ETHIO12.COM

የአሜሪካ ሰኔተሮች ውሳኔ ቁጥር 97 (ተርጓሚ-ጥበቡ ሞላ)

መቶ አስራ ሰባተኛ ኮንግረስ

1ኛ ስብሰባ ሰኔት ውሳኔ 97 – May 19, 2021 (ሚያዚያ 11, 2013)

us senat

የአሜሪካ ሰኔት የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሃትና ሌሎች በትግራይ ክፍል ግጭት ውስጥ ያሉ ወሮ በላዎችና ጠብ አጫሪዎች ጋር ያሉትን ጠላትነቶች እንዲይቆም፣ሰብዓዊ መብትን እንዲያከብር፣ያለምንም ገደብ ሰብዓዊ እርዳታ ማስገባት እንዲፈቅድና ተፈጽመዋል የምንላቸው በደሎችን ነጻና ገለልተኛ  ከሆኑ መርማሪዎች ጋር ትብብር እንዲያደርግ ጥሪውን እያቀረበ፤

  1. Risch, James E (IN) Republican = አቶ ሪሽ, ጄምስ ኢ (ኢንዲያና) ሪፐብሊካን
  2. Cardin, Benjamin L (MD) Democrat=አቶ ካርዲን, ቤንጃሚን ኤል (ሜሪላንድ)
  3. Rubio, Marco (FL) Republican=አቶ ሩቢዮ, ማርኮ (ፍሎሪዳ) ሪፐብሊካን
  4. Coons, Christopher A (DE) Democrat=አቶ ኩንስ, ክሪስቶፈር ኤ (ዴለዌር)
  5. Kaine, Tim (VA) Democrat=አቶ ኬይን, ቲም (ቨርጂንያ) ዲሞክራት
  6. Young, Todd (IN) Republican=አቶ ያንግ, ቶድ (ኢንዲያና) ረፐብሊካን
  7. Van Hollen, Chris (MD) Democrat=አቶ ቫን ሆለን, ክሪስ( ሜሪላንድ)
  8. Markley, Jeff (OR) Democrat=አቶ ማርክሌይ, ጄፍ (ኦሬጋን) ዲሞክራት
  9. Wyden, Ron (OR) Democrat=አቶ ዋይደን, ሮን (ኦሬጋን) ዲሞክራት
  10. Markey, Edward J (MA) Democrat=አቶ መርኬይ, ኤድዋርድ ጄ (ማሳቹሰትስ)
  11. Sinema, Kyrsten (AZ) Democrat=(ወ/ት) ሲነማ, ካይርስተን (አሪዞና)
  12. Sullivan, Dan (AK) Republican=አቶ ሱሊቫን, ዳን (አርካንሳ) ሪፐብሊካን
  13. Collins, Susan M (ME) Republican=ወ/ት ኮሊንስ, ሱዛን ኤም (ሜይን)
  14. Booker, Corry A (NJ) Democrat=አቶ ቡከር, ኮሪ (ኒውጀርሲ) ዲሞክራት
  15. Rosen, Jacky (NV) Democrat=ወ/ት ሮሰን, ጃኪ (ነቫዳ) ዲሞክራት
  16. Grham, Lindsey (SC) Republican=አቶ ግርሃም, ሊንድሴይ (ሳውዝ ኮሮላና)
  17. Durbin, Richard J (IL) Democrat =አቶ ደርቢን, ሪቻርድ ጄ( ኢሊኖይ)ዲሞክራት
  18. Hassan, Margaret Wood (NH) Democrat=ወ/ት ሃሳን, ማርጋሬት ዉድ

ውሳኔ

የአሜሪካ መንግሥትና የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ከመቶ ዓመት የበለጠ ጠቃሚ ግንኙነት ያላቸው እንደመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሁለተኛ የህዝብ ብዛት ያላት እንደመሆኗ ቁልፍ የሆነ የጸጥታና መረጋጋት ሚና ስላላት በተባበሩት መንግስታትም ውስጥ የመለያ ልብስ በመልበስ ተሳታፊ ብትሆንም፣

በጠቅላይ ሚንስቴር እብይ አህመድ ብልጽግና ፓርቲና በትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር( ቲፒ ኤል ኤፍ ) እስከ መጨረሻ 2011 ድረስ የገዢው ጥምር ፓርቲ ውስጥ የነበረ ጋር ያሉ ውጥረቶች ቲፒ ኤል ኤፍ በሰብተምበር 9, 2020 ምርጫ  የኢትዮጵያን ፌደራል መንግሥት  በኮቪድ-19 ምክንያት ያሰላፋቸውን ውሳኔ ጥሶ በማካሄዱ ውጥረቶቹ ስለተባብሱ፣

የኢትዮጵያ ፊደራላዊ መንግሥት በትግራይ የተደረገው ምርጭ ውድቅ፣ፉርሽና ህገወጥ መሆኑን ገለጸ፣

በኖቨምበር 4, 2020 ማለዳ ላይ ቲፒ ኤል ኤፍ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ሰሜን እዝ ላይ ጥቃት በመፈጸሙ የተናሳ ጠቅላይ ሚንስተር አብይ የጦር ሃይል ትእዛዝ በመስጠት በቲፒ ኤል ኤፍና በኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ መካከል ውጊያ በመኪያሄዱ የብዙዎች መሞት በመገናኛዎ ብዙሃኖች ስለተነገረ፣

የኢትዮጵያ መንግሥት የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሲሪል ራማፎሳን ጨምሮ በኖቨምበር 2020 ከቲፒ ኤል ኤፍ ጋር የስምምነት ድርድር እንዲያደርግ የተደረገለትን በጎ ችሮታ ባለመቀበሉ፣

በኖቨምበር 28, 2020 የኢትዮጵያ መንግሥት የትግራይ ክፍል ዋና ከተማ መቀሌን ከተቆጣጠረ በኋላ ግጭቱን በድል መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አስትውቀው የጦር እንቅስቃሴዎች  ትኩረታቸውን ወደ ግንባታና ሰብዓዊ እርዳታ መስጠት ላይ እንደሚሰማራ፣ የቲፒ ኤል ኤፍ መሪዎችንም አሳድዶ እንደሚይዝ በመግለጹ፣

በትግራይ ውስጥ ግጭቶች በመቀጠላቸው የኢትዮጵያ ወታደሮች በቲፒ ኤል ኤፍ ላይ በሚያደርጉት ክትትል የታወቁ የቲፒ ኤል ኤፍ አመራር አባላትን እንደ ቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የነበረ ስዩም መስፍንና መስሎችን በመግደል እንደ “ማረግያግያ ተልእኮ፣ ፍትህን ለማምጣት” በማለት የሚወሰዱ እርምጃዎች ስለቀጠሉ፣ተጨማሪ ያንብቡ:  በእምነት ተቋማቱ ውስጥ የተፈፀመው ነፍስ ግድያ

በ 2020 ጦርነቱ  ከመጀመሩ በፊት በትግራይ ውስጥ ከ1,800,000 (አንድ ነጥብ ስምንት ሚልዮን) ሰዎች በላይ በኢትዮጵያ ውስጥ ከነበሩበት የተፈናቀሉ ሲሆን በግምት 2,000,000 (ሁለት ሚልዮን) ሰዎች በትግራይ ውስጥ ሰብዓዊ እርዳታ ስለሚያስፈልጋቸው፣

በጦርነቱ ከ 61,000 (ስድሳ አንድ ሺህ) በላይ ኢትዮጵያውያን ሱዳን ውስጥ ጥገኝነት እንዲጠይቁ በማድረጉ፣ ከ 500,000 ( አምስት መቶ ሺህ) በላይ ሰዎች ከነበሩበት በመፈናቀላቸው የምግብ፣የውህኃ፣የመድኃኒትና ሌሎች ለኑሮ አስፈላጊ ነገሮች በትግራይ ውስጥ ከፍተኛ እጥረቶች ስለተከሰቱ፣

ግጭቱ የሰብል መሰብሰብ አስተጓግሏል፤ ግብይትን፣የአቅርቦት መንገዶችን አስተጓግሏል፣ምግብና መድሃኒት ተሰርቋል፤ በስራ መጓተት ምክንያት አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ 4,000,000 (አራት ሚልዮን) ለሚጠጉ የትግራይ ሰዎችና 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ኤርትራውያንን ጨምሮ ለማቅረብ ባለመቻሉ፣

ግጭቱ በተጀመረ ጥቂት ሳምንቶች ውስጥ የመብራት፣የባንክ፣የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎቶች በትግራይ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ከአገልግሎት ውጭ እንደነበሩ የኢትዮጵያ መንግስትም የቲፒ ኤል ኤፍ ሰራዊት ያደረሳቸው ጥፋቶች ምሆኑን የገለጸና የተወሰኑ የጥገና ስራዎች መካሄዳቸው ገልጿል፣

የስልክና ኢንተርኔት መዘጋት በተጨማሪ ጋዜጠኞች ስለ ትግራይ ክፍል መረጃ ስለ ግጭቱ ለማግኘት በከፍተኛ ደረጃ ውሱን ስለሆኑ፣ ስለ ግጭቱ የዘገቡ ጋዜጠኞች በመታሰራቸው፣ የትግራይ ብዙሃን መገናኛ ወኪል የሆነ ጋዜጠኛ በመገደሉ፣

የኢትዮጵያ መንግሥት ከተባበሩት መንግስታት ጋር በኖቨምበር 29, 2020 የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ለማመቻቸት ስምምነት ቢያደርግም በትግራይ ውስጥ ያልተገደበ እንቅስቃሴ ለማድረግ ባለመቻሉ፣

በፌብሩዋሪ 1, 2021 የኖርዌይ ስደተኞች አማካሪ ዋና ጸሃፊ “ ጦርነቱ በጀመረ አስራ ሁለት ሳምንቶች ውስጥ በሚፈለገው ደረጃ ለአስችኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ በተፈለገው መጠን እስከ አሁን ማቅረብ አልተቻለም፣ ሁኔታዎች እየተሻሻሉ፣ድጋፍ አቅርቦቱም በመጠኑ እያደገ ነው ማለትም ስህተት ነው።እርዳታው ሊደርስ የቻለው ጥቂት ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች ነው፣ ያሉን የተወሰኑ የድጋፍ ምንጮች ካሉት የአስቸኳይ ስብዓዊ ፍላጎቶች ጋር አልተመጣጠኑም” በማለት ስለ ገለጹ፣

በፌብሩዋሪ 6, 2021 የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም (ደብልዩ ኤፍ ፒ) ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ አቅርቦት፣ ሂደቱንና አቅርቦትን ገምግሞ ውሳኔ ለመስጠት አዲስ ስምምነት ከተባበሩት መንግሥታትና ዓለም አቀፍ ተባባሪዎች ወኪሎች ጋር ስምምነት ላይ ቢደረስም፣

በተለይም ለ100,000 (መቶ ሺህ) በስደት ካምፕ ለሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች እርዳታ ለማቅረብ በጣም ውሱን መሆን፣ ሂስትስና ሺመልባ ካምፖች እስከ አሁን ድረስ የማይደረስባቸው በመሁኑ፣ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ወኪል ከ20,000 (ሃያ ሺህ) ኤርትራውያን ስደተኞች ከካምፑ የተፈናቀሉ የት እንደደረሱ የማይታወቅ መሆኑን በመግለጹ፣

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፍሊፖ ግራንዲ “ ህሊናን የሚረብሽ በከፍተኛ ቁጥር የሚገመት የኤርትራውያን ስደተኞች በትግራይ ውስጥ እንደተገደሉ፣ በግድ የተወሰዱና ወደ ኤርትራ የተመለሱ እንደነበሩ  በመገረም ያመለከተ በመሆኑ፣

በ ኖቨምበር 2020 አራት ሰብዓውያን ሰራተኞች አንድ የአለም አቀፍ ደርሶ አጋዥ ኮሚቴ ሰራተኛና ሦስት የዳኒሽ ስደተኛ ካውንስል ሰራተኞች በሂትሳትስ ስደት ካምፕ ውስጥ በመገደላቸው፣

የመድረሻ መንግዶች በጣም ውስን በመሆናቸው የሚፈጸሙ ሰብዓዊ ግፎችን ለመዘገብና ለህዝብ ለማሳወቅ አስቸጋሪ በመሆኑ ከዓይን ምስክሮችና የሳቴላይት ምስሎች እንደሚያመለክቱት በተራ ሰዎች ላይ ያተኮረ በርካታ ጥቃት በተለያዩ የግጭት ቡድኖች መፈጸሙ፣

እንደ ምሳሌ ከሚጠቀሱት የህዝብ ጭፍጨፋዎች የተጠቀሰው በትግራይ ክፍል ማይካድራ ከተማ ውስጥ በ ኖቨምበር 9, 2020 የተፈጸመውን በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ኮሚሽን ግምት ከ600( ስድስት መቶ) ተራ ሰዎች ሲገደሉ ኮሚሽኑ ድርጊቱን “ የተገደሉበት ሌላ ምክንያት አይደለም በማንነታቸው በጎሳ ምክንያት ነው” በማለት ደምድሟል። በአክሱም ከተማ ከኖቨምበር 28 እስከ 29, 2020 የተደረገው የጅምላ ግድያ በአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት መሰረት ” በመቶዎች የሚቆጠሩ ያልታጠቁ ሰዎች “ በረቀቀ ዘዴ የኢትዮጵያና የኤርትራ ወታደሮች ከተማውን ሲያስመልሱ መግደላቸውን ሪፖርቱ በመግለጹ፣

የተባበሩት መንግሥታት በጾታ ግንኙነት ጥቃት በግጭት ወቅት ዋና ተጠሪ ፕራሚላ ፓተን ጾታን መሰረት ያደረጉ አስገድዶ መድፈር በመቀሌ መፈጸማቸው፣

በጃንዋሪ 27, 2021 የአሜሪካ መንግሥት በገሃድ የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል ጋር ተካፊይ ሆነው እንደሚዋጉ የገለጸ መሆኑና የኤርትራ ወታደሮችም በአስቸኳይ ከትግራይ ክፍል እንዲወጡ መጠየቁ፤ የሚታመኑ የዜና ምንጮች እንደገለጹት በግጭቱ የተሳተፉት የኤርትራ ወታደሮች ተራ ሰዎችን ማጥቃታቸውን፣ዘረፋ ማካሄዳቸው፣ቤቶችንና መሰረተ ልማቶችን ማውደማቸውን መዘገባቸው፣

ኢትዮጵያ አስር ዓመታት ያህል በበርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ችግር ውስጥ ቆይታለች፣ከነዚህም ማንነትና ጎሳ ላይ በተነጣጠረ የሚፈጸም ጥቃት፣ የተፈጥሮ አደጋና የፖለቲካ አለመረጋጋት እንደተፈታተኗት፣

ከመሃል 2020 ጀምሮ የተባበሩት መንግሥታት ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጽህፈት ቤትና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ኮሚሽን በጎሳና ማንነት ላይ ያተኮሩ አስከፊ ጥቃቶች በተለያዮ የኢትዮጵያ ክፎሎች፣ በአማራ፣ቤንሻንጉል ጉመዝ፣ ሶማሊ፣አፋርና ኦሮሚያ   እየጨመሩ መሆኑን በመግለጻቸው፣

እንደ ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ያሉ ድርጅቶች ስልትግራይ ክፍል በግጭቱ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ከስራቸው በመወገድ ከአገር እንዳይወጡ ታግደው በዐይነ ቁራኛ እየተጠበቁ በገፍ በጎሳነት ተለይተው መታሰራቸውን በመዘገባቸው፣

በማርች 2021 የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆ ባይድን ሰናተር ክሪስቶፈር ኩንስን መልዕክት ለጠቅላይ ሚንስተር አብይ  በትግራይ ውስጥ ስለ ስብዓዊ መብት ጥሰት፣ የተከሰቱ ቀውሶችና ስለ አፍሪካ ቀንድ ድንበር አለመረጋጋት  እንዲያደርሱ ጠየቋችው።

ኢትዮጵያ  እንክብካቤ የሚያስፈልገው  የፖለቲካ ሽግግር በማድረግ ላይ ከመሆኗ ጋር የጁን 2020 ጠቅላላ ምርጫ ወደ ጁን 2021 ከትግራይ ክፍል በስተቀር እንዲሸጋገር ሲደረግ ትግራይ ውስጥ መቼ ምርጫ እንደሚደረግ የቀን ሰሌዳ አልተያዘም።

የኢትዮጵያ መንግስት ብዙ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በሰላም ተሰብስበው እንድይደራጁ በማገድ ብዙ ተቃዋሚ መሪዎችን ከበጋው 2020 ወቅት ጀምሮ ታስረው ይገኛሉ፣የህግ መብት በመጣስ የፍርድ ቤት ቀጠሮዎች ይቀያየራሉ፣ በዚህም ተማርረው ጥቂት ስማችው የሚታወቅ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች በምርጫው ከመሳተፍ እራሳቸውን  ከሚመጣው ሀገራዊ ምርጫ እንደሚያገልሉ ማስፈራርያ በመስጠታቸው፣

በትግራይ ውስጥ ያለው ግጭት፣በሌሎች ኢትዮጵያ ክፍሎች የሚደረጉ የእርስ በርስ ደም መፋሰሶች፣የፖለቲካ እንቅስቃሴ የማድረግ መድረክ መቦርበር በጁን 2021 የሚደረገው  ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያውያንን ምኞት የሚያሟላና በአለም የአለም ምርጫ መለኪያ መስፈርትን የጠበቀ ሚዛናው አይሆንም የሚል እሳቤ በመኖሩ፣

በትግራይ ውስጥ ያለው ግጭት ከተወሳሰቡ  አህጉራዊና የዓለም ሁኔታዎች ጋር መያያዙ እንደ በውይይት ላይ ያለው የኢትዮጵያ ፣ግብጽና ሱዳን ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ግድብ፣ የኢትዮጵያና የኤርትራ ወዳጅነት ፣የአልሸባብ አደጋ፣ የአለም ሃያላት የአካባቢ ቁጥጥር የበላይነት ፉክክሮች፣ እየጠነከረ ያለው የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ክርክር፣ በቋፍ ላይ ያለው የሱዳን ወደ ዲሞክራሲ የሚደረግ ሽግግርና የሱዳን የሰላም ሂደት ያካተተ በመሆኑ፣ ስለዚህ፣ እንዲሆን፣

  1. አጽድቋል፣ ሰኔቱ–
  2. (1)         በኢትዮጵያ የትግራይ ክፍል ደመኝነቶች ባስቸኳይ እንዲቆሙ ይጠይቃል
  3. (2)         በተራ ህዝብ ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ክፉኛ ያወግዛል
  4. (3)         የኤርትራ መንግሥት የጦር ሃይሉን ባስቸኳይ ከኢትዮጵያ እንዲያስወጣ ይጠይቃል፣ ማናቸውንም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን፣ ግድያዎችን፣ ዘረፋዎችን፣ አስገድዶ መድፈርና በኤርትራውያን ጦር ወይም በሌሎች ኃይሎች በትግራይ ክፍል ወይም ሌሎች ኢትዮጵያ ክፍሎች የሚፈጸሙትን አጥብቆ ይኮንናል፣
  5. (4)    በኢትዮጵያ መንግሥትና በቲፒ ኤል ኤፍ መሃከል ያለውን  የፖለቲካ ውጥረት ወደ ጦርነት የወሰደውን ሁኔታ  ከፍተኛ በሚባል ቃልና ሃረግ እንደማይደግፍ ይገልጻል፣
  6. (5)    መብራት፣የባንክ አገልግሎት፣ ስልክ፣ ኢንተርኔት አገልግሎቶች በትግራይ ክፍልና በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በአስችኳይና ሙሉ በሙሉ ጥገና ተድርጎ እንዲጀምሩ ያዝዛል፣ጥሪ ያደርጋል፣
  7. (6) የሱዳን መንግስት ከትግራይ ክፍል የተሰደዱ ስደተኞችን በመቀበሉ ያደንቅል፣ያመሰግናል፣
  8. (7)           በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ግፊትና ጫና—

ተጨማሪ ያንብቡ:  መኢአድና አንድነት ለውህደት ማስፈፀሚያ የገንዘብ ድጋፍ እያሰባሰቡ ነው

(ሀ)  ተጨባጭ እርምጃዎች የስብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ ለተባበሩት መንግሥታት ዓለም ምግብ ፕሮግራምና ለአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሃላፊ አንቶኒ ብሊንከን ቃል በተገባው መሰረት እንዲፈጸም፣

(ለ)   ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በፈጸሙ ላይ ተጠያቂነት እንዲኖር፣

(ሐ)  የትግራይን ክፍል በተመለከቱ ሌሎች ጉዳዮች ላይ መሻሻል እንዲኖርና በአካባቢው መረጋጋት ከሰኔተር ኩንስ ጉብኝት በኋላ እንዲረጋገጥ፣

(8)     የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲያደርግ የሚጠበቅብት–

(ሀ)   የተያዙ የቲፒ ኤል ኤፍ አባላት ያለምንም ሃይል መጠቀምና መብት ጥሰት  በኢትዮጵያና ዓለም አቀፍ ህግ ሙሉ በሙሉ መብታቸውን እንዲያከበር፣

(ለ)    የኤርትራ ወታደሮች  ሙሉ በሙሉ በአስቸኳይ ከኢትዮጵያ ለቅቀው እንዲወጡ፣

(ሐ)  የታሰሩ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፣ደጋፊዎችና ኣክቲቪስቶች ባሳዩት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ምክንያት የታሰሩ በሙሉ፣ ስለፖለቲካ እንቅስቃሴ በመገናኛ ብዙሃን በማሰራጨት የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ መብታቸው ያለ ምንም አድልዎና ልዩነት ተጠብቆ በነጻ እንዲለቀቁ፣

(መ)   ሀገር አቀፍ ተቀባይነት ያለው ብሄራዊ ውይይትና እርቅ በኃይል ሳይሆን በሰላማዊ መንገድ ላሉት ብሶቶች ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ሁሉን ፓርቲዎች፣የጎሳ ህብረተሰቦች፣የሃይማኖት ክፍሎች ያካተተ ስብስብ በማቀናበር ለአገር ሰላም እንዲሰራ፣

  1. (9)    ሁሉም የግጭት ተሳታፊ ፓርቲዎች ላይ ግፊት በማድረግ፣

(ሀ)   ማንኛቸውንም ጠላትነት እንዲያስወግዱ፣በፖለቲካ መፍትሄ ላሉት ልዩነቶች መፍትሄ ማምጣት፣ የዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ህግን ሙሉ በሙሉ ማክበርና የተራውን ህዝብ ሰላም ከሚያውኩ የፖለቲካ ቅስቀሳዎች እንዲቆጠቡ፣

(ለ)  የሰብዓዊ እርዳታ ያለምንም ቁጥጥርና ግደባ ለእርዳታ አቅራቢዎች፣ለቁሳቁሶች በግጭቱ ለተጎዱ የትግራይ ክፍሎአ የሚደርሱባቸው ሁኔታዎች በአስቸኳይ በግልጽ በሚታይ ሁኔታ እንዲሻሻሉ፣ ከነበሩበት ስፍራ ለተፈናቀሉ ሰዎች፣ስደተኞች አስፈላጊ ጥበቃና ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደረግላቸው፣

(ሐ)  በትግራይ ክልል በተነሳው ግጭት አሉ የሚባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ከሚመረምሩ ነጻ መርማሪዎች ጋር ትብብር እንዲደረግ፣ተቀባይነት ባላቸው መርማሪዎችም ተጠያቁ የሚባሉትን ተጠያቂ እንዲደረጉን

  1. (10) የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፣ ጸሀፊና የገንዘብ ሚንስቴር ዋና ጸሃፍና የአሜሪካ አስተዳደር ወኪሎች፣አለም አቀፍ እድገት ወኪሎች ፣ሀላፊዎች በትብብርና ቅንጅት የሚከተሉትን እንዲያስፈጽሙ፣

(ሀ)  የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣኖችና ቲፒ ኤል ኤፍን በማገናኘት በመሃከላቸው ያሉትን ግጭቶች ሙሉ  በሙሉ እንዲቆሙ ማሳተፍ፣ የኤርትራ ወታደሮች በግጭቱ የተነሳ የመጣውን የስብዓዊ ቀውስን እንዲያቆሙና ብሄራዊ ውይይትን እና እርቅን እንዲደግፉ፣

(ለ)    ለነፍስ ማቆያ አላስፈላጊ  የሆኑ ለኢትዮጵያ የተባሉ ሁሉ በአስቸኳይ እንዳይሰጡና እንዲታገዱ፣የአስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፎች ግን አስፈላጊ ተረጂዎች ፍላጎቶችን  ለመርዳት እንዲፈቀድ፣ሰላማዊ የግጭት መፍቻ ውሳኔዎችና እርቅን በመላው ሀገርና የኢትዮጵያ ወደ ዲሞክራሲ መሸጋገርን መርዳት፣

(ሐ)   “ሙሉ በሙሉ” ነጻ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መርማሪዎች በትግራይ ግጭት በአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ዋና ጸሀፊ በፌብርዋሪ 27, 2021 ተከሰቱ ያሏቸውን ጥሰቶች እንዲመረምሩ ተከታታይ እርምጃ መወሰዱን ማረጋገጥ፣

(መ)    ያሉትን የዲፕሎማሲያዊ፣የዕድገትና ህጋዊ መሳሪያዎች ሁሉ በመጠቀም ጎሳና ማንነትን ምክንያት በማድረግ ግጭቶች  በማንም፣ መንግሥት ባልሆኑ ታጣቂዎችን ጨምሮ እንዳይቀጥሉ ለመከላከልና የብዙሃን ተፎካካሪ -ፓርቲ ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ እንዲተወቅና፣

(ሠ)    ከአለም አቀፍ አጋሮች ፣ከተለያዩ ብዙ-ዘርፍ ድርጅቶች ጋር የቅርብ ቅንብር በማድረግ በትግራይ ክፍልና በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ ስላሉ ግጭቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ የተባበሩት መንግሥታትን ጸጥታ ምክር ቤት ጨምሮ ትኩረት እንዲሰጥባቸው፤

የአሜሪካው ሰኔት ውሳኔ አስተላልፏል።

ከዘሃበሻ የተወሰደ

Exit mobile version