ETHIO12.COM

የትህነግ “ውሮ ወሸባዬ” – የመንግስት ሩጫ – የሃላኑ የኢትዮጵያን ቋንጃ የመበጠስ የእባብ አካሄድና ባንዳዎች!

foto – የአገር መከላከያ ሰራዊት ከታገተ በሁዋላ ባዶ እግሩን ሆኖ ” ሃድጊ” እየተባለ እየተሰደበ በከትመ ሲሄድ ከሚያሳየው ቪዲዮ የተወሰደ

ሰሞኑንን አዳዲስ ጉዳዮች እንደሚሰሙና አሁን ያለንበት የግንቦት መባቻ የቀጣይዋ ኢትዮጵያ እድል የሚለካበት ስለመሆኑ በርካታ መረጃዎችና ምልክቶች እየታዩ ነው። እንደ እባብ በለስላሳ ቆዳቸው የሚሳቡት ሃያላኖቹ በሚቀልቧቸው የሚዲያ ሰራተኞች በኩል መርዛቸውን እየተፉ ነው። መንግስት ሰሞኑንን ከ”ጁንታነት” አውርዶ ” የስንዴ ሌባ” ያለው ቡድን ” የድል አድርጊያለሁ” ዜማና መንግስት ዙሩን ማክረሩ በቅርቡ አዲስ ነገር እንደሚሆን ማሳያዎች ናቸው።

የትህነግ ወይም መንግስት ” የስንዴ ሌባ” የሚለው ስብስብ ውሮ ወሸባዬ 

ተቀማጭነቱ ብራሰልስ የሆነው ICG የሚባለው የዓለም አቀፉ የግጭት ተንታኝ ቡድን በትግራይ የተጀመረው የህግ ማስከበር ዘመቻ በቅርቡ ያበቃል የሚል እምነት እንደሌለው ይፋ አድርጓል።  ተቋሙ ባለፈው ዓርብ በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ስላለው ወቅታዊ  ሁኔታ በሰጠው መግለጫው እንዳለው ዓለማቀፉ ማሕበረሰብ በቅድምያ ተኩስ ቆሞ በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች እርዳታ እንዲደርስ ግፊት እንዲያደርጉ አሳስቧል። እዚህ ላይ አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ በብራስልስ ረዥም ጊዜ የቆዩና መለስ ዜናዊና ብረሃን ገብረክርስቶስ በዚችው ከተማ ብዙ ግንኙነት መስርተው እንደነበር የሚታወስ ነው።

ደብረጽዮን መለዮ ለብሰው የታዩበት ምስል

ይህንኑ ተከትሎ መንግስት ሰሞኑንን “ድርጅታዊ ህልውናው እንደሞተ፣ የሚያስተዳድረው ቦታ፣ የሚመራው አካል፣ የሚያዝበት መዋቅር የሌለው፣ ሽብር የሚያስፋፋበት ኢኮኖሚውን የተነጠቀና በተወሰኑ ህይወታቸውን በሚወዱ ጥቂት ሃይሎች መሪነት ወደ ስንዴ ዘረፋ የገባ፣ በዋለበት የማያድር፣ ህጻናትን እያፈነ የሚያስቸርስ …” ሲል አዋድቆና አኮስሶ የጠራው የትህነግ ትርፍራፊ ” ውሮ ወሸባዬ” ሲል  የሚያሳይ ምስል ይፋ አድርጓል።

ምስሉ የቀድሞው የትግራይ ክልል መሪ የነበሩት ዶክተር ደብረጽዮን ባርኔጣ ለብሰው፣ ሰውነታቸው ተጎሳቅሎ የሚታዩበት ሲሆን ክላሽ በታጠቁ ወጣቶች ተከበው ይታያል። በዚሁ ጭፈራ መሳይ ስዕል ” አለን” የሚል ሃሳብ ለማስተላለፍ የታሰበ ይመስላል። ለወትሮው ፈጥሮ ስም የሚሰጠው የፌስ ቡክ ሰፈር ይህንኑ ምስል ያሻውን ስያሜ እየሰጠ የተሳለቀበት ሲሆን፣ ለሚደግፉዋቸው ደግሞ ደስታን ሰጥቷል።

ከደስታው ስሜት ውስጥ ያለው ረመጥ መለካት ባይቻልም፣ እኒያ ሊፈርጡ የነበሩ መሪ፣ እንደታቦት በሰው ትከሻ ላይ ሆነው ሰልፈኛ ሰላምታ ሲሰጡ የነበሩ መሪ በስተርጅና በዚህ ደረጃ መታያታቸው ኩራት ሊሆን እንደማይችል የአብዛኞች እምነት ነው። ከ ICG የተኩስ ማቆም ጥሪ ጋር ተሳስሞ የዚህ ምስል መለቀቅ፣ ” የትግራይ መከላከያ በሺህ የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላትን ገደለና ማረከ” ዜና መከተሉ የተኩስ አቁሙን ጣያቄ ይበልጥ ለማጉላት እንዲረዳ ታስቦ የሚሆን ይመስላል።

ጆን ባይደን አዲስ አበባ የላኩዋቸው ሴናተር ” ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲደረግ ጠይቄያቸው አልተቀበሉትም” ሲሉ ያቀረቡትን ሪፖርት፣ ከዛም የአውሮፓ ህብረት ” እንደ ዱቄት አየር ላይ ተበትኗል” ሲሉ የጠሩትን ሃይል ያካተተ ስልታዊ የሽግግር መንግስት ጥያቄ ማቅረቡ፣ መከላከያ የሃሰት ቅንብር እነደሆነ የገለጸውን የግድያ ቪዲዮ እያሰራጩ ያሉ ሚዲያዎች ለርዳታ ስራ ሲባል ተኩስ ማቆም ሊደረግ እንደሚገባ በሚወተውቱበት ወቅት፣ ጫካ ያለው ሃይል የድል ዜና ደጋግሞ ማሰማቱ ይህንኑ ውትወታ ለማተናከርና ” ጦርነቱ እየተባባሰ ነው” በሚል ኢትዮጵያ ላይ ያለው ጫና እንዲጠናከር ለማድረግ እንደሆነ አስተያየት ይሰጣል። ይህም ብቻ ሳይሆን በሌሎች ቦታዎችም በተመሳሳይ ግድያና ግጭት ሪፖርት እንዲደረግ እየተሰራ ነው።

” ግፉ ቀጥሏል” ለማስባል በመቶ የሚቆጠሩ ቄሶች እንደተገደሉ፣ መስጊድ እንኳን ገንብተው እንዳያመልኩ፣ በቂ የመቀበሪያ ቦታ የተከለከሉትን ሙስሊሞች ሳይቀር የመከላከያ ሰራዊት እንደጨፈጨፈ በማስመስል ሪፖርቶች እየቀረቡ ነው።

የመንግስት ሩጫ 

መንግስት ይፋ እንዳደረገው መከላከያ በስምንት ግምባሮች ዘመቻውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ዘመቻው በተጠናከረ መልኩ መቀጠሉን ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ በይፋ አስታውቀዋል። ጀነራሉ ትህነግ ፈርሷል ኢሉ ” የስንዴ ሌቦች” ያሉዋቸውን ሃይሎች መከላከያ የገቡበት ገብቶ እየለቀመ ለህግ እያቀረበ መሆኑንን በድፈናው ገልጸዋል። ጀነራሉ አይናገሩት እንጂ በሰሞኑ ዘመቻ ታማኝ ወታደራዊ መረጃ የሚያገኙ እንዳሉት መከላከያን ከከዱት ጀነራሎች መካከል እስካሁን ዘጠኝ ተገድለዋል። ከሁለት ሺህ በላይ ተገድለዋል። በሺህ የሚቆጠሩ ተማርከዋል። እጅ ሰጥተዋል።

መንግስት ዝርዝር መረጃ ከልክሎ እያካሄደ ያለው ዘመቻ እየከረረ የሄደውን የነጮቹን ጫና ቀድሞ ጫካ ለጫካ የሚሹለከለኩ ያላቸውን አመራሮች ለመያዝ ወይም ለማስወገድ ነው። ጉዳዩን የሚከታተሉ እንደሚሉት አሁን ጫካ ካሉት ውስጥ የፖለቲካው ቀንደኛ መሪ የነበሩት ከተመቱ ማንናውም በር ክፍት ሊሆን ይችላል።

መንግስት ኮሮና፣ ሻጥር ወለድ የኑሮ ውድነት፣ ምርጫ፣ የሱዳን ወረራ፣ የውስጥና የውጭ ባንዶች፣ የዘር ክፍፍልና የጽንፈኛ አካላት ደባ፣ ተከፋይ ሚዲያዎች ቅስቀሳ፣ በጠላት ወጥመድና አጀንዳ የሚነዱ ክፍሎች ዘመቻ፣ በቀድሞ የትህነግ እሳቤ በየቦታው የተሰገሰጉ አመራሮችን… በተለይም የግብጽን ሴራ አንድ ላይ ለመሸከም ስለሚከብደውና ክንዱም ስለሚዝል ዘመቻውን ካጠናቀቀና እንደ አሳቡ ድል ከቀናው ትግራይ ላይ የአቋም ለውጥ ሊያደርግ እንደሚችል ይጠበቃል።

የነጮቹ ጫና 

የአውሮፓውያኑ ጫና ከእንግሊዝ በስተቀር ፍርሃት እንደሆነ አንዳንድ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ይናገራሉ። አውሮፓ ስደተኞች የመቀበል ስጋት ስላለባት ነው የትግራይን ጉዳይ እየፈራችና እየተባች፣ እንዳንዴም እንደ እባብ እየተሳበች ለታለዝብ የምትፈልገው። ቀውሱ በዚህ ከቀጠለና፣ /ቀውሱ ለፖለቲካ ፍጆታ ስለሚፈለግ እንዲቆም አይደርግም/ አውሮፓ ሰደተኛ የመቀበል ግዴታ ሊጫንባት ይችላል። ይህ ከሆነ ደግሞ ሁሉም አገር ጥሎ የሚወጣ ስለሚሆን ስጋታቸው ከፍተኛ ነው። በዚህ መነሻ ኢትዮጵያ ላይ ጫኛ የሚያደርጉ አገሮች አሉ። እንድሊዝ ግን ከዚህ በተለየ እንደሆነ ከትህነግ አመሰራረት ጀመሮ በርካታ ማስረጃ በማቅረብ ዓላማዋ የተለየ እንደሆነ የሚያስታውቁ አሉ።

አሜሪካ በእስራኤል ምልጃ የግብጽ አጀንዳ አስፈሳሚ ስለሆነች እንጂ ሌላ ምንም መነሻ እነደሌላት ባለሙያዎች ይናገራሉ። አይሁዱ አዲሱ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአገራቸው አቋም ቢሆንም በግልጽ መረጃ አልባ በሆነ ጉዳይ ኢትዮጵያ ላይ የሚዛበቱትም ከዚሁ የደም/ የዘሬ ያንዘርዝረኝ ስሜታቸው/  አጀንዳቸው ተነስተው ነው።

እናም አሜሪካ በዚሁ የአስፈጻሚነት ሚናዋ ሳታስበው ” እንደ ህወሃት ያታለለን የለም” ስትል እንዲወገዱ በተስማማች ሁለት ዓመት ውስጥ ዳግም  ቁልቁል ወርዶ ” የስንዴ ሌባ” ከተባለ አካል ጋር ” ፍቅር እሹሩሩ” የምትለበት ምንም ዓይነት ስትራቴጂካል የላትም። ኢትዮጵያ “የአባይ ወንዝን ግንባታ ነገ አቆማለሁ፣ ውሃውን መሙላት አዘገያለሁ” ብትል፣ አምሬካ 360 ዲግሪ እንደምትዞር ፖለቲከኞች የሚናገሩት ያለ አንዳች ማመንታት ነው።

እርግጥ የትህነግ ሰዎች ለባይደን ምርጫ ከዴሞክራቶች ጋር ሆነው በርካታ ሃብት አጥፍተዋል። የምርቻው ቅስቀሳ አካል ሆነው ዶላር ረጭተዋል። ዶናልድ ትራምፕ ወደ ዋይት ሃውስ ሲገቡ ያባረሯቸው ” የቀን ጅብ” ዲፕሎማቶችም ታክለውበት ትህነግ የከሰከሰው ሃብት በዩልንታ ከንፈር እንዲመጠጥላቸው ቢያደርግም ይህን ያህል አይንን በጨው አጥቦ ጥብቅና ለማስቆም የሚደርስ እንደማይሆን በዚህ ጉዳይ ጠለቅ ብለው የጻፉ በቀጥታም ባይሆን በተዘዋሪ አመላክተዋል።

ተከፋይ ሚዲያዎች

ተከፋይ ሚዲያዎች ሁለት አይይነት እንደሆኑ ሰሞኑንን አንዳንድ የድረ ገጽ ጸሃፊዎች እየገለጹ ነው። በስውር የሚጎርሱና በገሃድ ነጮቹ ለራሳቸው ጥቅም ማስጠበቂያ ባቋቋሟቸው ሚዲያዎች ተቀጥረው አቋም በተቀያየረ ቁጥር እየተቀያየር የሚኖሩ የአደባባይ ሪፖርተሮች ይሉዋቸዋል።

በስውር የሚሰሩት ተከፋዮች ተናበው፣ አጀንዳ የሚፈለፍሉና ራሳቸውን በእምነት ስም፣ በአክቲቪስት ስም፣ በገለልተና ሚዲያ ስም፣ በተቆርቋሪነት ታርጋ የሚንቀሳቀሱ ሲሆኑ፣ በዋናነት ህዝብን አወናብዶ ለመንዳት መመሸጊያ የሆነውን የዘር መርዝ ግተው የሚግቱ በክፋታቸውና በአደገናኛነታቸው ይገለጻሉ። ለሰው ልጆች ወይም ለብሄር መከራከር የሚያስወነጅል ባይሆንም፣ ጽንፍ በመርገጥ የልዩ አጀንዳ ማስፈጸሚያና የስልጣን መጨበጫ የሚያደርጉት አገሪቱን ዋጋ እያስከፍሉዋት ነው። ለዚህ ስሌታቸው የሚጠቅማቸው ወይም ኪስ የሚያደልብ ከሆነ ደንታ ስለሌላቸው ወዲያውኑ ” ተሸካሚ” እንደሚባለው ሁሌም እየተጫኑ ህዝብ ላይ ይረጫሉ።

በውጭ አገር ያለው የሚዲያ ዘመቻና ፍትሃዊ ያልሆነ የግነት ድራማ ብዙ ሊባልለት ቢገባም ዛሬ የደረሱት ” ተኩስ አቁሙ” ባስቸኳይ ተጋራዊ እንዲሆን መግፋት ላይ ነው። አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ነን ባዮች፣ አይሲጂ፣ … እና ቀለብተኞቹ ሚድያዎች ቀደም ሲል የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ እንዲገባ ሲማጸኑ እንድ ላይ እንደነበረው ዛሬ ይህን ዜማ እያዜሙ ነው። ተኩስ አቁሞ ሰላም ማውረዱ ለህዝብ ሲባል ደግ ቢሆንም ” መርዝ ያረገዘ” ሃሳብ ሲሆን ግን ዞሮ አገጋው ለአገር ነው።

በውጭ አገር ካሉት ተከፋይና ባለ ልዩ ጥቅም ሚዲያዎች ባሻገር ነጮች ቀጥረው የሚያሰሯቸው ወገኖቻችንም በዚሁ የአጀንዳ ተሸካሚነትና  በዘር ቋት ውስጥ ተወትፎ የማራገብ አዝማሚያቸው እየከፋ እየሄደ ነው። ድሮ በጫካው ትግል ወቅት ለወያኔ ሲላዝኑ የነበሩ ዛሬም አሉ። ወያኔ እንዳሻው ሲቀተቅጥ፣ ሲዘርፍ፣ ሴገድል፣ ጉድጓድ ሲከት፣ በምርጫ ስም ሲነግድና ዜጎችን በዓለሞ ተኳሾች ሲደፋ ዝም ብለው የአለቆቻቸውን አቋም ሲያራምዱ የነበሩ ዛሬም አሉ። አሁን ደግሞ የአገር መከላከያ ሰራዊት በግፍ ክህደት ተፈጽሞበት፣ መሳሪያ አውርደው የታገቱት ሲታረዱ፣ ሴቶቹ ሲደፈሩ፣ አገር ተባቂ ወገን እንደ ባዕድ ባዶ እግሩን እየተፋበት ሲሄድ፣ በከባድ መኪና ሲጨፈላለቅ … “አልሰማሁም” በሚል ወይም በቂ ጊዜ ባለምስተት ውጤቱ ባስከተለው ጉዳይ ላይ አተኩረው እየሰሩ ነው።

የሰው ልጅ መቼም ቢሆን ህሊና አለው። ህሊና ደግሞ ትልቁ ፍርድ ቤት ነው። ዛሬ አገር በተለያዩ ሁኔታዎች ተወጥራ ሳለ ሚዛንን መሳት አንድነትን ያላላል። አንድነት ሲላላ መውደቅ ይመጣል። መውደቅ ደግሞ ዘር፣ ቡድን፣ ሃይማኖት፣ ቀለም፣ ሃብት፣ ለነጭ አሸርጋጅ የነበሩትን አይለይም። አገር አልባ ዜጎች ዘወትር አፍረት ታቅፈው ከማለፍ ሌላ አማራጭ የላቸውም። ስለሆነም ሚዛናዊ ለመሆን መሞከር ከሁሉም ዘነድ የሚተበቅ እነደሆነ የጋባቸው ይመክራሉ። አለያ ግን ሁሉም ነገር ተመዝግቦ በሚቀመጥበት የዛሬው ዓለም፣ ወይ በበጎ አለያም በባንዳነት መፈረጅ አይቀርም። ልጅ፣ የልጅ ልጅ … የሚወርሰው ይህንኑ ነው። ሽፍቶችን፣ በደም የተቸማለቁ አራጆችን፣ አስከሬን ላይ ቆመው እንደ ጀብዱ ሲያናፉ የነበሩትን ማስተዋወቅና የጎደፈውን ስም በአዲስ ብራንድ ጭራ እየቆሉ ማስተዋወቅ ነጹሃንን ከጉድጓድ እያወጡ ዳግም መረሸን ወይም ማረድ ነው።

ሃቅ ባይኖርም ሁሉም ጋር ችግር ቢኖርም ትልቋን ምስል ማየት የጊዜው ጥሪ ነው። እጅ ጥምዘዛውና የማዕቀቡ ማስፈራሪያ አጋፋሪነት ያብቃ። ዛሬ በአደባባይ አገራችን ማእቀብ እንዲጣልባት፣ ከዓለም እንድትገለል፣ የውስጥ ጉዳዩዋን ማከም እንዳትችል የተከፈተውን ዘመቻ በብር፣ በሰልፍ፣ በፈጠራና በግነት ድራማ  እየተጫወቱ ያሉ ክፍሎች በኢትዮጵያ ሰፊ ሕዝብ ላይ ክህደት እንደፈጸሙም ሊታወቅ ይገባል። ይህ ታሪካዊ ክህደት ታሪክ ነው። በባንዳነትም ሆነ በአገር ክህደት ይቀመጣል። በአክሱም ወደፊት ይቆማል እንደተባለው ስሙ የማይታወቅ ግምብ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ልብ ውስጥ የሚታወቅና የማይፈስር የክፋት ሃውልት አታኑሩ!! በሁሉም ስፍራ የሰው ልጆች ክብር ይገባቸዋል። የግፍ ትልቅና ትንሽም የለውምና ሚዛናዊ መሆን የጊዜው ጥያቄ ነው። ሕዝብ ወገብህን አጥብቅ!! የመጣውን ቻል!! መንበርከክ የለም

Exit mobile version