Site icon ETHIO12.COM

እነ እስክንድር ነጋ በምርጫ ሊሳተፉ ነው- 1.3 ሚሊዮን የሚጠጋ የድምጽ መስጫ ወረቀት እንዲቃጠል ተወሰነ

ምርጫ ቦርድ የባልደራስ አመራሮችን በእጩነት የመመዝገብ ሂደት መጀመሩን አስታወቀ

አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮችን በዕጩነት የመመዝገብ ሂደት መጀመሩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ቦርዱ የፓርቲው አመራሮች ለሚወዳደሩባቸው ቦታዎች፤ ቀደም ሲል አሳትሟቸው የነበራቸውን ወደ 1.3 ሚሊዮን የሚጠጉ የድምጽ መስጫ ወረቀቶች እንዲቃጠሉ ትዕዛዝ ማስተላለፉንም ገልጿል።

ቦርዱ ይህን የገለጸው ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 26 ላስቻለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ አንደኛ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ለችሎቱ እንደተናገሩት፤

የባልደራስ ፓርቲ ቀደም ሲል አስመዝግቧቸው በነበሩ ዕጩዎች ምትክ፤ ለምርጫ እንዲቀርቡለት የሚፈልጋቸውን ግለሰቦች እንዲያሳውቅ፤ በመስሪያ ቤታቸው በኩል ጥያቄ ቀርቦለታል። በዚህም መሰረት ፓርቲው በትላንትናው ዕለት አዲሶቹን ዕጩዎች ማሳወቁን አስረድተዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

Exit mobile version