Site icon ETHIO12.COM

ለምርጫና ለሁለተኛው የውሃ ሙሌት መከላከያ ዝግጁ መሆኑ ተሰማ

የአገር መከላከያ ሰራዊት ለምርጫና ለሁለለተኛው የህዳሴ ግድብ ሙሌት እንከን እንዳይፈጠር በጥብቅ ዝግጅት ማድረጉ ተገለጸ። የምድርና የአየር ሃይል አዛዦች በተደጋጋሚ ይህንን ቢሉም ዛሬ በድጋሚ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ይህንኑ አጠንከረው አስታውቀዋል። በምርጫ ዙሪያ ወንጀል የሰሩም ተያዘዋል።

የመከላከያ ሚኒስቴርም ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት የተናገሩት ለአሐዱ ሬዲዮ ነው። 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የመከላከያ ሰራዊት ዝግጅት አድርጓል ነው ያሉት።

” በመላው ሀገሪቱ ወንጀለኛን አድኖ ለመያዝ የመከላከያ ሰራዊቱ ዝግጁ ነው” ሲሉ ያስታወቁት ኮሎኔሉ በተለይ ስለተደረገው ዝግጅት ማብራሪያ አልሰጡም።

ኢትዮጵያ 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ለማካሄድ ቀን መቁረጧ ይታወቃል፡፡ ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ዝግጅት እያደረጉ ስለመሆኑ በየፊናቸው ከሚሰጡት መረጃ ለመረዳት ተችሏል። ብልጽግናም ስብሰባውን ሲያጠቃልል ምርጫው መሰላማዊ እንዲጠናቀቅ፣ ሁለተኛው የውሃ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ አቋም መያዛቸው ይታውሳል። ላለፉት አራት ወራት ቁጥራቸው በውል ያልተገለጸ የፖሊስ አባላት፣ በልዩ ልዩ ስልታዊ ተግባር የሰለጠኑ፣ ከፖሊስ ኮሌጅ የወጡ መኮንኖች በተከታታይ ሲመረቁ በክልል ደረጃም ሰፊ ቁጥር ያለው ሃይል ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል።

በለኢላ የምርጫ ዜና የምርጫ ቅስቀሳ ባነር ወይም የምርጫ ምልክት በመቅደድ የተጠረጠሩ 22 ግለሰቦችን በመያዝ እያጣራሁ ነዉ ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን አስታወቋል።

ስድስተኛዉ ሀገራዊ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ እየሰራሁ ነዉ ያለዉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን የፖለቲካ ፓርቲዎች የቅስቀሳ ባነሮችን ቀደዋል ተብለዉ የተጠረጠሩ 22 ግለሰቦችን መያዙን ገልፃል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ እንደተናገሩት በከተማዋ ስድስተኛዉን ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ የተሰቀሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባነርን በመቅደድ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን መያዙን ገልፀዉ ከነዚህ ዉስጥ በኮልፌ ቀራንዮ አንድ ግለሰብ የ5 ወር እስራት ተፈርዶበታል ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ኮማንደሩ አክለዉም የዘንድሮዉ ስድስተኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ከዚህ በፊት ከተካሄዱ አምስት ሀገራዊ ምርጫዎች የተሻለ እና የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ከዚህ ቀደም ከነበሩ ምርጫዎች በተሻለ የምርጫ ምልክታቸዉን በነፃነት እያስተዋወቁ ነዉ ሲሉ ጨምረዉ ገልፀዋል፡፡


Exit mobile version