የፀጥታው ምክር ቤት መደበኛ ያልሆነ ውይይት ለስድስተኛ ጊዜ ከሽፏል!

በኢትዮጵያ ላይ እርምጃ ለማስወሰድ በአየርላንድ ጠሪነት የተካሄደው የፀጥታው ምክር ቤት መደበኛ ያልሆነ ውይይት ለስድስተኛ ጊዜ ከሽፏል! ዛሬም የጠላቶቻችን ሴራ ከሽፏል ሃዘን እና እሮሮ በጠላት መንደር ይሰማል

በአየርላንድ የተጠራው መደበኛ ያልሆነው እና ለስድስተኛ ጊዜ የተካሄደው የፀጥታው ም/ቤት ስብሰባ ትላንት ማክሰኞ በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመወያየት ቢቀመጥም ራሽያ እና ቻይና ጉዳዩን በማጣጣላቸው (ridicule) በኢመደበኛ ውይይት ብቻ ተወስኖ ለፐብሊክ አጀንዳነት እንኳን ሳይበቃ በአጭሩ አስቀርተውታል

በተመድ የአየርላንድ አምባሳደር ጄራልዲን ባይረን በሰጠው መግለጫ “የትግራይ ህዝብ በረሃብ እየተጎዳ ስለሆነ መዘግየት አንችልም:: ከዚህ በኋላ ህይወት እንዳይጠፋ ማረጋገጥ አለብን” በማለት ወትውቷል:: በተመድ የእንግሊዝ አምባሳደር ባርባራ ውድዋርድ ተመሳሳይ ክስ ያቀረበች ሲሆን “ሰው ሰራሽ ረሃብ” በሚል በማስረጃ ያልተደገፈ ሃሜት አቅርባለች::

ተሰናባቹ የተመድ የእርዳታ ሀላፊና የቴድሮስ አድሃኖም ጓደኛ የሆነው ማርክ ሎውኮክ በበኩሉ ለ15ቱ የፀጥታው ምክር ቤት አባላት በግል መግለጫው ስለ ትግራይ ቀውስ ከተረከ በኃላ የኤርትራ ወታደሮች ካልወጡ ትግራይ ከ1977ቱ ድርቅ የከፋ ችግር ይከሰታል ሲል አቅርቧል:: ለዚያውም ባልተጣራ መረጃ የአንድ ወገን ክስ አውርቷል::

አምባሳደር ዛንግ ጁን

በምክር ቤቱ ውይይት የተሳተፉት በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ የኤርትራ መውጣት “አንዳንድ የቴክኒክ እና የአሰራር ጉዳዮችን የመለየት ጉዳይ ነው የቀረው” በማለት የሎውኮክን ክስ ቀዝቃዛ ውሃ ቸልሰውበታል – አክለውም የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ያልተገደበ የእርዳታ ተደራሽነትን እንደፈቀደ ፣ ሁኔታውን ለማሻሻል ቁርጠኛ መሆኑን ፣ የሰብዓዊ ድጋፉ እንደቀጠለና ምርመራም እየተካሄደ መሆኑን ገለፀው ድጋፍ እያደረገ ላለው የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ምስጋና አቅርበዋል!!!

ጥበበኛው አምባሳደር ታዬ አክለውም: “…. የትግራይ ሁኔታ የዚህን ያህል የፀጥታው ም/ቤትን ብዙ የሚያሳስብ ጉዳይ አይደለም” በማለት ምዕራባዊያኑ በተለይም አሜሪካ አየርላንድና እንግሊዝ የትግራይ ጉዳይ አሳስቧቸው ሳይሆን ፖለቲካዊ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ነው የሚል አንድምታ ያለውን ሃሳብ በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ አጋልጠዋል!!!!

በመጨረሻም በኢትዮጵያ ላይ እርምጃ ለማስወሰድ ለስድስተኛ ጊዜ የተካሄደው የፀጥታው ምክር ቤት መደበኛ ያልሆነ ስብሰባ በዋናነት ራሽያ እና ቻይና ውድቅ በማድረጋቸው እና አምባሳደር ታዬም በበቂ ሁኔታ ከሳሾቻችንን በመሞገታቸው ሳቢያ ውይይቱ እንኳን ጆይንት ስቴትመንት ሊወጣበት ቀርቶ ጭራሽ ለፐብሊክ አጀንዳነት (በመደበኛ ስብሰባ ሊታይ እንኳን የማይበቃ) ሳይሆን ቀርቷል!!!!!

ይህን አስመልክቶ ሮይተርስ “የምእራባዊያኑ የፀጥታው ም/ቤት አባላት በኢትዮጵያ ጉዳይ ከሩሲያና ቻይና ጋር ተፋጠዋል!!” ሲል ዘግቦታል! https://www.reuters.com/…/ethiopia-un-envoy-says…/#አዎ! ኢትዮጵያ ብቸኛ አይደለችም!!! ጠላት አይሳካለትም!! ራሽያና ቻይና ስለ ኢትዮጵያ ግንባራቸውን ሰጥተዋል!!!! ያሰቡትንም አድርገዋል!!!!!በዚህም ሳቢያ የጠላቶቻችን አከርካሪ ተሰብሯል!!!! በተመድ የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ብሶቷን እና ንዴቷን መቋቋም አቅቷት “የፀጥታው ምክር ቤት በትግራይ ዙሪያ አሁንም ክፍት ክርክር አላደረገም” ስትል እዬዬዋን አስነክታዋለች!!!!

ለጁንታው ደጋፊዎች ቃል ገብታ ወደ ስብሰባው የገባችው የእንግሊዝ አምባሳደር ባርባራም ስላልተሳካላት ከዚያ ወዲያ ድምጿ የለም!!!! የቴድሮስ ቅጥረኛ የሆነው ሎውኮክ ቅስሙ ተሰብሯል!!! ከዚያ ወዲህ ትንፍሽ ማለት አልቻለም!!!! የቴድሮስ ተላላኪ የሆነው ፕሮፌሰር ማኩሽ ካፒላ ድንኳን ጥሎ ተቀምጧል! የጁንታው ደጋፊ ካሚሮን ሁድሰን የፀጥታው ምክር ቤትን በንዴት ዘልፏል

አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ

ብቻ ሁሉም ጠላቶቻችን በልብ ስብራት እና በሞራል ውድቀት እንክትክታቸው ወጥቷል! ሳማንታ ፓወር ከባለፈው የቡድን ሰባት ሃገራት ስብስባ ወዲህ አቅሏን በመሳቷ የትግራይን ጉዳይ “ውሾን ያነሰ ውሾ” ብላ ትታዋለች! ጨዋታዋ ስለ ጓቲማላ ሆኗል! ሱዳናዊቷ የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ኒማ ኢልባጊር እሷም እንደ ሳማንታ ፓወር ቀልቧ ተገፎ ከ ጂ7 ስብሰባ ወዲህ ስለ ትግራይ እርም ብላለች!!! እነ ማርቲን ፕላውት ዝብርቅርቅ ብሎባቸዋል!!

ቢቢሲ ተራ ሃሜት ውስጥ ተዘፍቋል!!!! ዶክተር አብይን በመስደብ ዋንጫ ሊያነሳ ይጣጣራል!!! ዋሽንግተን ፖስት አሉቧልታ ብቻ ሆኗል!!!! ሁሉም ተስፋ ቆርጠዋል!!!! አዝነዋል ተክዘዋል!!!! በጠላት መንደር ጫጫታ ዋይታ ለቅሶ ጥርስ ማፋጨት መኪና መስበር መስታውት ማድቀቅ ቁዘማ እና ምሬት እጣ ፈንታቸው ሆኗል!!!!! ሃቅን እና ፈጣሪን የያዘችው ኢትዮጵያም በተራዋ መሳቅ ጀምራለች!!!!! ሳቋም ፍፁም ይሆናል!!!! ምንም ማድረግ አይቻልም!!!! ጊዜው የኢትዮጵያ ነው!!!! በተመድ የራሽያ አምባሳደር ዲሚትሪ ፖሊያስኪይ በተመድ የቻይና ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ዛንግ ጁን እንወዳችኃለን!!!!!

የኢትዮጵያ ልጅ አምባሳደር ታዬ እንኮራብሃለን በርታልን! ታላቅ ምስጋና ለአባት ሃገር ራሽያ!!!! ታላቅ ምስጋና ለወዳጅ ሃገር ቻይና!!!! ምስጋናችን ብዙ ነው!!!!! በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የዋላችሁትን ውለታ ኢትዮጵያ አትረሳውም!!!!!! ኢትዮጵያ ዛሬም አሸንፋለች!!!! ፈተናዎችን እያለፈች እስከመጨረሻው በድል ትቀጥላለች!!!! ፈጣሪ ይክበር ይመስገን!!!!! ብራቮ! ብራቮ! ብራቮ ኢትዮጵያ!!!!!!

BY Dejene Assefa FB

Leave a Reply