ETHIO12.COM

በሀይማኖት መካከል ግጭት እንዲነሳ የሚቆሰቁሱ ሃይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የሲቪክ ማህበራት ጠየቁ



በሀይማኖት መካከል ግጭት እንዲነሳ የሚቆሰቁሱ ሃይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሶስት የሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች በጋራ ባወጡት የአቋም መግለጫ አሳሰቡ፡፡

አገራዊ፣ ህዝባዊ እና ወቅታዊ ሁኔታዎችን በማስመልከት ኢትዮጵያ ትቀጥላለች፣ ዓለም ዓቀፍ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ እና ኦሞ ኢትዮጵያ አንድነትና ፍትህ ማዕከል የሲቪክ ማህበራት በጋራ በመሆን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም በለውጡ ያልተደሰቱ የውጭና የውስጥ ሃይሎች ግንባር ፈጥረው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎልና አገራዊ ምርጫውን ለማደናቀፍ አሉታዊ እርምጃ ሲወስዱ መቆየታቸውን ገልጿል።

በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ውድድር ተሸናፊነታቸውን አረጋግጠው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም በተጻራሪ በመቆም ባንዳነታቸውን በገሃድ ማስመስከራቸውን መገንዘቡንም አመልክቷል።

(ኢ ፕ ድ)

Exit mobile version