ETHIO12.COM

በአስመጪ ዳዊት የማነ ሀሰተኛ ሰነድን ተጠቅሞ ወደ ሀገር ዉስጥ ሊገባ የነበረ ገጀራ ተያዘ

ከፌደራል ፖሊስ ፈቅድ እንደተሰተው ባምስመሰል በተጭበረበረ ሰነድ ርክክብ ተፈጽሞ ባለቤት የተባለው ሰው ከተረከበ በሁዋላ በተደረገ ክትትል 186 ሺህ 240 ገጀራ በቁጥጥር ስር ዋለ። በጅምላ ጭፍጨፋ በተካሄደባቸው አገራት በተገነ ልምድ ገጀራ ክልከላ የጣለበት የእጅ የጥፋት መሳሪያ ነው። ገጀራው በቁጥጥር ስር ከዋለ በብሁዋላ በማህበራዊ ሚዲያዎች ህጋዊ ፈቃድ እንዳለው እየተገለጸ የሚሰራጨው ደብዳቤ ሃሰት መሆኑም ተመልክቷል።

ከ15 ቀን በፊት በአስመጪ ዳዊት የማነ ስም ብዛቱ 186,240 የእጅ ገጀራ በአራት ባለ 20 ጫማ ኮንቴይነሮች ከቻይና ተጭኖ ሞጆ ጉምሩክ ይደርሳል። እቃው በዲክላራሲዮን ቁጥር 4-1919/21 ተመዝግቦ ወደ ሀገር ዉስጥ እንዲገባ ከፌዴራል ፖሊስ የተፈቀደለት በማስመሰል እና ሐሰተኛ ሰነድ የተዘጋጀለት ነው። ይኸው ሃሰተና ሰነድ ለገቢ ዕቃ አወጣጥ የሰነድ መርማሪው አቅርቦ ሰነዱ ተመርምሮ ከ7.7ሚሊዮን ብር በላይ ቀረጥና ታክስ ይከፈልና እቃው የለቀቃል። እቃው ከተለቀቀ በኃላ በጉምሩክ ኮሚሽን እና በሞጆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኢንተለጀንስ በኩል ክትትል ተደርጎ የቀረበው ሰነድ ሲጣራ ሐሰተኛ እና እቃዉም ወደ ሀገር ዉስጥ እንዲገባ ከፌዴራል ፖሊስ ፈቃድ ያልተሰጠው መሆኑ ተረጋገጠ።

ጉዳዩ ከ15 ቀን በፊት የተፈጸመ ቢሆንም፤ አስመጪው “ያቀረብኩት ሰነድ ህጋዊ ነው” በማለት ቅሬታ ስላቀረበ ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጋር በጣምራ የማጥራት ስራ ተሰራ። እንደ ኦቢኤን ዘገባ ማጣራት የተካሄደበት ሰነድ ሐሰተኛ እና ከፌደራል ፖሊስ ፍቃድ ያልተሰጠው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

በተጨማሪም በጉምሩክ ኮምሽን ሰራተኛ የእጅ ገጀራው ተገቢውን የጉምሩክ ስነ-ስርዓት በመፈጸም እንዲስተናገድ የሚገልጽ ሐሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ለማውጣት የተሞከረ ሲሆን ይህም ሐሰተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ይህን መነሻ በማድረግም በፌዴራል ፖሊስ ለሞጆ የወንጀል ምርመራ ማስተባባሪያ ፅ/ቤት መረጃዉን በመስጠት በተደረገው እልህ አስጨራሽ ክትትል የእቃው ባለቤት እና ትራንዚተሩ ተይዘው ጉዳዩ በምርመራ ላይ ይገኛል። ገጀራ ክልከላ ከተደረገባቸው እቃዎች አንዱ ሲሆን ከፌደራል ፖሊስ ሕጋዊ ፈቃድ ሳያገኙ ማስገባት አይቻልም። በዚም ምክንያት ነው አስመጪው አቶ ዳዊት የማነ ከፌደራል ፖሊስ ህጋዊ ፈቃድ እንዳገኙ በማስመሰል ገጀራውን በሃሰተኛ መረጃ ያስገቡት።

በአንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በጉምሩክ ኮምሽን ባለሙያ እቃው እንዲወጣ የተፈቀደበት ደብዳቤ በማስመሰልና የሐሰተኛውን የደብዳቤ ፎቶ በመጠቀም አስመጪው ሕጋዊ እንደሆነ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማስታወቁን ዜናው ያመለክታል። በማህበራዊ ሚዲያ ገጀራው መያዝ የለበትም የሚሉትና ሃሰተኛ ደብዳቤውን በመለጠፍ የሚሞግቱት ወገኖች ላይ ክትትል እየተደረገ መሆኑም ተሰምቷል። የተያዘው ገጀራ መለቀቅ እንዳለበት እየሞገቱ ያሉት ክፍሎች ምኞታቸውና ሃሳባቸው ግልጽ መሆኑም ተመልክቷል።

ሃሰተኛ ደብዳቤው

Exit mobile version