ከአማራ ክልል ከተለያዩ ዞኖች በደላሎች ተታለው በህገ ወጥ መንገድ ከሃገር ለመውጣት የሞከሩ 60 ወጣቶች መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የባቲ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር መሃመድ አሊ ለኢዜአ እንደገለጹት ወጣቶቹ ጨለማን ተገን አድርገው ከሃገር ለመውጣት ሲሞክሩ ትላንት ከለሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በባቲ ከተማ ተይዘዋል ።
ወጣቶቹ በህገ ወጥ መንገድ ወደ አረብ ሀገር ለመውጣት የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 43619 አአ በሆነ የጭነት አይሱዙ ተሽከርካሪ ተሳፍረው ከደጋን መስመር ወደ አፋር በመጓዝ ላይ እንዳሉ በከተማው ቀበሌ 03 ቀርሳ ፍተሻ ጣቢያ ላይ መያዛቸውን ተናግረዋል ።
ወጣቶቹ ከ17 እስከ 28 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ መሆናቸውን ጠቁመው ከወጣቶቹ መካከል ሶስቱ ሴቶች እንደሆኑ ገልጸዋል።
እንደ ዋና ኢኒስፔክተሩ ገለጻ ወጣቶቹ ከሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሽዋና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች በህገ ወጥ ደላሎች ተታለው የተሰባሰቡ መሆናቸውን አመልክተዋል።
ወጣቶቹን በህገወጥ መንገድ ከሀገር ለማሶጣት በታሰበ ወንጀል ተሳትፎ እንዳላቸው የተጠረጠሩ አሽከርካሪውን ጨምሮ ሁለት ግለሰቦች ተሸከርካሪውን አቁመው መሰወራቸውን ተናግረዋል ።
ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል መጀመሩን አመልክተዋል ።
ወጣቶቹን በሂደት ወደ አካባቢያቸው ለመመለስ ከወዲሁ ስራዎች መጀመራቸውንም ጠቁመዋል።
ዜጎች ጫካ ለጫካ ጭምር በእግራቸው በመጓዝ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ውጭ ሀገራት ለመውጣት በሚያደርጉት ሙከራ ለሞት፣ ለአካል ጉዳትና ለመደፈር እየተጋለጡ መሆናቸውን አብራርተዋል።
ድርጊቱ በተደራጀ አግባብ የሚፈፀም በመሆኑ ለመከላከል አስቸጋሪ እንዳደረገው ያመለከቱት ዋና ኢኒስፔክተሩ የባለድርሻ አካላት ጠንካራ ትብብር በመፍጠር ድርጊቱን ለመከላከል ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ። via (ኢዜአ)
- የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ“ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ የሆኗት ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው።… Read more: የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
- አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ“ወገኖቼ እንማርና እናስተምር፣ ወንጀልን እንጸየፈው፣ እንጥላው፣ ወንጀልን ተጸይፈን ወንጌልን እንውደደው፣ በወንጌል እንኑር፣ ወንጌል ሕጓም ስርዓቷም ያማረች ናት፤… Read more: አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ
- ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናውቤት የተባለች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች፦ “ደም ማነስ የያዘኝ በአሥራዎቹ ዕድሜ ሳለሁ ነው። ቶሎ ይደክመኝ፣ አጥንቶቼን ይቆረጥመኝ፣… Read more: ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ ከሃምሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ገለልተኛ ወገኖች… Read more: የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
- ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረትዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ መገባደዱ እያመራ እንደሆነ ተገለጸ። ለውጭ… Read more: ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት