Site icon ETHIO12.COM

መቀለ ከተማ ተደብቆ የሚሰራው የፕሮፓጋንዳ ሃይል ተያዘ፤ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ውስጥ አሉበት

... በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራር መዋቅር ውስጥ በመሆን ከፀረ ሰላም ሃይሎች ጋር እየሰሩ የነበሩ ግለሰቦችን ጨምሮ የትግራይ ሚዲያ ሃውስ ጋዜጠኛ ፍፁም ብርሃኔ እና የአይጋ ፎረም ኢዲቶሪያል ዋና አዘጋጅና የኢትዮጵያ ተወካይ ጋዜጠኛ ታምራት የማነ በመቀሌ ከተማ በግለሰብ ቤት ስቱዲዮ ተከራይተው የውሸት ፕሮፓጋንዳ በቀጥታ ስርጭት እያስተላለፉ እያሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።

በልዩ ዘመቻዎች ሃይል 2ኛ ኮማንዶ ብርጌድ 3ኛ ኮማንዶ ሻለቃ በትግራይ ክልል ህግ በማስከበር ዘመቻ አመርቂ ግዳጅ መፈፀማቸው ተገለፀ።የትግራይ ሚዲያ ሃውስ ጋዜጠኛ ፍፁም ብርሃኔ እና የአይጋ ፎረም ዋና አዘጋጅና የኢትዮጵያ ተወካይ ጋዜጠኛ ታምራት የማነ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የ3ኛ ሻለቃ ዋና አዛዥ ሻለቃ ደረጄ ዴቢሳ እንደገለፁት፣ በትግራይ በተደረገው ህግን በማስከበር ዘመቻ ጠለት የሚመካባቸውን ምሽጎች በሶሮቃ፣ በዳንሻ፣ በባካር፤ በመሶበር፤ በጨርጨርና በአይደፈር ተራሮች ላይ የተገነቡ ምሽጎችን በመስበር የጠላትን ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን በመቆጣጠር ታሪክ የማይረሳው ገድል ፈጽመዋል፡፡

አሁንም ሻላቃው የመቀሌ ከተማ ሁለንተናዊ የፀጥታ ሁኔታዎችን ለማረጋገጥ ለ24 ሰዓት በቀንና በሌሊት የፖትሮሊንግ ስራዎችን በመስራት በከተማዋ ውስጥ በግለሰብ እጅ የሚገኙ ከቀላል እስከ ቡድን መሣሪያዎችን በማስፈታት ስርቆትና ዝርፊያ መቀነስ መቻሉን ዋና አዛዡ ተናግረዋል።

በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራር መዋቅር ውስጥ በመሆን ከፀረ ሰላም ሃይሎች ጋር እየሰሩ የነበሩ ግለሰቦችን ጨምሮ የትግራይ ሚዲያ ሃውስ ጋዜጠኛ ፍፁም ብርሃኔ እና የአይጋ ፎረም ኢዲቶሪያል ዋና አዘጋጅና የኢትዮጵያ ተወካይ ጋዜጠኛ ታምራት የማነ በመቀሌ ከተማ በግለሰብ ቤት ስቱዲዮ ተከራይተው የውሸት ፕሮፓጋንዳ በቀጥታ ስርጭት እያስተላለፉ እያሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።

በግለሰቦቹ ቤት በተደረገው ፍተሻም ለጁንታው ታጣቂ ቡድን ወደ በረሃ ለመላክ የተዘጋጁ በርካታ መድሀኒቶች ፤ አልባሳትና የፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ የኤሌክትሮኒክ እቃዎችና በርካታ ዶክመንቶች በቁጥጥር ስር መዋሉን አዛዡ ተናግረዋል።በአሁኑ ወቅት በመቀሌ ከተማ በሰፈነው ሰላም ህዝቡ የዕለት ተዕለት ተግባሩን በሰላማዊ መንገድ እየፈጸመ ከመገኘቱም በተጨማሪ የኮማንዶ ሻለቃው አባላት ከመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ለትግራይ ክልል የሚደረገውን ሁለንተናዊ እርዳታና ድጋፎችን የተጠናከረ እጀባ በማድረግ ለህብረተሰቡ እያደረሱ እንደሚገኙ የሻለቃው ዋና አዛዥ አክለው ገልጸዋል።(ምንጭ፡- የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት)

Exit mobile version