Site icon ETHIO12.COM

“አቡነ ማቲያስ የሰጡት መግለጫ የግላቸው እንጂ የቅዱስ ሲኖዶስ ወይም የቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ አይደለም”

የፓትሪያርኩ መግለጫ የቅዱስ ሲኖዶሱን አሠራር ያልተከለተለ እና ከሲኖዶሱ ዕውቅና ውጭ የተካሄደ መሆኑን የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊና እና ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ ገልጸዋል።

ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ መሰል መግለጫዎች የሚሰጡት የምዕላተ ጉባኤውን እና የቋሚ ሲኖዶሱን አዎንታ ሲያገኙ መሆኑን አስታውሰው፤ “ቅዱስ ሲኖዶስ እና ቋሚ ሲኖዶስ ሳይወስን ቅዱስ ፓትሪያርኩ በግላቸው ቤተክርስቲያን እና ቅዱስ ሲኖዶስን ወክለው መግለጫ መስጠት አይችሉም በዚህም ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ከሰሞኑ የሰጡት መግለጫ በግላቸው የሰጡት እንጂ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አይደለም” ብለዋል በጉዳዩ ዙሪያም በቀጣዩ በካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ በአጀንዳ የሚነጋገርበት መሆኑንም ጭምር አስረድተዋል።

“ቅዱስ ፓትሪያርኩ የሰጡት መግለጫ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ያለመሆኑን እየገለጽን ይህንንም የዓለም መንግሥታት በሃገር ውስጥ እና በውጭ ያላችሁ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግሥት ሊያውቁት እና ሊገነዘቡት ይገባል” ብለዋል።

“በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ችግር ሲፈጠር ቅዱስ ሲኖዶሱ ተወያይቶ መግለጫ ሲሰጥ ቆይቷል፤ እየሰጠም ነው፤ እርዳታም ተደርጓል” ሲሉ የተናገሩት የሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ፡፡ አቡነ ማትያስ ተናገሩት ተብሎ በማኀበራዊ መገናኛዎች የተሰራጨው ንግግር ቅዱስ ሲኖዶሱ ያልተወያየበት እና ያልወሰነዉ ጉዳይ በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶሱን የማይወክል ሀሳብ ነዉ ብለዋል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያም በቀጣዩ በካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ በአጀንዳ የሚነጋገርበት መሆኑንም ጭምር አስረድተዋል።

Exit mobile version