Site icon ETHIO12.COM

የ26 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሎቶሪ አሸናፊዋ ያልተጠበቀ ገጠመኝ

በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ከተማ የ26 ሚሊየን ዶላር የሎተሪ ዕጣ ባለዕድለኛ የሆነችው ሴት ዕድሏን ከልብስ ጋር በማጠቧ ምክንያት የዕድሉ ተጠቃሚ ሳትሆን መቅረቷ ተዘገበ፡፡

የሎተሪ ዕጣው ባለዕድለኛ ሰው ገንዘቡን መረከብ የነበረበት የመጨረሻ ቀን ትላንት ሐሙስ የነበረ ሲሆን፤ ቀደም ባለው ቀን ረቡዕ አንዲት ሴት ወደ ሎተሪ ሽያጭ ቢሮ በመምጣት ዕድለኛ የሚያደርጋትን ቲኬት ከልብሶች ጋር እንዳጠበች ለሽያጭ ሰራተኞች መግለጿ ተነግሯል፡፡

ዕድለኛዋ የሎተሪ ቲኬቱን ውስጥ ሱሪዋ ውስጥ አስቀምጣው እንደነበርና በስህተት ከልብስ ጋር ማጠቧን መግለጿን ኢስፒሬንዛ ሄርናንዴዝ የተባለች የድርጅቱ ሰራተኛ ለኋይተር ዕለታዊ የዜና ምንጭ መናገሯን ዘገባው አስነብቧል፡፡

ዕድለኛ ያደረጋትን የሎተሪ ቲኬት በውስጥ ሱሪዋ ውስጥ አስቀምጣው የነበረ መሆኑንና ከሌሎች ልብሶች ጋር በልብስ ማጠቢያ ማሽን ውስጥ በማስገባቷ ምክንያት ቲኬቱ መበላሸቱም ተጠቅሷል።

ባለዕድለኛዋ ሴትቲኬቱን መግዛቷን የቪዲዮ ማስረጃ ማመላከቱ እና የሽያጭ ሰራወተኞችም እንደሚስታውሷት የድርጅቱ ሀላፊ መናገራቸውን እና መረጃዎችም ወደ ካሊፎርኒያ የድርጅቱ ዋና ቢሮ መላኩ ተዘግቧል፡፡

የቀረበው ቅሬታ በምርመራ የሚጣራ መሆኑን ነገር ግን ምርመራው ውጤታማ እንዲሆን ቅሬታ አቅራቢ ሰዎች የጠፋው ቲኬት የእነሱ ስለመሆኑ የሚያመለክት የቲኬቱ የፊት ወይም የጀርባ ምስል በፎቶ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ የድርጅቱ ቃል-አቀባይ ካቲ ጆንስተን ተናግረዋል፡፡

26 ሚሊየን ዶላር አሸናፊ የሚያደርገው የሎቶሪ ቲኬቱ ቁጥር 23, 36, 12, 31, 13, እና የማስተዛዘኛ ቁጥሩም 10 እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፤ ባለቤት ካልቀረበ 19.7 ሚሊየን ዶላሩ በካሊፎርኒያ ከተማ ለሚገኙ የህዝብ ትምህርት ቤቶች የሚሰጥ መሆኑንም ኤቢሲ ኒውስ ዘግቧል።

በኢትዮጵያም በርካታ ሰዎች የሎቶሪ ቲኬት በመግዛት የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን ጥረት እንደሚደርጉ ይታወቃል፡፡

የሎተሪ ቲኬት የሚገዙ ሰዎች መሰል አሳዛኝ ገጠመኝ እንዳይከሰት በሎተሪ ቲኬት አያያዝ ላይ ተገቢውን ጥንቃቄ ቢያደርጉ መልካም ይሆናል፡፡ via (ኢዜአ)

Exit mobile version