ETHIO12.COM

የቡድን 7 አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች የኤርትራ ወታደሮች በፍጥነት እንዲወጡ ጥሪና የመንግስት መግለጫ

በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁሉን አሳታፊ የፖለቲካ ሥርዓት በአገሪቱ መፈጠር እንዳለበትም የቡድን ሰባት አሳስበዋል።  ትግራይን ጨምሮ በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ተቀባይነት የሚኖረው ሁሉን አሳታፊ የፖለቲካ ሥርዓት በመፍጠር፣ ተዓማኒነት የሚኖረው ምርጫ ማካሄድና በቀጣይ ብሔራዊ ዕርቅ የሚደረግበት ሥርዓት ማመቻቸት እንደሚገባ …..

. የጊዜያዊ መስተዳድሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉ ነጋ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ለመውጣት « ሂደት የሚጠይቅ እና በፍጥነት ላይከናወን የሚችል »

. ያወጡት መግለጫ መንግስት በክልሉ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትንና መሬት ላይ ያለውን እውነታ በትክክል ያላገናዘበ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በኢኮኖሚ የበለጸጉት የቡድን 7 አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል «በፍጥነት ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ እና በተረጋገጠ መልኩ» ለቆ እንዲወጣ ጥሪ አቀረቡ።

ከትግራይ ክልል የሚወጡ የመብት ጥሰት ሪፖርቶች «እጅጉን ያሳስበናል»ም ብለዋል። በኢትዮጵያ እየታዩ ያሉ ግጭቶች ማብቂያ እንዲያገኙ እና የትግራይ ክልልን ጨምሮ ሁሉን አሳታፊ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመርም ሚንስትሮቹ ጠይቀዋል።

ሂደቱ በመላ ሀገሪቱ ብሔራዊ እርቅ እንዲሰፍን እና በሁሉ ዘንድ ተአማኒነት ያለው ምርጫ እንዲካሄድ መንገድ የሚጠርግ መሆን አለበትም ብሏል። የናይትድስቴትስ እና ብሪታንያን ጨምሮ የአውሮጳ ህብረት አባል ሃገራት ያሉበት የቡድን 7 አባል ሃገራት ትናንት ዓርብ በበርሊን ባወጡት መግለጫቸው በቅርቡ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የኤርትራ ወታደሮች ትግራይን ለቀው እንደሚወጡ ማስታወቃቸውን በበጎ እንደተቀበለው አስታውቋል።

ነገር ግን ትግራይን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው የጊዜያዊ መስተዳድሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉ ነጋ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ለመውጣት « ሂደት የሚጠይቅ እና በፍጥነት ላይከናወን የሚችል » ነው ሲሉ ለፈረንሳይ ዜና ምንጭ AFP ተናግረዋል። ነገርግን የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮቹ በመግለጫቸው እንዳመለከቱት በትግራይ ክልል ግጭት ተሳትፎ ያላቸው “ሁሉም ወገኖች በኃይሎቻቸው ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር ማድረግ ፣ የዜጎችን ደህንነት ማረጋገጥ እና የሰብአዊ መብቶችን እና ዓለም አቀፍ ህጎችን ማክበር አለባቸው” ብለዋል DW.

የትግራይ ክልልን አስመልክቶ የቡድን ሰባት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ያወጡት መግለጫ መንግስት በክልሉ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትንና መሬት ላይ ያለውን እውነታ በትክክል ያላገናዘበ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ መንግስት በክልሉ የተከሰተውን ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ በርካታ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ባወጣው መግለጫ አመላክቷል፡፡በሌላ በኩል የኤርትራ ወታደር ከድንበር አከባቢ ለቆ መውጣት መጀመሩንና የአትዮጵያ መከላከያ ኃይል መረከቡን በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

Exit mobile version