Site icon ETHIO12.COM

ፌስቡክ የኢትዮጵያ ምርጫን ተከትሎ የተሳሳተ መረጃ በሚያሰራጩ ደንበኞቹ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ

ፌስቡክ የኢትዮጵያ ምርጫን ተከትሎ መራጮች ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኙ የሚያስችል ሁኔታ ለማመቻቸት እና ገፁን የተሳሳተ መረጃ ለመልቀቅ የሚጠቀሙበት ደንበኞቹ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ከተሳሳተ መረጃ የሚጠበቁበት እና ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ የሚያስችል የማህበረሰብ ማነቃቅያ ዘመቻን እንደሚያካሂድም ባወጣው ፅሁፍ አትቷል።ከሚመለከታቸው አካለት ጋር በጋራ ለመስራት በሚችልባቸው ሁኔዎች ላይ እየሰራ መሆኑንም ባወጣው ፅሁፍ ላይ ጠቅሷል።

ድርጅቱ የህዝቡን ደሀንነት ለማስጠበቅ ሲባል ገፁ ላይ የጥላቻ ንግግር፣ ብጥብጥን የሚቀሰቅስ፣ ዘርን እና ፆተን ያተኮረ ጥቃት በሚፈፅሙ አካላት ላይ እርምጃ ለመውሰድ መወሰኑን የገለፀም ሲሆን ጥቃት የደረሰባቸው ኢትዮጵያውያንም የፌሰቡክ ህግ ተጥሶ ሲመለከቱ በተቀመጠላቸው የመጠቆሚያ መንገድ ተጠቅመው ሪፖርት እነዲያደርጉ ጠይቋል።

የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚከታተል እና የአማርኛ፤ ኦሮምኛ፤ ትግረኛ እና ሶማለኛ ተናጋሪዎች የተካተቱበት ቡድን ማዋቀሩን የገለፀው ፌስቡክ፣ ሓሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎችን ለመለየት እሰራለው ብሏል።ጥቃትን ለማስቀረት ፈጣን መረጃ ማጣራት ላይ የሚሰራው ፌስቡክ መረጃን ማጣራት ላይ ከሚሰሩ እንደ AFP ያሉ ሌሎች ድርጅቶችም ጋር እንደሚሰራ ገልጿል።

ኢትዮጵያውያን እውነተኛ መረጃ ማጣራት የሚያስችላቸውን የሚዲያ እና የዲጅታል እውቀት ለማሳደግ የሚያስችል ዘመቻ እንደሚያካሂድም አመልክቷል። ይህን ማሳካት የሚያስችለውን የቢልቦርድ ማስታወቂያ በአዲስ አበባ 43 ቦታዎች ላይ ከፈረንጆቹ ታህሳስ 2020 ጀምሮ እያስኬደ መሆኑን ገልጿል። ለጥላቻ ንግግር ትዕግስት የለኝም ያለው ድርጅቱ ይህን ለመዋጋትም በቴክኖሎጂ እና የሚከታተል ቡድን ላይ ከፍተኛ ገንዘብ መድቦ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

የፖለቲካ ውይይቶች አና ክርክሮች በግልፀኝነት መካሄዳቸውን የሚረጋገጥበት አካሄድ በገጹ ማካተቱን የሚገልጸው ድርጅቱ ከመጋቢት ጀምሮም የፖለቲካ ፓርቲዎች ራሳቸውን ማስተዋወቅ የሚችሉ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን በኢትዮጵያ እንደሚኖሩ እና ማን እንደሆኑ መለያ ፎርምን ሞልተው ገፁን መጠቀም እንደሚችሉ በፅሁፉ ማተቱን ፋና ዘግቧል።


Exit mobile version