Site icon ETHIO12.COM

የሲኤንኤን ዘጋቢ ኒማ- በተወነችው ተውኔት ውስጥ ዳግም ሞት የተፈረደባቸው ዜጎች

“ሁለት ጉዳዮች ወለል ብለው ይታያሉ” ዋሲሁን ሰማን። ጋዜጠኛዋ መሰረቷ ከሱዳን ነው። የምትኖረውና የተማረችው እንግሊዝ ነው። እነዚህ ሁለት ጉዳዮች አያይዞ ለሚያየው የኒማ ኢልባጊር ዘገባ መነሻና መድረሻ ይገባዋል። ይህ ሊደበቅ የማይችል ጉዳይ ነው።

ሲታሰርና ሲፈታ ከነበረው ጋዜጠኛ አባቷና የመጀመሪያ አሳታሚ ከነበረችው እናቷ ሱዳን የተወለደችው ኒማ አልባጊር ተቀማጭነቷ ሎንዶን የሆነ የሲኤኔን ሪፖርተር ነች።

ኒማ ሰሞኑንን እንደ ፊልም አክተር “ ጋዜጠኞች ነን፣ ፈቃድ አለን…” እያለች ከመከላከያ አባላት ጋር የነበራትን ግንኙነት በፊልም እያሳየች በአክሱም ተፈጸመ ያለችውን የዘጠኝ ደቂቃ ትረካ አቅርባለች። በዘገባው የኤርትራ ወታደሮችን ናቸው ያለቻቸውን አሳይታለች።

ኒማ ጎበዝ ጋዜጣኛ እንደሆነች የሚነገርላት ናት። ያለ ፍርሃት በግጭት ቀጠና ውስጥ ገብታ መስራቷ ያስመሰግናታል። በዚህ መመዘኛ ትግራይ ገብታ መዘገቧ ደግ የሚባል ሲሆን፣ ከሁሉም በላይ እዛ እንደትገባ የፈቀደላትም መንግስት ሊመሰገን ግድ ነው። ይህንን ሁሉ ብለን ዘገባዋን ስንመለከተው ኒማ ሰባራ ሆና አግኝተናታል።

ለውጭ አገር ሚዲያዎች በአስተርጓሚነት የሚሰራና በተመሳሳይ የሚሰሩ ኤትዮጵያዊያንን የሚያውቅ ምስክርነቱን እንደሰጠው ከሆነ የሲኤን ኤን ጋዜጠኞች ኢትዮጵያ ከገቡ በሁዋላ የትህነግ ሃይል ከፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ የተረፉ የመከላከያ አባላትን አነጋገረዋል።

አዲ አቦ ትግራይ ኖቬምበር 4 ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ስለነበረው፣ ማን ምን እንዳደረገና እንዴት ጦርነቱ እንደተነሳ ነዋሪዎችን አነአገረው እውነቱ ተነግሯቸዋል። የመጨረሻዋን አውሮፕላን ይዘው ብር ለማስረከብ ትግራይ የገቡ ወገኖች ምን እንደገጠማቸውና በማን ትዕዛዝ ያ ሁሉ ጉዳይ እነድተፈጸመ ቃል በቃል ኢንተርቪው አድርገው መረጃ ይዘዋል።

በሆስፒታልና ማገገሚያ ያሉ ወገኖችን አግኝተው አነጋገረዋል። ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊትና ከተጀመረ በሁዋላ ምን እንደሆነ የትግራይ አዛውንቶች ምስክርነት ሰጥተዋል። ሚዲያው ይህንን ሁሉ መረጃ ሰብስቦ ያቀረበው ግን ኒማ የምትተውንበትን ለዘመቻቸው የሚመቻቸውን የ9 ደቂቃ ሪፖርት ብቻ ነው። ለምን?

ለሲኤን ኤን ቃላቸውን ከሰጡ አንድ ዜጋ አንደበት እንደሰማነው በሲቪሊያን ወይም ወታደር ባልሆኑ ላይ መንግስትና የኤርትራ ጦር እርምጃ ይወስዳሉ በሚል ለተነሳው ሃሳብ በቂ ምላሽ አቅርበዋል። መላሹ የመቀሌ ነዋሪ ሲሆኑ ስልጣን ላይ ያሉ ሰው አይደሉም።

“የመንግስት ሰራዊት መታወቂያ አለው፤ መለያ ልብስና አድራሻ አለው” ሲሉ ጀመሩ ቀጥለውም “ የትህነግ ሃይል ሲፈልግ ሲቪል፣ ሲፈልግ ወታደር ይሆንና ይዋጋል። መታወቂያና መለያ የለውም። ይህ ሃይል ሲተኩስና ሲመታ ሲቪሎች አለቁ ትላላችሁ። እስኪ እንዴት ይለያል? ደሞስ ሲቪል የለበሰ ሲገድል መከላከያ ዝም ብሎ ይሙት?…” በሚል ኒማ ቀርጻለች። ሰምታለች። ግን የዘገባዋ አካል አላደረገችውም?

አዲ አቦ አካባቢ ነዋሪዎችን ሲያነጋገሩ ለዚህ ሁሉ ችግር ዋንኛ ተጠያቂ ማን ሊሆን እንደሚችል በሚያስረዳ መልኩ መረጃ ያገኘው ሲኤን ኤን ከዚህ ድንበር ላይ ያለው ወታደር በድንገት ሳያስበው ጥቃት ሲፈጸምበት ናሲመታ የኤርትራ ሰራዊት እንደገባ ገልጸዋል። ከዛ በፊት የኤርትራ ወታደሮች ወደ ክልሉ ብቅ ብለው እንደማያውቁ አብራርተዋል።

ይህ ብቻ አይደለም የአገር ሽማግሌዎችና እናቶች ለሽምግልና ትግራይ ሄደው ምን እንደተባሉ ለኒማ አስረድተዋታል። ግን የዘገባዋ አካል አላደረገቸውም።

ሱዳናዊቷን ኒማ በአክሱም የተወነችው ትወና የሚሆነው ይህንን ሁሉ ሃቅ ወደሁዋላ አድርጋ ኢትዮጵያ ላይ ለተከፈተው የተባበረ ዘመቻ ማቀጣጠያ የሚሆን ሪፖርት አቅርባለች። “በዘገባዋ ያላካተተቻቸው ዜጎች ከሞት ትርፈው ዳግም ሞት የተፈረደባቸው ዜጎች ናቸው” ሲል ታዛቢው ግልጿል። ከቢላና ጥይት የተረፉ ወገኖች ፍትህ ይመጣል፣ እውነቱ ይገለሳል፣ ዓለም በመከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈጸመውን ግፍ ባይክድም በሚገባ ይረዳል የሚል እምነትም ነበራቸው። መንግስትም እስኪ ጉዳዩን ከስሩ መርመሩ ብሎ ነበር ይህንን ሁሉ ያመቻቸው። ለዚህ ይመስላል አሜሪካ ኤምባሲ ድረስ ሄደው አቤቱታ ያቀረቡት። ሲኤን ኤን የተሟላ ሪፖርት እንደሚያቀርብ ምሎ ሲያበቃ ይህን መፈጸሙ ህዝብ ኢትዮጵያ ላይ ምን እየተከናወነ እንደሆነ እንዲረዳ ጥሩ አጋጣሚ ሊሆን እንደሚችልም ዜናውን ያጋራን ገልጿል።


Exit mobile version