የአብደላህ ሃምዶክ ነገር እና የሃሙሱ የካይሮ ጥሪ

ባለፈው ቅዳሜ የግብፁ ኘሬዝደንት አብዱልፈታ አል ሲሲ ለይፋዊ ጉብኝት ሱዳን መጓዛቸው ይታወሳል።
ቆይታቸው በሁለት ምክኒያት እንዳሰቡት አልነበረም።

▪አንዱ፦ በሱዳን ወታደራዊው ክንፍ እና በሲቪል አስተዳደሩ ሃላፊዎች ያለው ልዩነት ነው። አልሲሲ ለግብፅ ጥቅም ሱዳንን ለመማገድ የነደፋትን ሃሳብ ከሲቭል አስተዳደሩ የተጠበቀዉን ያህል ድጋፍ አላገኘም። ወትሮም የግብፅ ምስለኔ ወታደራዊ ቡድኑ በመሆኑ አልሲሲ በካርቱም ቆይታቸው ምክክር ያደረጉት ከአብዱልፈታ አልቡርሃን ጋር ነበር። ጠ/ሚር ሃምዶክ ጋር ምንም የተወያዩት ነገር አልነበረም።

▪ሁለት፦ በሱዳን ሙሁራን፣ጋዜጠኞች እና የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች የተጠራው ተቃውሞ ከተገመተው በላይ በካርቱም ውጥረትን ፈጥሮ ነበር። ሁኔታው ከሃገሪቱ አጠቃላይ የፀጥታ ችግር ጋር ተዳምሮ አደጋ እንዳያመጣ ተሰግቶ አል ሲሲ በቂ ውይይት ሳያደርጉ እንዲመለሱ አስገድዷቸዋል።

በአሁኑ ሰአት የሱዳን ወታደራዊ ቡድን (አል ቡርሃን) የሲቪል አስተዳደሩን ደፍቆ ስልጣኑን በሙሉ በሚባል ደረጃ ጨብጧል፥ በሁለቱ ሃይሎች መካከል ፍትጊያ እና ቅራኔ እየሰፋ መጥቷል። ይህም ለግብፅ ተልዕኮ መሳካት ጋሬጣ ስለሆነ በመጪው ሃሙስ ጠ/ሚር አብደላ ሃምዶክ ወደ ካይሮ ” እንዲመጡ” በጉብኝት ስም ቀጭን #ትዕዛዝ” ደርሷቸዋል።

የካይሮው ጥሪ አላማ ጠ/ሚ ሃምዱክ የሚመሩት ቡድን በህዳሴ ግድብ እና በድንበር ጉዳይ እንደ ወታደራዊ ክንፋ የግብፅን ሃሳብ እንዲቀበል እና ያለማንገራገር እንዲፈፅሙ ለማግባባት ካልሆነ ለማስፈራራት ነው።
ከሲቪል አስተዳደሩ ባለስልጣናት ውስጥ የው/ጉ/ሚኒስትሯ አስማ ሞሀመድ አብደላ አፍቃሪ ግብፅ እንደሆኑ ይነገራል። አስማህ የግብፅ መንግስት ያሳደረው ውስጣዊ ጫና ተጨምሮበት ነው በቅርቡ በተዋቀረው ካቢኔ ውስጥ የውጭ ጉዳይ ስልጣንን እንዲጨብጡ የተደረገው። አካሄዱ የሽግግር መንግስቱን በፀረ ኢትዮጵያ አቋም ባላቸው ሰዎች የበላይነት ውስጥ እንዲወድቅ ማድረግ ነበር።

በዚህም መሰረት የጦር ሰራዊቱን በአል ቡርሃን፣ ዲኘሎማሲውን ደግሞ በአስማ ሞሃመድ እያሾፈሩት ነው፤ ግብፆቹ።

ባለፋት አስር ቀናት ብቻ ከአልሲሲ በተጨማሪ የግብፅ ጦር አዛዥ ካርቱም በማምራት የጦር ትብብር ስምምነት የፈፀሙ ሲሆን የሱዳን ው/ጉ ሚኒስትር ደግሞ በካይሮ ጉብኝት አድርገዋል።

ግብፅ እና ሱዳን ኢትዮጵያን እና ምስራቅ አፍሪካን ለማወክ ሽርጉዱን በጥምረት በብዙ ግንባር እያካሄዱ ነው።
በወታደራዊ ፣ በሚዲያ እና በዲኘሎማሲው መስክ ግልፅ ዘመቻ ላይ ናቸው። የሚረጩት ግጭት ቀስቃሽ ፣መርዛማ የሃሰት መረጃዎች እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አይደለም።

ዛሬ ይህን አወሩ ….
~~
የኢትዮጵያ መንግስት በሱዳን ብሉ ናይል ግዛት ለሚንቀሳቀሰው የሱዳን ህዝብ ነፃነት ንቅናቄ ( SPLM-N) የትጥቅ ድጋፍ እንዳደረገ የሱዳን ብሄራዊ የዜና ወኪል ሱና ዘገበ የሚል ወሬን የግብፁ አል አህራም አሰራጭቷል።

የትጥቅ ድጋፋ ታጣቂ ቡድኑ ኩምሩክ የተሰኘ ከተማን እንዲቆጣጠር እና በአል ፋሽቃ ያለውን የሱዳን ሰራዊት ለማዳከም ያለመ ነው ይላል ዜናው።

የሳኡዲ አረቢያው አሽራቅ #Ashraqnews ግን ስሙ ያልተገለፀ የታጣቂ ቡድኑን ሃላፊ ጠቅሶ ወሬው ፍፁም #ሃሰት መሆኑን አስታውቋል።

ፀብ ያለሽ በዳቦ አደረጉት !!

Via Selam Mulugeta

Leave a Reply