Site icon ETHIO12.COM

ሱሃይር መታለች – ለካይሮው መንግስት መርዝ፣ ለሱዳን መንግስት ጭንቀት፣ ለሀበሾቹ ብርታት

ፁሁፏ ከመለቀቁ የተነሳ የአረብ ሶሻል ሚዲያዎች አንድ መቶ ሰማንያ ዲግሪ ተለውጠዋል!
.
ፕሬዝዳንት ሲሲ ሱዳን ለጉብኝት ሊመጣ መሆኑን ከሰማችበት ቀን ጀምራ
የፀረ አይሲሲ መንግስት ተቃውሞ ጠርታ የሱዳንን ከተሞች በተቃውሞ አጨናንቃለች
ሲሲ እንደ ብርቱካን በካርቶን የመጣ እስኪመስል ድረስ ተሸማቆ ምሳ እበላበት ቤተመንግሥት እራቱን እንዳይደግም አድርጋለች (ብዕረኛዋ ሱሀር )

ከዛን ግዜ ጀምራ ድምጿ ጠፍቶ ነበር። ምንም ነገር ፅፋና ተናግራም አታውቅም።
የትናቱን የኮንጎ የግብፅ ሱዳን ኢትዮጵያ የድርድሩን አጠቃላይ ይዘት ከሰማች ቡሀላ
እንደሚሳኤል የሚወነጨፈውን ሀሳቧን ከዋና ከተማ ካርቱም ዳርቻ ላይ ለካይሮው መንግስት መርዝ፣ ለሱዳን መንግስት ጭንቀት፣ ለሀበሾቹ ብርታትን የሚጨምር ፁሁፍ አሶንጭፋለች

በጠንካራ መጣጥፎቿና በግድቡ ዙሪያ ያለማቋረጥ እውነታዎችን ስለምትፅፍ ወደ ግብፅ እንዳትገባ፣ በግብፅ መንግስት ታግዳለች !
.

ውድ አንባቢያን በዚህ ፅሁፍ ውስጥ የማጠቃልለው በከፍተኛ ፀፀት በመረጃና በማስረጃ የተረጋገጡ እውነታዎች ሲሆኑ
ማንኛውም የፍትህ ባለስልጣን ፊት ለፊት ለመጠየቅ ዝግጁ ነኝ ፡፡

ከዓመት በፊት የመስኖ ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ያሲር አባስ በሚኒስቴሩ የተመራ
በአባይ ውሃ ጉዳይ በተካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስብሰባ ላይ እንደ ጋዜጠኛ ተገኝቼ ነበር።

የስብሰባው ርዕስ የህዳሴ ግድብና የሱዳን አቋምና የግድቡ ጥቅምና ጉዳት የሚል ነበር። እኔም በግድቡ ዙሪያ የሚደረጉ ውይይቶችን ለመታዘብ እንደ አንድ ጋዜጠኛና ተደራዳሪ ታባቢ አብሬ ተቀምጫለሁ ።

በዎቀቱ የተነሱ ሀሳቦች ግድቡ የሚሰጠው የመሰረተ ልማትና የግድቡ አሰራር ጥንካሬው ምን ያህል እንደሆነ ፣
ግድቡ የሚሰራበት ጉባ ተራራ ምን ያህል ጠንካራ የመሬት አቀማመጥ አለው በሚልና በመሰል ጉዳዩች ላይ ጥያቄ ተንስቶ ከመስኖ ሚኒስቴሩ ያሲር አባስ በኩል ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥቶናል ፡
.
ሚኒስትር ያሲር አባስ ቃል በቃል የተናገሩት ግድቡ ለሱዳን የሚሰጠው ጥቅም ስፍር ቁጥር የሌለ ከኢትዮጵያ ይልቅ ሱዳን እጅግ ተጠቃሚ እንደሆነች ነው።

የግድቡን አሰራር በተመከለተ ግድቡ አሁን ከሚሰሩ ዘመናዊ ግድቦች የበለጠ በጠንካራ መሀንዲሶች የተሰራ ምንም ዓይነት የቴክኒክ ችግር እንደሌለ ነው የነገሩን። በግድቡ ዙሪያ የቀረው

ኢትዮጵያ በውሀ አለቃቅና ቀጣይ ሱዳን በወንዙ ላይ የምሰራቸውን ፕሮጀክትን በተመከለ ውይይት ተደርጎ ህጋዊ ፊርማ መፈራረም ብቻ ነው የቀረን ብለው ነው የነገሩን።

ከኔጋር አብሮ የነበረው የአል-ሱዳኒ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ “.አጣፍ መሐመድ ሙካር ” በግድቡ ዙሪያ እጅግ ወሳኝ የሆነኑ ጥያቄዎችን ለሚኒስትር አባስ ያሲር አቅርቦ ነበር።

ሚኒስቴር ያሲር የግብፅን አቋም በተመለከተ ጥያቄ ቀርቦለት፣ ቃል በቃል የተናገረው ግብፅ የኢትዮጵያ ግድብ ሳይሆን የሱዳንን ጥቅም ነው እየተቃወመች ያለችው አሉ። ይሄንን ያሉት እፊቴ ቁጭ ብለው ነው !
.
ከአመት በፊት ይሄንን ሀቅ የመሰከሩ የውሀ
ሚኒስትሩ ዛሬ ላይ አቋማቸውን ቀይረው የግብፅን እስትንፋስ እያስጋቡ ነው።

የተከበረው የሱዳን ህዝብ ይሄንን አቋማቸውን ለምን እንደቀየሩ በውል የሚረዳ አልመሰላቸውም። ይመስለኛል ከሱ ውጭ ሌላው 35 ሚሊየን የሱዳን ህዝብ ያልተማረ ደንቆር አድርጎ ነው የሳላቸው።
.
ግብፅ ከአመት በፊት ሱዳንን ትታ ከአዲስ አበባ ጋር እንደራደር ብላ 11 ጊዜ ጥያቄ ያቀረበች አገር ናት። ይሄንን ጥያቄ ያቀረበችው ሱዳን በውሃው ላይ ምንም ነገር የማድረግ መብት የላትም ብላ ሳይሆን ንቄት ስላለባት ነው። አዲስ አበባ ግን ድርድሩ ያለሱዳን መካሄድ አይችልም ሱዳንም ይመለከታታል ብላ ነው የመለሰችላት።
.
ይሄንን ሁሉ እውነት ሸምጥው የሱዳን ባለስልጣናት ዛሬ ላይ ኢትዮጵያን ለማስፈራራት በየድርድሩ ላይ የግብፀን ሻንጣ ተሸክመው ሲሮጡ እያየናቸው ነው።

ሁለቱ አገራት ከተመሳሳይ አቋም እስከ የጋራ ጦር እስከመመስረት ደረጃ ደርሰዋል። አንደውም ሁለት ግዜ የናይል
ንስር በሚል ስም የጦር ልምምድ አድርገዋል።

አሁን ባለው ሁኔታ ይሄንን ሁሉ የሚያደርጉት
ቀጣይ የሱዳን ጥቅም ከኢትዮጵያ ይልቅ ወደ ግብፅ አዙረውታል። በጭንቅላታቸው ላይ የተሳለው የግብፅ ጥቅም እንጅ የሱዳን ተጠቃሚነት አይደለም።
እውነታው ግን ከግብፅ ጋር የሚደረግ ወዳጅነት” በግብፅ ከመታለል ውጪ ለሱዳን አንድም ጥቅም የለውም። ኢትዮጵያ አንቢ ባትል ኖሮ የኛ መሪዎች
የሱዳን ህዝብ በወንዙ ላይ ባይተዋር ሆኖ
የግብፅ ዘበኛ የሚያደርገውን ስምምነት ለመፈረም ጫፍ ደረሰዋል። እነዚህ ሰዎች የእውቀትም የሞራልም እጥረት ችጋር ይዟለዋል። የሱዳን ህዝብ ከአሁኑ የነዚህ ሰዎች አቋም አይቶ ካልተቃወመ በነዚህ ሰዎች ምክኒያት የናይል ተጠቀሚ ሳንሆን
እንደኖርነው « ሺ » ዘመን ሁሉ አሁንም
ሌላ ሺ ዘመን ዘበኛ ሊያደርጉን እጫፍ ደርሰዋል !

ሱሌማን አብደላ

Exit mobile version