ETHIO12.COM

ያደግንበት ኦሮሙማ


አማራዋ እናኑ ክብረት፡ ትግሬዋ የሰለሞን ወዳጆ እናት፤ የኦሮሞው የፈይሳ ሚስት አማራዋ ብዙዬ (ሀደ ዳዊት)፤ የከምባታዎቹ ትቸር አቤና መምህርት ሀቦ፤ ጉራጌዎቹ የመምህር መለሰ ቤተሰቦች፤ የአረብና ኦሮም ክልሶቹ የአብደላ ልጆች እነ ቶፊቅ፤ ሮማን፤ ሀሊማና ቹቹ (ቃና ቲቪ በለው) ከዚያም ሲያልፍ ባለሱቆቹ እነ አክመል ኬረታና ጮርናቄ ቤት ያላቸው የሰይዶ ቤተሰቦች፡፡ ትኩስ ፉርኖ ዳቦ ሻጩና በብስክሌት ሂያጁ ብሩ ሁንዴ፤ ባለፈረንጅ ላሞቹ አያሌው ተገኝና አያሌ ሌሎች የኩዩ ነዋሪዎች የልጅነት ትዝታዬ አካል ናቸው፡፡

By Tatek Kebede


ያደግንበት ኦሮሙማ ቁመቱ መለሎ እንደ አማዞን ዛፍ የተስተካከለ፤ አለባበሱ ዘወትር ሽክ፤ ትህትናና እንግሊዝኛ የሁል ጊዜ ማጌጫው፤ የሁላችን አባትና ከገርበጉራቻ አድባራት አንዱ፡፡ ለራሱ እንደነ ነብሪድ ያሉትን ለገርበጉራቻ ህዝብ ደግሞ አያሌ ምሁራንን ያፈራ ባለውለታ፡፡

የፊት ቅርፁ የቭላድሚር ፑቲንን የመሰለ፤ ቁመቱ ዘለግ ብሎ ሰውነቱ እንደጃንሆይ መጠጥ ያለ፤ ከቀደምት የከተማችን ዋርካዎች ተርታ የሚሰለፍ፡፡ የእነፍቅሩ አባት፡፡

ጥፊው አይጣል ነው፤ በተቆለመመ እጁ ካላጋህ ጆሮህ እስከወዲያኛው ላይሰማ ይችላል፤ አማርኛ ቋንቋን ከጥፊ ጋር አስማምቶ ያስተምርሃል፤ ጣቶቹ ከሲጋራ ጋር የቆየ ወዳጅነት ያላቸው ይመስላል፤ ባልሳሳት ከጥርሶቹ መካከል አንዷ የወርቅ ናት፤ ይህም ታላቅ ሰው የሁላችን አባትና የከተማችን ሰንደቅ ነው፡፡ የእነቴዲ አባት፡፡

በቅደም ተከተል ፍሰሐ ዘ/ሚካኤል፤ ገብረ እግዚአብሔር መንግስተአብ ፤ ወንድሙ ከበደ ናቸው፡፡ ሦስቱም የገርበጉራቻ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራንና የቀደምት የከተማችን ዕንቁ ተማሪዎችን የቀረፁ ባለውለታ ናቸው፡፡ እርግጠኛ ባልሆንም የዘር ሀረጋቸው ከሰሜናዊቷ ኤርትራ ክፍለ ሀገር ይመዘዛል፡፡

አባመቻል ቦርጃ፤ ሰው ሁሉ በእግሩ በሚኳትነበት ከተማ ውስጥ እሳቸው የፈረስ ጋሪ ባለቤት ነበሩ፡፡ የቤተክህነት ትምህርት ቀመስ ስለነበሩ ሰላሌ በዕውቀት ብርሀን እንድተሎኮስ ክብሪት ያቀበሉ እሳቸው ሳይሆኑ አይቀርም፡፡ አባ መቹ ቀይ ሰው፤ አጠር ያሉ፤ ደስተኛና ሳቂታ ፊት ያላቸው፤ የተስተካከለ ግን የሚነፋነፍ አፍንጫ ባለቤት፡፡ አባተ የሚባል ልጅ አላቸው ለዓመት በዓል ከኩዩ ቢሞት አይቀርም፡፡


ዛሬ ግን እስካሁን ከመጣንበት እጅግ ፈታኝ ውስብስብ ችግሮች በመማር በአዲስ አስተሳሰብ ከመምሰል ወጥተን ወደ መሆን በመቀየር ችግሮችን በማረቅ ወደፊት መጓዝ ይኖርብናል። ለቀጣይ ትውልድም ፍትሃዊ እና ምቹ ሃገር ለመፍጠር መትጋትና መግባባት ይገባል። እንደ ሃገር ጠንካራ ሆኖ ለመቀጠል መግባባትና መስማማት ውዴታ ሳይሆን ግዴታም ጭምር ነው።

ከዕለታት አንድ ቀን አባ መቹ ቅድመ አያቴን የልጅ ልጆትን ትምህርት ቤት ያስገቡ ብለው መከሯት፤ እሷም ሳታቅማማ ከበደ ወንድሙን ስንቅ ቋጥራ፤ ፈራንካ አስጨብጣ፤ ፈረስ ሸልማ ከማይሞተው ደጃፍ ከትምህርት ገበታ ተቋዳሽ እንዲሆን ሰደደችው፡፡ አያቱ ላቀች ብሩ አቀማጥላና አስተምራ አሳደገችው፡፡ እኔም ታጠቅ ከበደ የላቀች ብሩ ሶስተኛ ትውልድ በ 1970ዎቹ መጀመሪያ ስወለድ ከአባቴ የመፅሐፍት መደርደሪያ ላይ የዚያን ዘመን ስላሴዎችን ማርክስ፤ ኤንግልስና ሌኒንን አገኘኋቸው፡፡

ባሻ ቅጣው፤ የኔ ጋሻ፤ አሉላ አባ ነጋ፤ ፍቅር እስከ መቃብር፤ አንድ ለአምስት፤ ዶሰኛው፤ ሰመመን፤ እሳት ወይ አበባ፤ አልወለድም፤ ኦሮማይ ወ.ዘ.ተና አያሌ ሌሎች መፅሐፍትን ገና በጨቅላነቴ ነበር ያነበብኳቸው፡፡ ጠቅላይ ሚንትር አብይ አህመድ በልጅነቴ ፈተና አርም ነበር እንዳሉት እኔም የጎበዞቹ ተማሪዎች የእነሰለሞን አረዳን ፈተና ጨምሮ የበርካታ የዚያን ዘመን የኩዩ ተማሪዎችን ፈተና ሳላርም አልቀርም፡፡

ታላቅ ወንድሜ ጥበቡ ማርክ እንዲጨምርላቸው በጉቦ የተማፀኑት የዘመኑ ሰነፍ ተማሪዎችም እንደነበሩ አጫውቶኛል፡፡ ዛሬ ላይ የአንዳንዶቹ ስልጣን ስለሚያስፈራ ስም አልጠራም፡፡ የሆነ ሆኖ የኔም አባት ከገርበጉራቻዎቹ አድባራት ይመደባል፡፡ የተዋጣለት ኦሮሞ የአማርኛ አስተማሪ ነው፡፡ ጉድ በል ጎንደር! ታድያ ቁማር ይወዳል፡፡ የበዓላት ቀናት ሳይቀር ቁማር ቤት ያመሻል፡፡ ሲለውም እዚያው ያድራል፡፡ከእለታት አንድ ቀን እሱን ፍለጋ ሄጄ፤ ካርታ ከሚጫወቱበት የአባ መቻል ቦርጃ ቤት ዘው ብዬ ስገባ ከአንበሳ የማይተናነስ ውሻ ተከመረብኝ፡፡ አስተኝቶ ይዘነጣጥለኝ ጀመር፡፡ ምን አለፋችሁ በልቶኝ ሲጠግብ ነው ትቶኝ የሄደው፡፡ ዛሬምድረስ ጠባሳውና የጥርሱ አሻራ በግራ እጄና እግሬ ላይ አለ፡፡ አባ መቹ ይሄ ልጅ ወደ ትምህርት ቤት ይሂድ ሲሉ ቁማር ቤት አዘጋጅተው መሆኑን ብታውቅ ላቀች ብሩ ከበደ ወንድሙን አበበ ወንድሙ አርጋ ባሳደገችው ነበር፡፡ ከበደ-ወንድሙ-ገመዳ-አሰሪ-ዶዶት-ኩሬ…

ደሞ አለላችሁ የጨፌ ዶንሳው ወርቁ ክበበው፤ ምትሀተኛው የጠረጴዛ ቴኒስ ተጫዋችና የእንግሊዝኛ ሰዋሰው አዋቂ፡፡ አጭርና ጀነን ያለው የእነ አበባየሁ አባት፡፡

town of Gebra guracha.

ክብሩ፤ ባለምላይ፤ ፍሬው፤ በላይነህ አድማሱ፤ ታደሰ ፈንታ፤ ጌታቸው፤ አርገታ ጃርሶ፤ ቶሎሳ፤ አንዱአለም፤ አወል፤ ውዴ ታደሰ፤ ባንትይረጉ፤ … ስንቱን መምህር አንስቼ ስንቱን እተወዋለሁ?! ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ ብሔር ብሔረሰብ ብለህ የምትጠራቸውን ሁሉ ማንነቶች ገርበጉራቻ አቅፋና አወዳጅታ እንደኖረች ዘልቃለች፡፡

በቡሄ ሆያ ሆዬ፤ በመስቀል አሳሴና በሰርግ ጊዜ የሽኖት ጭፈራ የማይለያይ፤ በከተራ በጥምቀት በአስተሪዮ ማርያም የፈረስ ጉግስ የማይነጣጠል፤

አማራዋ እናኑ ክብረት፡ ትግሬዋ የሰለሞን ወዳጆ እናት፤ የኦሮሞው የፈይሳ ሚስት አማራዋ ብዙዬ (ሀደ ዳዊት)፤ የከምባታዎቹ ትቸር አቤና መምህርት ሀቦ፤ ጉራጌዎቹ የመምህር መለሰ ቤተሰቦች፤ የአረብና ኦሮም ክልሶቹ የአብደላ ልጆች እነ ቶፊቅ፤ ሮማን፤ ሀሊማና ቹቹ (ቃና ቲቪ በለው) ከዚያም ሲያልፍ ባለሱቆቹ እነ አክመል ኬረታና ጮርናቄ ቤት ያላቸው የሰይዶ ቤተሰቦች፡፡ ትኩስ ፉርኖ ዳቦ ሻጩና በብስክሌት ሂያጁ ብሩ ሁንዴ፤ ባለፈረንጅ ላሞቹ አያሌው ተገኝና አያሌ ሌሎች የኩዩ ነዋሪዎች የልጅነት ትዝታዬ አካል ናቸው፡፡

ውሀ በእንስራ በማመላለስ ኑሮአቸውን የሚገፉት እማማ አቻሜ፤ ዛፍ በመቁረጥና በመፍለጥ ልጆቻቸውን የሚያስተዳሩት ገብሬ ማንያዘዋል፤ የባህል መድሃት አዋቂዋ፤ አዋላጇና ወጌሻዋ ገነት መኩሪያ፤ የዕድር ጡሩምባ እየነፉ ፈራንካ የሚያገኙት አባባ ጉተኔ፤ በወዙ የሚያድረው ገረመው ወፉ፤ ቀብራራውና የፈረንጅ ቡዳ በልቶት እንግሊዝኛ እንጂ የማይቀናው ከበደ ቆሌ፤ በቁሙ ከአውቶብስ ላይ ዕቃ የሚያወርደው የመናኸሪያው ሀብታሙ አቤቤ፤ በአህዮች ድንጋይ እያጋዘ ከተማዋን የገነባት የደኮ አባት ቱፋ፤ የከተማዋን እና የዙሪያ ገባውን ገጠር መንደሮች እህል ድቅቅ አርጎ የሚፈጨው ባለወፍጮው ጉደታ አያሌው፤ የአንድ ለናቱ ፎቶ ቤት ባለቤት ስሜና ስማቸውን ብጠራ የማልጨርሰው ህልቆ መሳፈርት የልጅነት መንደሬ ሰዎች ሰላሌ ስኖር፤ ገርበጉራቻ ተወልጄ ሳድግ የማውቀው የኦሮሞ ቀዬ፤ እኔ የማውቀው ኦሮሙማ ይህ ነው፡፡ ልዩነት የለውም፤ ጣፋጭና አዝናኝ ትዝታ እንጂ፡፡

Exit mobile version