Site icon ETHIO12.COM

የ“ጄኖሣይድ ” ፕሮጀክቶች የደም ፖለቲካ አራማጆች የመጨረሻው የትርምስ እቅድ!!

ለማጋደል በጀት ይመደባል። በጀቱን የሚያከፋፍሉ አሉ። በበሉት መጠን ሰው ለማረድ የሚሰማሩት ወደ ማረዱ ከመግባታቸው በፊት ” ነጭ ነጯን” ምናምን እያሉ መርዝ ያሰራጫሉ። ስልጣን የተከለከሉ፣ የትህነግ ቅሪቶችና የቀድሞ ካድሬዎች በብሄርና ሰባኪነት ስም ተከልለው በተቆርቋሪነት ካባ ተጀቡነው የልቂት ከበሮ እየተናበቡ ያራግባሉ።

መንግስትን በየመካከሉ እያስገቡ ማስጠንቀቂያ ይሰጣሉ። እርዱ እንዲከናወን በተወሰነበት አካባቢ የሚኖሩ ” አስቀድመው መንግስት ሃይል እንዲያስገባ ተይቀው ነበር” የሚል ሃሜት ለማዝነብ ሰዎችን እየተቀሱ ፍርሃት እንዳለ ጠቆም አድርገው ያልፋሉ። ከዛም እርዱ በተፈጸመ ቅጽበት የተቀነባበረ ቪዲዮና የድምጽ ማስረጃ እንደ ሻምፒዮንስ ሊግ አከራካሪ ጎል ከተለያየ አቅጣጫ የተቀዳ ዘገናኝ ፊልም ያሳዩናል። የሚሰጣቸውን ሳያላምጡ የሚውጡ፣ የማይጠይቁ፣ የማይመረመሩ፣ ይህንኑ ቪዲዮ ምሬት እየጨመሩ ያሰራቻሉ። በማህበራዊ ሚዲያዎች አውቆ አስለቃሾች ለቅሶውን ያደራሉ። በምስኪን ዜጎች ደም ድራማ የተውናሉ። ያልገባቸው 360 ዲግሪ ይዞርባቸዋል። ነጭና ትቁር መለየት እስከማይቅቱ በድራማው ይሰክራሉ።

ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ አዲስ አበባ ደርሶ ወንበር ሲከለከልና ያሰበውን ሲያጣ አገር ከድቶ ደርግ እንዲፈርስ የተጫወተውን አይነት ድራማ ለመተውን ሲነሳ ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ” ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ” ብሎ አሟረተ። ዛሬ ደግሞ አኦባንግ ሜቶ አዲስ አበባ ከርሞ አሜሪካ ሲመለስ ” ኢትዮጵያ ትፈርሳለች” አለ። ይህን ተከትሎ እርድ እንዲከናወን በበሉት መጠን ቁጭ ብለው ካፋትና የመተላለቂያ አጀንዳ የሚያመርቱት እርጉሞች ” የጄኖሳይድ ፕሮጀክት” ይዘው መጡ። የትህነግን እብሪትና ግልሙትና ያመከነው የመከላከያ ሰራዊታችን ደም ሳይደርቅ ዓለም ፊት ” ጄኖሳይድ የማጋለጥ ዘመቻ” ብለው ተነሱ። ዓላማው ግልጽ የሆነው ይህ ንቅናቄ ምርጫ እንዳይካሄድ ብቻ ሳይሆን የውጭ ሃይሎችንም አጀንዳ ያነገበ፤ በአባይ ግድብ የመጨረሻ እጣ ፈንታ ላይ ወሳኝ ወቅት በመሆናችን የ” ጭራቆቹን” ሃሳብ ለመተግበር ያለመ ነው። ከዚ ቀጥሎ ያለው ሃሳብ መነሻውን ስለሚያጎላው ተውሰነዋል።

ሃሳቡ የቀድሞው ” ሰብአዊ መብት ተሟጋች “ ኦባንጎ ሜቶ የ “Failed State” ስጋት ላይ የቀረበ የግል አስተያየታቸው ከተሰጠ ጽሁፍ ላይ የተውሰደ ነው። ጸሃፊው አቶ አንድነት ይበልጣል በስፋት ያቀረቡትን ሃሳባቸውን አስፈንጣሪውን ተጭነው ያንብቡ። ” የጄኖሳይድ ፕሮጀክት” በሚል ንዑስ ርዕስ ስር ያቀረቡት ጉዳይ ግን እጅግ ጥንቃቄ የሚያሻው በመሆኑ ቆርጠን እንዳለ ከስር አትመነዋል።

“የጄኖሣይድ” ፕሮጀክቶች – “ፕሮጀክት ጄኖሣይድ”

“የጄኖሣይድ” ፕሮጀክቶች – “ፕሮጀክት ጄኖሣይድ”

1ኛ) “ቪኦኤና ቢቢሲ ትግርኛ (ጣቢያዎች) ዜና ተርበዋል፤ እናንተ ዜና እየፈጠራችሁና እየፈበረካችሁ፣ እነዚህን የተራቡ ጋዜጠኞች (Single celled Organisms) መቀለብና ማጥገብ አለባችሁ”፣

2ኛ) “የኤርትራ ተቃዋሚዎችም ከእንግዲህ እንደቀድሞው ተቃውሞ ብቻ ለማሰማት ኤርትራ ኤምባሲ ደጅ መሄድ የለባችሁም፤ ከሄዳችሁ የምትሄዱት ኤምባሲውን ለማቃጠል መሆን አለበት” እያለ ለኃይል እርምጃ ሲያነሳሳቸው ነበር፡፡

እርግጥ፣ ከፊታችን የተደቀነው ፈተና እጅግ ከባድና አስፈሪም ነው፤ ይህ አያጠያይቅም፡፡ ሆኖም የኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ዕድል ከፈጣሪ በታች፣ በኛ በልጇቿ እጅ ላይ ነው፡፡ ከተባበርን እንቆማለን ፈተናውንም እንሻገረዋለን፡፡ ከተከፋፈልን እንወድቃለን፡፡ ጸጥታን፣ አንድነትንና ሉዓላዊነትን ከማስከበሩ ወሣኝ ትግል ጎን ለጎን በልዩ ትኩረትና በአንድነት ተረባርበን ልናሳካቸው የሚገቡት ሁለቱ ፈተናዎቻችን የግንቦቱ ምርጫና የሐምሌው የግድቡ ሙሌት ናቸው፡፡ እነርሱ ላይ ያለ ልዩነት ተረባርበን ማሳካት የዛሬን ብቻ ሣይሆን የነገን ትልልቅ ስጋቶች ያስወግዱልናል፡፡ ብርሐንና ሰላምም ያመጡልናል!

ውድ ኦባንግ፣ “እኛን እየጎዳን ያለው ድንጋይ ወርዋሪው ብቻ ሣይሆን ዝምታችንም ነው” አላልክም? ተስፋ መቁረጥ የለም!! በዚህ ፈተና ውስጥና በጥረቱም ላይ አብረን ነን!! በርታ የኔ ወንድም! ማሸነፋችን የማይቀር ነገር ነው!

ፈጣሪ ወደ ብርሐንና ሰላም ያሸጋግረናል፡፡

በመከላከያ ሰአርዊታችን ላይ የተፈጸመውን ክህደትና እልቂት፣ በተለይም የሴት ወታደሮች ጡት ሲቆረጥ፣ በማይካድራ በሺህ የሚቆተሩ ዜጎች በብሄራቸው ተለይተው በጅምላ ሲታረዱ፣ ኦባንግ ሜቶም ሆነ “ድርጅታቸው” ምንም አለማለቱ ገራ እያጋባ ሳለ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች በሚል የሞሳድ ተላላኪ ዳዊት ከኈለት ዓመት ተኩል በፊት ያለውን ደግሟል። በዚህ ጉዳይ ላይ ቃለ መጠይቅ አድርገን የምንመለስ ሲሆን ኦባንጎ ሜቶ የ “Failed State” ስጋት ላይ የቀረበ የግል አስተያየታቸው ሊንኩን ተጭነው ያንብቡ።


Exit mobile version