አሜሪካ ከሳይበር ጥቃት ጋር በተያያዘ ሩሲያ ላይ ማዕቀብ ልትጥል ነው

የአሜሪካ መንግሥት በሩሲያ ላይ መጠነ ሰፊ ማዕቀብ ሊጥል እንደሆነ ተገለጸ፡፡አሜሪካ ማዕቀቡ የምትጥለው ሩሲያ ባደረገችው የሳይበር ጥቃት አፀፋዊ ምላሽ እንደሆነ አስታውቃለች።ከዚህም በተጨማሪ አሜሪካ በባለፈው አመት ባደረገችው ምርጫ ሩሲያ ጣልቃ ገብታለች በማለትም ትወነጅላለች።

ማዕቀቡ በያዝነው ሳምንት ሃሙስ ይጀምራል ተብሎ የሚታመን ሲሆን፣ በመጀመሪያው ዙር 30 የሩሲያ ተቋማትን ጨምሮ 10 ሩሲያውያን እንደሚባረሩ ተገልጿል። ኢላማ ከሆኑት መካከል ዲፕሎማቶችም አሉበት ተብሏል።

የጆ ባይደን አስተዳደር በተጨማሪ የአሜሪካ የፋይናንስ ተቋማት ከሰኔ ጀምሮ የሩሲያ ቦንድ ከመግዛት እንደሚታገዱም ምንጮችን ጠቅሶ ሲቢኤስ ዘግቧል።የአሜሪካና የሩሲያ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሻከረ መጥቶ ወደ ባላንጣነት ሊሸጋገሩ ይችላል በሚባልበት ወቅት ነው ይህ ማዕቀብ የሚጣለው።

ጆ ባይደንና የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ማክሰኞ እለት ባደረጉት የስልክ ልውውጥ ባይደን አገራቸው ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር “ቆፍጠን ያለ እርምጃ ትወስዳለች” ብለዋል።ባይደን ከዚህ በተጨማሪ ከፑቲን ጋር “ሶስተኛ አገር እንገናኝ” የሚል እቅድ ያቀረቡ ሲሆን፣ ሁለቱም መሪዎች አብረው የሚሰሩባቸውን ዘርፎችም ለማየት ያስችላቸዋል ተብሏል።

በባለፈው ወር ጆ ባይደን ከአንድ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ “ፑቲን ነፍሰ ገዳይ ነው ብለው ያስባሉ ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሻቸው “አዎ” የሚል ነበር።ውስብስብ በተባለው ሩሲያን ጥፋተኛ ባደረገው የሳይበር ጥቃት ዒላማ ከሆኑት የአሜሪካ ኢነርጂ ቢሮ እና ፌደራል መሥሪያ ቤቶች በተጨማሪ የመከላከያ፣ የአገር ውስጥ ደኅንነት (ሆምላንድ ሴኩሪቲ)፣ የአሜሪካ ግምጃ ቤትና ንግድ ሚኒስቴር ዳታዎች ዒላማ መደረጋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። (ዋልታ) –


Related posts:

«ሕወሓት ጦርነትን እንደ አምልኮ የሚቆጥር ቡድን ነው» – ፕሮፌሰር ሀረገወይን አሰፋ
«በሕገወጦች ላይ ያለ ምኅረት እርምጃ መውሰድ አለብን፤ ይህ የመንግሥት ተግባር ነው» የአማራ ክልል
125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ

Leave a Reply