Site icon ETHIO12.COM

37 ሺ በሚሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ሙከራ ተደረገ

በኢትዮጵያ በሚገኙ 37 ሺህ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ይፋ አድርጓል፡፡

ተቋሙ ባወጣው መረጃ “ሳይበር ሆርስ ግሩፕ” የተሰኘ የመረጃ ሰርሳሪ ቡድን አዲስ የኮምፒውተር ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ኮምፒውተሮች ላይ ለመልቀቅ ዝግጅት ማድረጉ ተደርሶበታል፡፡

ይህ ቫይረስ “ብላክ ፒራሚድ ዋር” የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን 37 ሺህ በሚደርሱ ኮምፒውተሮች ላይ ማነጣጠሩ ተገልጿል፡፡

ቡድን ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ውሃ ሙሌት ጋር ተያይዞ በተለያዩ የሀገራችን ድረ-ገጾች ላይ የመበርበር ሙከራ ሲያደርግ መቆየቱንም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አስታውቋል።

ኤጀንሲው ለሁሉም የሳይበር ምህዳሩ ተጠቃሚዎች ተገቢውን የሳይበር ደህንነት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ያሳስባል ሲል የዘገበው ኢፕድ ነው።


Exit mobile version