Site icon ETHIO12.COM

“የናይል ንስር” የግብጽ ባታሊዮን ጦር ሱዳን ገባ-ኢትዮጵያዊያን በአርበኝነት ስሜት ውስጥ ናቸው

ቀደም ሲል ” የናይል ሰይፍ “፣ባለፈው ኖቬምበር የግብፅ እና የሱዳን ኮማንዶ ክፍሎች እና የአየር ኃይሎች “አባይ ንስሮች 1” የሚል ስያሜ የተሰጠው ወታደራዊ ልምምድ አድርገው ነበር። ይህ ኢትዮጵያን ዒላማ አድርጎ የተደረገው ልምምድ በ2019 ኦማር አልበሽር ከተወገዱ በኋላ የተደረገ የሁለቱ አገራት የመጀመሪያው የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ነው።

ኤቢሲ የተሰኘው የዜና ወኪል የሱዳን የመንግስት መገናኛዎችን ጠቅሶ እንዳለው ከሆነ ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የግብጽ ባታሊዮን ጦር ሱዳን ገብቷል። ቀጣዩ ሃይልም ወደ ሱዳን በባህር ከነ ሙሉ ትጥቁ እንደሚገባ አስታውቋል።

ይህ የሆነው “በመጋቢት ወር የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ኤል ሲሲ ሀገራቸው በናይል ውሃ ድርሻዋ ላይ ከቶውንም “የማይነካ” መሆኑን በማስጠንቀቅ ኢትዮጵያ ያለዓለም ዓቀፍ ስምምነት ግድቧን ብትሞላ በአካባቢው “ማንም ሊገምተው በማይችል ደረጃ አለመረጋጋት ውስጥ እንደሚወድቅ ካስተነቀቁ በሁዋላ ነው።

አልሲሲ ” የማይነካ ” በሚል የአገራቸውን ተጠቃሚነት በማስቀደም ኢትዮጵያን ሱዳንን በመጠቀም ለማስፈራራት ቢሞክሩም፣ የጦር ሃያላቸውን በልምምድ ስም ቢልኩም ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ሁለተኛው የውሃ ሙሌት በተያዘው እቅድና ሶስቱ አገሮ በባለሙያዎች ቀርቦላቸው በፈረሙት ውል መሰረት እንደሚከናወን ይፋ አድርጋለች። እንደ ግብጽ ሁሉ ኢትዮጵያም ” በብሄራዊ ጥቅሜ አልደራደርም፤ ፍትሃዊ ጥቅሜን ከማስተበቅ የሚከለክለኝ ምድራዊ ሃይል የለም” እያለች ነው። ግድቡም ሰማኒያ በመቶ እንደተጠናቀቀና የሙከራ ምርት በክረምቱ እንደሚጀመር ይፋ አድርጋለች።

ይህንን ተከትሎ “የናይል ተከላካይ ንስሮች” በሚል ስያሜ ሲሰለጥኑ የነበሩ ወታደሮቿን ወደ ሱዳን ልካለች። የግብጽ የጦር መኮንኖች ካርቱም ሲደርሱ የሚያሳይ ምስል ተደግፎ ይፋ የሆነው ዜና ምን ያህይል ሰራዊት እንደገባና እንደሚገባ ይፋ ባያደርግም አስራ አንድ ሺህ እንደሚደርስ አንዳንድ ምንጮች እየጠቆሙ ነው።

ቀደም ሲል ለወታደራዊ ልምምድ ሱዳን ገብቶ የነበረው ” የናይል ሰይፍ ” የተሰኘው ሃይል ልምምዱን ከቸረሰ በሁዋላ ሱዳን እንደሚገኝ መረጃዎች አሉ። የኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር አካባቢ ነዋሪ የሆኑናና ንብረታቸውን የተዘረፉ ቀደም ሲል ለቪኦኤ ሲናገሩ ካምፖች መሰራታቸውንና እጅግ ታዳጊ የሆን ግብጻውያን ወታደሮች ማየታቸውን ተናግረው እንደነበር ይታወሳል።

ሱዳን የቤኒሻንጉልንና የትህነግ ሰራዊት በማስለተን ወደ ኢትዮጵያ ሰርገው እንዲገቡ በተደጋጋሚ ሙከራ ማድረጉ፣ በርካቶች ሰርገው ለመግባት ሲሞክሩ መደምሰሳቸውና መማረካቸውን መንግስት ሲያስታውቅ ቆይቷል።

የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዋና አዛዥ ብ/ጄ/ ይልማ መርዳሳ በተደጋጋሚ ቢናገሩም በቅርቡ የተወካዮች ምክር ቤት አየር ሃይልን በጎበኘበት ወቅት ” በህዳሴው ግድም ሆነ በአጠቃላይ የአገሪቱ ክልል አንድም የጠላት ሃይል ስጋት ሊጥል እንደማይችል ማረጋገጥ እወዳለሁ” ሲሉ መናገራቸው አይዘነጋም። በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የበረራ ማዕቀብ መጣሉንና ያለ ኢትዮጵያ ፈቃድ አካባቢው ዘንድ የሚመታ ካለ ከመድረሱ በፊት እርምጃ እንደሚወሰድበት አስተንቅቀም ነበር።

በአካባቢው የተሰማራውን ልዩ ሃይልና የመከላከያ ሰራዊት የሚመሩ መኮንኖች በበኩላቸው በአካባቢው ያለው እንቅስቃሴ ሁሌም በቁጥጥር ስር መሆኑንና ሰራዊቱ ግድቡን እንደ ዓይኑ ብሌን እንደሚጠብቀው መግለጻቸው አይዘነጋም።

የሱዳን የጦር መሪዎች ጦርነት እንደማይፈልጉ በተደጋጋሚ ቢናገሩም ከግብጽ በወሰዱት ተልዕኮ አማካይነት ወረው ከያዙት መሬት በተጨማሪ በየጊዜው ትንኮሳ እንደሚያደርጉ ከአካባቢው መረጃዎች እየወጡ ነው። መንግስት በትግራይ ከጀመረው የህግ ማስከበር፣ በየአካባቢው ከሚታዩት “የተላላኪዎች” ረብሻ አንጻር ሱዳን ላይ ተዕግስት መምረጡ እንደታክቲክ ትክክለኛ መሆኑንን ምሁራንና ፖለቲከኞች ይናገራሉ። አቶ ልደቱ አያሌው ብቻ ነበሩ በልብ ህመም እየተሰቃዩ እርምጃ መውሰድ አለበት ሲሉ የተደመጡት።


Exit mobile version