Site icon ETHIO12.COM

በሂልተን ሎቢ ባልደራስ ምርጫ ቦርድ ለእስክንድር ደጋፊዎች ተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ እንዲሰጠው የመጠይቀ ሃሳብ እንዳለው ማናገሩተሰማ

ወ/ሪ ብርቱካን ሚደቅሳ የሚመሩት የኢትጵያ ምርጫ ቦርድን ባልደራስ ክስ መስርቶ በክርከሩ ማሸነፉ ይታወሳል። ምርጫ ቦርድ የፍርድ ቤት ውሳኔን ባይነቅፍም ሕትመት በማጠናቀቁ ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚቸገር መግለጡን ተከትሎ ያቀረበው የቴክኒክ ችግር የፍርድ ቤት ውሳኔን ወደ ጎን እንዳለ ተደርጎ ሰፊ ወቀሳ ሲሰነዘርበት እንደነበርም አይዘነጋም።

በመጨረሻም ምርጫ ቦርድ በሚሊዮን የሚቆጠር የህትመት ሰነዶች እንዲቃተሉ። እስክንድርና ሌሎች የባልደራስ አባላት የተካተቱበት የመረጮች ሰነድ እንዲዘጋጅ ከትናንት በስቲያ መውሰኑን ተከትሎ አዲስ መረጃ እየወጣ ነው። መረጃውም የተሰማው ከወደ ሂልተን አካባቢ ነው።

ለኢትዮ 12 የአዲስ አበባ ተባባሪ ትዝብቱን የሚያካፍለው የውጭ አገር ጋዜጠኛ እንዳለው ባልደራስ እነ እስክንድር ምርጫ የሚወዳደሩ ያልመሰላቸው ደጋፊዎቻችን ስላልተመዘገቡ ምርጫ ቦርድ ተጨማሪ የመመዝገቢያ ቀን እዲሰጣቸው ለመጠይቅ ማቀዳቸውን ትልቅ ለምትባለዋ አገር ዲፕሎማት ነግረዋል።

በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ10 ሰዓት እስከ ምሽቶ 9 ሰዓት ድረስ በአዘቦት ቀን የሃፒ ሰዓት ሂልተን በምርጫና በርዳታ የመጡ፣ እንዲሁም ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ የሆኑ የውጭ ዜጎች ይታደማሉ። የአገር ቤት አንዳንድ ሚዲያዎችና ፖለቲከኞችም እዛው መታየታቸው የተለመደ ሆኗል።

ባልደራስ አባላቱ እንዲመዘገቡለት ለዲፕሎማቱ ሲናገር የሰማው የሚዲያ ሰው እንዳለው ዲፕሎማቱ ስቀው ቀልድ ቢጤ ጣል አድርገዋል። ቀልዳቸው ውስጥ ” ምርጫውን አንሸነፋለን ብላችሁ ፈራችሁ እንዴ” ብለዋቸዋል።

ባልደራስ በተጣበበ ቀን የመራጭ ምዝገባ ቀን እንዲራዘምለት ማሰቡን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ተባባሪያችን የጠየቃቸው አንድ አባሉ ” የማውቀው ነገር የለም” ሲሉ ተቆጥተዋል። ስማቸውም ሆነ ማንነታቸው ከማናቸውም አስተያየታቸው ጋር እንዳይጠቀስ ተይቀዋል። ከሌሎች አመራሮች አስተያየት ለመስጠት የተደረገው ጥረት አልተሳካም።

ኢትዮ 12 ባለፈው ሳምንት ምርጫው ሲቃረብ ራሳቸውን ለማግለል እየዶለቱ ያሉ ድርጅቶች መኖራቸውን፣ ፓርቲዎቹም በስም መለየታቸውንና የውጩ ማህበረሰብ ተወካዮችም ጠንቅቀው እንደሚያውቋቸው ቅድመ ምርጫ ዳሰሳ ላይ የሚሰሩ የአዲስ አበባ የምርጫ ታዛቢ መሪ ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

ምርጫው ቀርቶ ሁሉም የተሳተፉበት የሽግግር መንግስት ይቋቋም የሚለውን አቋም በመናበብ የሚያራምዱ፣ የአሜሪካና የአውሮፓ መንግስታት፣ እንዲሁም ምርጫ ለመወዳደር የተመዘገቡ ፓርቲዎች በዚህ በተዥጎረጎረው አቋማቸው ወደ ምርጫው ቀን ተጠግተዋል።


Exit mobile version