በቅርቡ ከዳርፉር ግዳጃቸውን አጠናቀው የተመለሱትን የሰላም እስከባሪ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የትህነግ ቡድን በተለያየ ዓለም አቀፍ ተቋም ውስጥ በሚሠሩ የራሱ ሰዎች አማካይነት የተለያዩ ጫናዎችን በማሳደር ወደ ሀገራቸው እንዳይመለሱ ጥረት ማድረጉን የገለጹት የ25ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል ተፈራ መላክ ናቸው፡፡
ኮሎኔል ተፈራ መላክ ጁንታው በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የሀሰት ወሬን እየነዛና ሠራዊቱ ውስጥ ባደራጃቸው ቅጥረኞቹ አማካይነት ቅስቀሳዎችን ሲያደርግ ነበር ብለዋል፤ ለዚህ አንሸነፍም በማለት የሀገራቸውን ሰንደቅ ዓላማ አንግበው የዘመቱት የሰላም አምባሳደሮች የጁንታውን ሴራ በማከሸፍ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡
የጁንታው ኃይል ኢትዮጵያ ሀገራችን በዓለም አቀፍ ሰላም የማስከበር ተልዕኮ ያላትን ስምና ዝና ለማጉደፍና ዝቅ ለማድረግ ቢጥርም በሠራዊቱ ጥንካሬ ይህ ሴራው ከሸፏል ያሉት ደግሞ የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምሕርት ቤት ዋና አዛዥ ኮሎኔል አዲሱ ተርፋሳ ናቸው፡፡
አሸባሪው ሕወሃት ለትግራይ ሕዝብ አንዳችም የጠቀመው ነገር እንደሌለና አሁንም በሴራ የተተበተበ ስለመሆኑ ተግባሩ ይመሰክራል ያሉት የሠራዊቱ አባላት ይህን ኃይል የትግራይ ወጣቶች ሊታገሉት ይገባል ብለዋል፡፡ ምንጭ የመከላከያ ሚዲያ ዳይሬክቶሬት ነው
- የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ“ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ የሆኗት ግን ጥቂቶች ብቻ… Read more: የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
- አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ“ወገኖቼ እንማርና እናስተምር፣ ወንጀልን እንጸየፈው፣ እንጥላው፣ ወንጀልን ተጸይፈን ወንጌልን እንውደደው፣ በወንጌል እንኑር፣ ወንጌል ሕጓም ስርዓቷም ያማረች… Read more: አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ
- ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናውቤት የተባለች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች፦ “ደም ማነስ የያዘኝ በአሥራዎቹ ዕድሜ ሳለሁ ነው። ቶሎ ይደክመኝ፣ አጥንቶቼን… Read more: ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ ከሃምሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ገለልተኛ… Read more: የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
- ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረትዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ መገባደዱ እያመራ እንደሆነ ተገለጸ።… Read more: ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት