ከትግራይ ክልል በስምንት መኪናዎች ተጭኖ በህገ ወጥ መንገድ ሊወጣ የነበረ 800 ኩንታል የዕርዳታ እህል አዲ ጉደም ኬላ ላይ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሰተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በድርጊቱ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችን በህግ ጥላ ስር አድርጎ እያጣራ እንደሚገኝም ኮሚሽኑ ገልጿል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሰተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መንግስትአብ የማነ ለኢቢሲ እንደገለጹት፤ በክልሉ ለስብዓዊ ድጋፉ የመጣውን የእርዳታ እህል ከተረጂው ሰው ጎሮሮ ቀምተው ለግል ጥቅማቸውና ብልፅግናቸው ሲሯሯጡ የነበሩ ነጋዴዎች ናቸው፡፡
ከእነዚህ ሰዎች ጀርባ የነበሩ እነማን እንደሆኑ ፖሊስ በምርመራ እያጣራ ይገኛል። በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር የማነ ገሰሰው በበኩላቸው ተደራጅተው እህልን ከዚህ አከባቢ በመግዛት ወደ ተለያዩ ቦታዎች በመውሰድ እጥረት በመፍጠር በትግራይ ረሃብና ችግር እንዲፈጠር የሚያደርጉ አካላት መኖናረቸውን ገልጸዋል፡፡
የወንጀል አፈጻጸሙ በተደራጀ መንገድ መሆኑንም የገለጹት ረዳት ኮሚሽነሩ፤ በዚህ ህገ ወጥ ድርጊት ውስጥ በየዋህነት የሚሳተፉ ባለሞያዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አሳስበዋል፡፡ ከዚህ በፊት በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረው ሶስት ሺህ ኩንታል የእርዳታ ዕህል መያዙን የገለጸው ፖሊስ በወንጀል ድርጊቱ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ሆነው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡
እንደ ኮሚሽነሩ ገለጻ፣ ከዚህ የከፋ ችግር ስለሌለ ህብረተሰቡ በንቃት መሳተፍ ይኖርበታል፡፡ ከህገ ወጥና ስግብግብ ነዳዴዎች በስተጀርባ ያለ ማንኛውም አካል ከህግ ተጠያቂነት እንደማያመልጥ ማወቅ ይኖርበታል ብለዋል፡፡ የመቀለ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጂነር ግዛው ሐጎስ በበኩላቸው፣ ይህ ህገ ወጥ ተግባር በመጀመሪያው እርዳታ አሰጣጥ ላይ መከሰቱን ጠቅሰው በሁለተኛው ዙር ላይ ይሄ እንዳይደገም በጥብቅ ቁጥጥር እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት… Read more: የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል
- ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁመግቢያ ሽግግር ፍትህ ጉልህ የመብት ጥሰቶች በተፈፀመባቸው ሀገራት ተጠያቂነትን ለማስፈን… Read more: ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁ
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን