Site icon ETHIO12.COM

ራሽያ ዶላር መጠቀምን ለማቆም ወሰነች


. አሜሪካ በቻይና ድርጅቶች ላይ ማዕቀብ ጣለች
. የራሽያ እና የቻይና ጥምረት በተግባር ተገለጠ

የአሜሪካንን ማዕቀብ እንደስጋት የቆጠረችው ራሽያ አሜሪካ አዲስ ማዕቀብ የምትጥል ከሆነ የአሜሪካ ዶላርን ከወዲሁ ለማዳከም እና ተፅእኖውን ለመቀነስ የሩሲያ የሀብት ፈንድ ዶላርን ላለመጠቀም ወስናለች ሲል ዎል ስትሪት ጆርናልስ ዘግቧል::

በራሽያ እና በአሜሪካ መካከል እያደገ የመጣውን መካረር ተከትሎ: ሩሲያ አሜሪካ አዲስ ማዕቀቦችን ብትጥል በዶላር የተደረጉ የነዳጅ ኮንትራቶችን በሙሉ ከዶላር ውጭ እንዲሆኑ ወስናለች፡፡ በተጨማሪም የአሜሪካ ዶላር ሀብቶች ከ 186 ቢሊዮን ዶላር ብሔራዊ ሀብታቸው እንደሚቆረጥ ትላንት ሐሙስ የራሽያ የፋይናንስ ሚኒስትሩ አንቶን ስሉአኖቭ አረጋግጠዋል፡፡

የሩሲያን ኢኮኖሚ ከዶላር ተፅዕኖ ነፃ (De-dolarize) ለማድረግ የተጀመረው ይህ እንቅስቃሴ አስገራሚው ነገር ባይደን እና ፑቲን ከፊታችን ባለው June 16 ጀኔቫ በአካል ተገናኝተው ለመወያየት ቀጠሮ በያዙበትና ከስብሰባው ቀናት በፊት መሆኑ ነው:: ምናልባትም ፑቲን ባይደንን ላለማግኘት አለያም አሜሪካ ከወዲሁ አስቢበት የሚል መልዕክት እየላከ ሊሆን ይችላል::

የራሽያ የፋይናንስ ሚኒስትር የሀገሪቱን የነዳጅ ገቢዎች በከፊል የሚይዘው ብሄራዊ ሀብት ፈንድ (National Wealth Fund) ከያዘው የዶላር ንብረት ድርሻ (dollar assets) ከ 35% ወደ ዜሮ እንደሚቀንሰው አስታውቋል፡፡ ከዚያም የ186 ቢሊዮን ዶላር ፈንድ ንብረቶቹን በዩሮ ፣ #በዩዋን እና በወርቅ ይይዛል ብሏል::

ይህ እርምጃ ሞስኮ እና ቤጂንግ የጠበቀ ግንኙነትን እያጎለበቱ ባሉበት በዚህ ወቅት የቻይና ምንዛሬ በሩሲያ ውስጥ ያለውን ሚና የበለጠ ያጠናክረዋልም ተብሏል፡፡ አሰላለፉ ግልፅ ሆነ!!! (ሁሉም ሊንኮች ከታች አሉ))

የሩሲያ ተቀዳሚ ምክትል ጠ/ሚኒስትር አንድሬ ቤሎሶቭ በሴንት ፒተርስበርግ እየተካሄደ ባለው ትልቁ የሃገሪቱ የኢኮኖሚ መድረክ የጎን ለጎን ውይይት ላይ እንደተናገሩት “ይህ የራሽያ ውሳኔ አስተዋይ (Sebsibe) ውሳኔ ነው:: ይህ ውሳኔ ከአሜሪካ መሪዎች እስከዛሬ በደረሰብን እና እየሰማን ካለነው ተደጋጋሚ የማዕቀብ ዛቻ እና ከሌሎች ነገሮች ጋር የሚያያዝ ነው::” ብለዋል በግልፅ!!!

የአሜሪካ እና የሩሲያ ግንኙነት እየሻከረ የመጣው ከ 2014 ጀምሮ ሲሆን ሩስያ ክሬምያን ዳግም የግዛቷ አካል ለማድረግ በጀመረችበት ወቅት ነው:: በቅርቡ አፕሪል ወር ላይ ዋሽንግተን በሞስኮ ላይ ማዕቀብ መጣሏ ግን ለሃገራቱ መካረር ተጠቃሽ ምክንያት ነው:: ይህም አምና በነበረው የአሜሪካ ምርጫ ፣ በሶላር-ዊንድና በኮርፖሬት ኮምፒዩተሮች… ወዘተ ላይ ራሽያ ሃክ አድርጋለች በሚል ነው ማዕቀቡ የተጣለው::

ታዲያ የአሜሪካ ማዕቀብ ቀጣይነት ያለው ስጋት መሆኑን የተረዳችው ሞስኮ ኢኮኖሚዋን ከ greenback ለማላቀቅ እርምጃዎችን በማፋጠን ዶላርን ከሉአላዊ-ሀብቷ ፈንድ ልታወጣ መሆኑ ትላንት መወሰኗ አነጋጋሪ ሆኗል:: ጅምር የአፀፋ ምላሽ ተደርጎም ተቆጥሯል:: በአንፃሩ ሩሲያ የቻይና ገንዘብ ዩዋንን ለመጠቀም መወሰኗ የሃይል አስላለፉን የበለጠ ግልፅ ያደርገዋል::
.
ይህ በእንዲህ እንዳለ የባይደን አስተዳደር ቤጂንግን ያስቆጣ እና በባለሀብቶች መካከል መደናገጥን ያስከተለ ማዕቀብ ጥሏል:: ይህም ከቻይና ጦር ኃይል ጋር ግንኙነት አላቸው ያለቻቸውን የቻይና የንግድ ድርጅቶችን በጥቁር መዝገብ ውስጥ በመጨመር በነዚህ ኩባንያዎች አሜሪካውያን ኢንቨስት እንዳያደርጉ እገዳ ጥሏል ፡፡

አዲስ ከተጠቀሱት ድርጅቶች ውስጥ: በመንግስት ባለቤትነት ከተያዘው ግዙፍ aerospace የቻይና አየር መንገድ አቪዬሽን ጋር የተሳሰሩ ኩባንያዎች እና ሁለት የቴሌኮሙኒኬሽን ጊር አምራች ሁዋዌ ቴክኖሎጅስ ኩባንያዎች ተካተዋል፡፡ ይህም የታገዱ የቻይና ኩባንያዎችን ጠቅላላ ቁጥር 59 ያደረሰ ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ ትቶት የነበረውን ጠንካራ የቻይና ፖሊሲዎች የባይደን አስተዳደር እንዴት እንደቀጠለ ያሳያል ተብሏል::

በአንፃሩ ቻይና: በህጋዊ መንገድ የሃገሯ ኩባንያዎችን ጥቅም እንደምታስጠብቅ እና እንዳስፈላጊነቱም የአፀፋ እርምጃ እንደምትወስድ ዛሬ በጥብቅ አስታውቃለች!!!! በአሜሪካ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ ኃይለኛ እየሆነች በመጣችው ቻይና መካከል እየጨመረ የመጣው ውዝግብ ወደ ጦርነት ግጭት ሊሸጋገሩ እንደሚችሉ በዚህ ጊዜ ግምቶች እየወጡ ይገኛል፡፡

ምናልባት በዚህ ጊዜ በቀጥታ ወደ ጦርነት ላይገቡ ቢችልም ፍጥጫው ጫፍ እንደደረሰ ግን ግልፅ ሆኗል:: የባይደን አስተዳደር ከዚህም በኃላ በቻይና እና ራሽያ ላይ በጣም ጥብቅ የሚባሉ እርምጃዎችን ይወስዳል መባሉ ውጥረቱን የበለጠ ከፍ አድርጎ ወደ ሌላ ደረጃ ሊያደርሰው ወይም ግጭቱ በተለየ መልክ ሊገለጥ እንደሚችል ስጋትን ፈጥሯል:: ቻይና እና ራሽያ በአንድ ላይ ሆነው የተቀናጀ በሚመስል መልኩ አሜሪካንን እንዲህ ፊትለፊት ሲጋፈጡ ማየታችን ጉዳዩ በቀላሉ የማይረግብ ለመሆኑ አመላካች ነው::

እንግዲህ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ስንል እንደቆየነው የራሽያ እና የቻይና ጥምረት ምናልባትም የዓለምን የሃይል ሚዛን ሊቀይረው እና የአለም አዲስ ኦርደር ሊታይ ጫፍ የደረሰ ይመስላል:: በዚህ የሃያላኑ ፍጥጫ ውስጥ ኢትዮጵያ የራሷን ብሄራዊ ጥቅም የምታስከብርበትን እና ህዝቧን የምትጠቀምበትን አካሄድ በደንብ ማሰብ እና ማስላት ይገባታል:: በዚህ ሂደት ውስጥ የገልፍ ሃገራት አሰላለፍም በየጊዜው እየተለዋወጠ በመሆኑ ሃገራችን ሁኔታዎችን እያጤነች በአጭር በመካከለኛ እና በረዥም ጊዜ ተጠቃሚ የሚያደርጋትን አካሄድ ትከተል!!!

ሳይደግስ አይጣላም እንዲሉ: ምንም እንኳን ኢትዮጵያችን በዚህ ወቅት ተግዳሮቶች ቢደቀንባትም በጣም ደስ የሚለው ነገር: ብዙ አማራጭ እድሎችም በኢትዮጵያ ፊት ወለል ብለው ተዘርግተዋል!!!! እድሎቹን በጥበብ እየተጠቀምን መሻገሪያ ድልድይ እናደርጋቸዋለን!!!!! እኛ የምንፈልገው ሰላም እና እድገት ነው!!!!! ይህም ከፈጣሪ ጋር ይሳካል!!!! እውን ይሆናል!!!!

Dejene Assefa

Exit mobile version