ ” አልፈርምም” ብሎ ኦዲት እንዲደረግ የመራው። ” ኦዲት ካልተደረገ አንከፍልም” በሚል የቀረበው የክፍያ ጥያቄ ለጊዜው መያዙን ኢትዮ12 አጣርቷሎ። ወደፊት ዘርዝሩን እንመለስበታለን።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ወይም ሻለቃ ደራርቱ ቱሉ በዚህ ጉዳይ ላይ ግልጽ መመሪያ ቢሰጡ ይመረጣል። ወይም ለዝግጅት ክፍላችን ምላሽ ካላቸው ሊያደርሱን ይችላሉ።

የኔክሰስ ሆቴል ባለቤት ትልቅ ሰው የሚባሉት ወይዘሮ ጋር ስለ ጉዳዩ ለመጠየቅ ሞክረን አልተሳካልንም። እሳቸውም የሚሉት ካለ ዝግጅት ክፍሉን ማግኘት ይችላሉ።

Girma’s one-year journey from unknown runner to global medallist

ለሜቻ ዋጋ የለህም በተባለ በሳምንቱ ሪኮርድ ሰብሮ ሲያሸንፍ

ለሜቻ ግርማ የአንድ ዓመት ጉዞ ከጓዳ አውጥቶ ወደ ዓለም ዓቀፍ ታዋቂነት፣ ብሎም ሜዳሊስት የበቃ ተዓምረኛ አትሌት ስለመሆኑ የዎርልድ አትሌቲክስ ዘገባ ያረጋገጠለት የአርሲ ልጅ ነው።

ይህ ምርጥ አትሌት ጉዞውን በ2018 በ1500 ሜትር የኢትዮጵያ ሻምፒዮና አሃዱ አለ። ከዛም ተክለ ሰውነቱ ለ3000 ሜትር መሰናክል የሰጠ መሆኑንን የተረዱት አስልጣኙ ከፍያለው በሰጡት ምክር ወደ ተባለው እርቀት ተዛውሮ ልምምድ መስራት ጀመረ። በዓለም ሻምፒዮና የነሃስ ሜዳሊያ አገኘ።

ይህ ድንቅ ልጅ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ብቁ እንዳልሆነ አትሌቲክስ ፌዴረሽን ውስጥ ከነዱቤ ጋር የኖሩት፣ በግል የተወሰኑ አትሌቶች አጫዋችና አገልጋይ እንደሆኑ የሚታሙት ዶክተር አያሌው ወሰኑ። ሃኪም ናቸውና ” አይመጥንም ” ብለው መሰከሩበት። በእሳቸው ሙያዊ ውሳኔ ለሜቻ ከቶኪዮ ኦሊምፒክ ልዑካን መካከል ስሙ ተሰረዘ። ለሜቻን የሚያውቁ ሁሉ ጉዳዩ አሳዘናቸው። ነገሩ የገባቸው ሚዲያዎች ቢኖሩም ተሸበቡ።

ይህ በሆነ በሳምነቱ ለሜቻ ሞናኮ ሄዶ በ3000 መሰናክል አዲስ ክብረውሰን አስመዝግቦ ተመለሰ። የዶክተር አያሌውን ” ሙያዊ” ውሳኔ አፈር አስጋጠው። በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውስጥ እንደ ጉለተኛ እድሚያቸውን የፈጁት ዶክተር አያሌው በዚህ ውሳኔያቸው ሳያፍሩ ” አይመጥንም” ብለው ደረቁና ሃይለማርያም የሚባለው አትሌት እንዲያዝ ምክረ ሃሳብ ለገሱ። በውል ባልታወቀ ምክንያት ለሜቻ ” ዞር በል” ተባለ። ይህ ሲሆን ታዋቂ ነገር ግን አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገለላቸው ሯጮች ውሳኔው አግባብ እንዳልሆነ ቢናገሩም ደራርቱን ጨመሮ ሊሰሙ አልፈለጉም። ለምን? ይህም ምላሽ ያስፈልገዋል።

ከትናት በስቲያ ባገኘነው መረጃ መሰረት በመጨረሻ የአትሌቶች ስም ማስተላለፊያ ቀን ስሙ የተዘለለው ለሜቻ በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና አኖካና ድጋፍ በከፍተኛ ውዝግብና ምልጃ ከዋናው የባህር መዘገብ ላይ ስሙ ስለሚገኝ በተወዳዳሪነት እንዲያዝ ተደርጓል።

ይህ አትሌት ተገፍቶ፣ አትችልም ተብሎ፣ እንደ ባጣ ቆዩኝ እንዲወዳደር ተደርጎ ውጤት ቢበላሽበት ተጠያቂው ማን ነው? ስማቸውን እንዳንጠስ የተየቁን አሰልጣኞች ” በሚሆነው ሁሉ የምናውቀ ነገር የለም። ጉዳዩ ሆድ ይፈጀው ነው። ከውድድሩ መልስ ማንም ሆነ ምን ውጤቱ መንግስት ዘነድ እንቀርባለን” ብለዋል።

አትሌት ደራርቱ ቱሉን ሽፋን አድርገው ወይም አውቃ ሊሆን ይችላል እነ አቶ ቢልልኝ በርካታ ህገወጥ ተግባር እየፈጸሙ እንደሆነ መረጃ አለ። የፌዴሬሽን ቅጥር ሰራተኛ ሊይዘው የማይገባ የአማተር ሃላፊነት ውስጥ ገብተው ተነክረዋል። ይህ ደራርቱ እያወቀች የሆነ ጉዳይ ነው። አቶ ቢልልኝ ተቀጣሪ የአትሌቲክስ ጽሐፊ ሆነው ሳለ ብመን መስፈርት በአማማተር የሚሰራ ስራ ውስጥ ገቡ? እሳቸው የዳርት ፌዴሬሽን ሊቀመንበር ሲሆኑ የዛሬው ሚኒስትር ” የተከበሩ” ዱቤ ጅሎ እንዴት እውቅና ሰጡ? መመሪያውን ሰማያውቁ? ወይስ እንዴት?

በሌላ ፌዴሬሽን ” አማተር ነኝ” ብሎ መሪ የሆነ ሰው ሻለቃ ደራርቱ ደሞዝ እየከፈለች የምታሰራው ለምንድን ነው? ሻለቃ ደራርቱ ይህን ህግ የመጣስ ስልጣን ከየት አገነች? ወይስ ጮሌዎቹ አሞኟት? ምንም ይሁን ምን ግን ይህ ሊያስወቅሳት እንደሚገባ በርካቶች ይስማማሉ። ሚዲያውም ከተራ ስድብና ውዳሴ ወጥቶ ደንብና መመሪያ በማጣቀስ እዚህ ጉዳይ ላይ ሊሞግት እንደሚገባ አስተያየት እየተሰጠ ነው። በኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ቡድን የመክፈቻ ሰነ ስርዓት ላይ ምን እንደሆነ ዝናና ስም ሳይፈራ ማጣራት እንዲደረግ እዛው ያሉ ጠቁመዋል። መመሳቀሉ የተፈጠረው ጭቃ ለመቀባባት ሆን ተብሎ የተሰራ ስለመሆኑ መረጃ ቢኖርም ጉዳዩን በስፍራው ላሉ ጋዜጠኞች መተውን መርጠናል።

በሌላ የአትሌቶች ዜና የመጨረሻ የምርጫ ውድድር ሄንግሎ ውጤት ላይ እንዲመሰረት ከተባለ በሁዋላ ገንዘቤ ዲባባ ” ኮቪድ ይዟታል” በሚል የሃሰት ሪፖርት ለብቻዋ ተወዳድራ ሰዓት እንድታሟላ የተኬደበት አግባ በራሱ ህግን የጣሰ መሆኑ ተጠቅሶ ምላሽ እንዲቀርበበት ሊጠየቅ እንደሚገባ ታዛቢዎች ነግረውናል። ውጤቱ ላይ ጫና ላለማሳደር ቀጣዩን እንመለስበታለን። ሁሉንም እያነሱ ዶክተር አሸብር ላይ መለጠፉ ብቻውን አያዋጣም። እሳቸው ሊጠየቁ በሚገባቸው ጉዳዮች ብቻ መጠየቅ አለባቸው። ከዚህ ውጭ በደቦ ሁሉንም ጉዳይ ወደ አንድ ሰው በመግፋት ወንጀል ውስጥ መደበቅ ሊፈቀድ አይገባም።መፍትሄ አይሆንም።

ደራርቱ ምርጥ የኢትዮጵያ ጀግና ናት። ደራርቱ ብቻ ሳትሆን ብዙ የማይረሱ የስፖርት ጀግኖች አሉ። መለኪያው ሪኮርድ፣ ብዙ ማሸነፍ፣ የሜዳሊያ ብዛት … ነውና ኢትዮጵያን ያኮሩ፣ ለአሸናፊዎች ድጋፍ የሰጡ፣ ያቅማቸውን የሞከሩ፣ ባይሳካም እንደ ችሎታቸው የተሳተፉ ሁሉ በየደረጃው ጀግኖች ናቸው። ጀግና መሆን ግን ማንንም ከምንም በላይ ሊያደርግ አይገባም። ደራርቱ አበጀሽ ተብላ የምትሸለመውን ያህል ልትጠየቅም ይገባል። በነገራችን ላይ የደራርቱ ሽልማት በራሱ ትልቅ አነጋጋሪና ጤነኛ ያልሆኑ ገጽታዎች ያሉት እንደሆነ ዝግጅት ክፍላችን ያምናል። ጀግናዋ ደራርቱ በባርሴሎና እንደ ዋላ ተንሳፋ ያስመዘገበችው ድል የሚረሳ አይደለም። ከእኛ አልፎ የአፍሪካም ነው። ሃይሌስ? ቀነኒሳስ? ፋጡማስ? ጌጤስ? መሰረት ደፋርስ? ጥሩነሻስ? ብረሃኔስ? …. መስፈርቱ ምንድን ነው?፡ወደፌት ይህንንም በዳታና በመረጃ እናየዋለን። ችግሩ ሚዲያው ረጋ ብሎ አለመመርመሩ ነው። ሚዲያው ዝም ብሎ ማመኑና በአመክንዮ ላይ ተመስርቶ አለምስራቱ ነው።


Donate Button with Credit Cards
 • አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአጎዋ የምታስወጣ ከሆነ 200 ሺ የሚጠጉ ሴቶች ከሥራ ውጪ ይሆናሉ
  አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአጎዋ የምታስወጣ ከሆነ በፋብሪካዎች ተቀጥረው የሚሠሩ 200 ሺ የሚጠጉ ወጣት ሴቶችና እናቶችን ከሥራ ውጪ ይሆናሉ ሲሉ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ገለጹ፡፡ የምጣኔ ሀብቱ ባለሙያ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በአሁኑ ጊዜ አሜሪካ ለአፍሪካ አገራት ከሰጠችው ከቀረጥ ነፃ ንግድ ማበረታቻ ዕድል (አጎዋ) ተጠቅመው በአሜሪካ ገበያ ምርታቸውን በሚያቀርቡ ፋብሪካዎችContinue Reading
 • አሜሪካ በትህነግ ላይ ቃታ ሳበች፤ የዜጎች ርብርብ ውጤት አስገኘ
  የጦርነቱ መነሻ ምክንያት የሰሜን ዕዝ ላይ ትህነግ በፈጸመ ጥቃት ሳቢያ መሆኑ ትህነግ ከኦነግ ሸኔ ጋር የፈጠረርውን ጥምረት የለቅድመ ሁኔታ እንዲያፈርስ ህጻናትን ለውትድርና መጠቀምን እንዲያቆም በወረራ ከያዛቸው የአማራ አካባቢዎች ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ለቆ እንዲወጣ በ H.Res.445 አዋጅ በአሜሪካ ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ጉዳይ ውሳኔ አሳልፏል። የውሳኔው መግለጫContinue Reading
 • ኦፌኮ ብሔራዊ ውይይቱ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪና ሸኔ እንዲካተቱበት ጠየቀ
  የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ በቅርቡ ይካሄዳል የተባለው የብሄራዊ ውይይት የታጠቁ ሃይሎች ሙሉ በሙሉ እንዲካተቱበት ሲል ጠየቀ። ወንጀል የሰሩና በከፍተኛ ደረጃ የመከላከያ ሰራዊትን ያሳረዱ፣ ሰላማዊ ዜጎች እንዲፈናቅሉና በጅምላ እንዲጨፈጨፉ፣ መጤ ተብለው እንዲሰደዱ አድርገዋል፣ አዘዋል፣ አመራር ሰጥተዋል በሚል ህግ ይጠይቃቸዋል የተባሉትን አስመልክቶ መግለጫው ስምና ድርጅት ጠቅሶ አልጠየቀም። ሙሉ መግለጫውን ያንብቡ የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲContinue Reading
 • የትግራይ ነጻ አውጪ ኩታበር ገባሁ አለ፤ መንግስት ሙትና ቁስለኛ ሆኖ መበተኑና የተቀረውም እየታደነ መሆኑን ገለጸ
  ፎቶ የትግራይ ሃይሎች በወረሯቸው አካባቢዎች የደረሰ ዕህል በደቦ ሲያጭዱ የሚያሳይ፣ ምንጭ የደሴ ወጣቶች መቀለ የሚገኘው የጀርመን ድምጽ ዘጋቢ ትህነግ በሰጠው መግለጫ ኩታበርን መቆጣጠሩን እንደዘገበለት በመጥቀስ በፌስ ቡክ ገጹ አስፍሯል። የጀርመን ድምጽ የኢትዮጵያን መንግስት ዘገባ ለምን እንዳካተተ አላስታወቀም። ይሁን እንጂ መንግስት ማምሻውን ባሰራጨው መግለጫ በወሎ ግንባር በወረባቦ፣ በተሁለደሬ፣ ኩታበርና ደላንታ በወሰዱትContinue Reading
 • ቀንና ታሪክን ታካ ቻይና በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጣላቃ ግብነት ተቃወመች
   ቻይና የአለምአቀፍ ድንጋጌዎች ጠበቃ፤ ዓለም አቀፍ ፍትሃዊነትን እና ፍትህን በማስጠበቅ ረገድ ቁልፍ ሚና ተጫውታለች ሲሉ ፕሬዚደንት ሺ ዢንፒንግ ገለጹ፡፡ቤጂንግ በተባበሩት መንግስታት የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ሕጋዊ መቀመጫ የተመለሰችበትን 50ኛ ዓመት አከበረች፡፡ በመርሃግብሩ የቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግን ጨምሮ÷ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፣ የዲፕሎማቲክ መልዕክተኞች እና በቻይና የሚገኙ የአለም አቀፍContinue Reading

Leave a Reply