ቅዱስ ሲኖዶስ ኢትዮጵያን በተዘዋዋሪ ለቅኝ ግዛት ማመቻቸትን አወገዘ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለአራት ቀናት ያካሄደውን የግንቦት ርክበ ካህናት ጠናቀቀ። ኢትዮጵያን ከጎረቤት አገራትን በጠላትነት ማነሳሳት በተዘዋሪ ተቅኝ ግዛት እንደሆነ አመልክቶ አወገሸ።

ባለ 12 ነጥብ የውሳኔ መግለጫ በማውጣት የተጠናቀው ጉቤል ህዝብ በአንድነት እንዲቆም ጠይቋል። ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ጉባኤው ስለሀገር ደህንነትና ስለህዝቦች አንድነት በመምከር፣ ከቀያቸው ስለተፈናቀሉ እና ለስደት የተዳረጉ ዜጎች፣ በተለያዩ አካባቢዎች እየታዩ ስላሉ አለመግባባቶች በመነጋገር ችግሮች በመግባባት ውይይትና ይቅርታ መፍታት እንደሚገባ አመልክቷል።ከሁሉም በላይ ወደ ፈጣሪ በመጸለይ ምሕረት መጠየቅ እንደሚያስፈልግ ተቀብሎ በተግባር እንዲውል ተስማምቷል።

በመግለጫውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀዳማዊ ፓትሪያሪክ አቡነ ማትያስ «በአሁኑ ጊዜ አንዳንድ የውጭ ሃገራት ከሩቅ እና ከቅርብ ግንባር በመፍጠር በሀገራችን ሕልውና ላይ እያደረጉት ያለው ጣልቃገብነት ሀገራዊ የመልማት ፍላጎታችንን ለመግታት፣ ዳርድንበራችንን ለመድፈር እያደረጉ ያለውን ሙከራ ጎረቤት ሃገራት ጭምር በጠላትነት እንዲነሳሱብን እያደረጉት ያለው ቅስቀሳ ተዘዋዋሪ ቅኝ ግዛት በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ተቃውሞታል ሲሉ ተናግረዋል።

ሕዝባችንም ከምንግዜውም በላይ በተለየ መልኩ ሀገራዊ አንድነቱን በመጠበቅ ሀገሪቱን ከውጭ ወራሪ በመከላከል ሀገራዊ ልማትን በማፋጠን የበኩሉን እንዲወጣ ጉባኤው ጥሪውን አቅርቧል። ከዚህም ሌላ የቤተክርስትያኗ የአምልኮ ስፍራ የሆኑት መስቀል አደባባይ እና ባሕረ ጥምቀት መንግሥት  ልዩ ጥበቃና እንክብካቤ እንዲያደረግላቸው ጉባኤው በጥብቅ አሳስቧል። ጉባዔው በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት እራሳቸውን በራሳቸው ጳጳስ እና ፓትርያርክ አድርገው የሾሙ ሦስት አገልጋዮችንም አውግዟል።

ቅዱስ ሲኖዶስ አቡነ ማቲያስ የኢትዮጵያን መንግስት ለይተው ጥፋተኛ በማድረግ ስለሰጡት መግለጫ ምን እንደተነጋገረና እንደወሰነ አልታወቀም። ወይም ብበግልጽ የተባለ ነገር የለም። አቡነ ማቲያስ መንግስት ጄኒሳይድ ፈጽሟል በሚል ከሰው የዓለም ህብረተሰብና ታላላቅ አገሮች ጣልቃ እንዲገቡ ጥሪ አድርገው በነበረበት ማግስት ከሲኖዶስ አባላት ቅሬታ ቀርቦባቸው ነበር። እንደ መንፈሳዊ አባት ሁሉንም እኩል አለማየታቸው አግባብ እንዳልሆነ ጠቅሰው ጉዳይ በሲኖዶስ ጉባኤ እንደሚነሳም ተመልክቶ ነበር።

በወቅቱ እሳቸውን ትክክል ናቸው በሚል 360 እና ሌሎች ደግፈዋቸው ነበር። አሁን ሲኖዶስ ጉቤውን ሲያጠናቅቅ አገርና ህዝብን አስቀድመው መግለጫ መስጠታቸው፣ ብሎም ሲኖዶስ በወሰነው መሰረት የውጭ አገር ጣልቃ ገብነትን ማውገዛቸው በደጋፊዎቻቸው ዘንዳ ደስታን አልፈጠረም።


Leave a Reply

%d bloggers like this: