Site icon ETHIO12.COM

ሽብርተኛው ሕወሃት በሰላም ማስከበር ግዳጅ ላይ የተሰማሩ አባላትን ከጎኑ ለማሰለፍ ጫናዎችን ሲያደርግ ነበር

በቅርቡ ከዳርፉር ግዳጃቸውን አጠናቀው የተመለሱትን የሰላም እስከባሪ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የትህነግ ቡድን በተለያየ ዓለም አቀፍ ተቋም ውስጥ በሚሠሩ የራሱ ሰዎች አማካይነት የተለያዩ ጫናዎችን በማሳደር ወደ ሀገራቸው እንዳይመለሱ ጥረት ማድረጉን የገለጹት የ25ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል ተፈራ መላክ ናቸው፡፡

ኮሎኔል ተፈራ መላክ ጁንታው በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የሀሰት ወሬን እየነዛና ሠራዊቱ ውስጥ ባደራጃቸው ቅጥረኞቹ አማካይነት ቅስቀሳዎችን ሲያደርግ ነበር ብለዋል፤ ለዚህ አንሸነፍም በማለት የሀገራቸውን ሰንደቅ ዓላማ አንግበው የዘመቱት የሰላም አምባሳደሮች የጁንታውን ሴራ በማከሸፍ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡

የጁንታው ኃይል ኢትዮጵያ ሀገራችን በዓለም አቀፍ ሰላም የማስከበር ተልዕኮ ያላትን ስምና ዝና ለማጉደፍና ዝቅ ለማድረግ ቢጥርም በሠራዊቱ ጥንካሬ ይህ ሴራው ከሸፏል ያሉት ደግሞ የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምሕርት ቤት ዋና አዛዥ ኮሎኔል አዲሱ ተርፋሳ ናቸው፡፡

አሸባሪው ሕወሃት ለትግራይ ሕዝብ አንዳችም የጠቀመው ነገር እንደሌለና አሁንም በሴራ የተተበተበ ስለመሆኑ ተግባሩ ይመሰክራል ያሉት የሠራዊቱ አባላት ይህን ኃይል የትግራይ ወጣቶች ሊታገሉት ይገባል ብለዋል፡፡ ምንጭ የመከላከያ ሚዲያ ዳይሬክቶሬት ነው


Exit mobile version