Site icon ETHIO12.COM

አስገድዶ መድፈር // ትግራይ

በጦርነቱ ላይ የተረጋገጠ የተባለው 108 ሴቶች ላይ ጥቃት መድረሱ የአለምን ሚዲያ ሲያንቀጠቅጥ የነበረ ዜና ነበረ። አንድ የህዋሃት ደህንነት ብቻ 50 ሴቶችን አስገድዶ የደፈረ ጊዜ በዋስ የለቀቀው

ልጅ ግሩም ( PHD) Opinion


አንዳንዶቻችን እንደምናስታውሰው ከጦርነቱ በፊት በትግራይ ክልል አዲ ዳዕሮ ወረዳ የደኅንነት አባል የተባለ አንድ ግለሰብ በወረዳው 50 ሴቶችን አስገድዶ መድፈሩን ለወቅቱ የክልሉ ባለስልጣኖች (ለህዋሃት አመራሮች) ሪፖርት እንዳያደርጉ በማስፈራራት ወረዳውን ካሸበረ በኋላ በሕዝብ እሮሮ በቁጥጥር ሥር ውሎ በ6 ሺህ ብር ዋስ መለቀቁ ነው። ይህ ዜና October 25, 2019 (ሁለት አመት ሊሞላው ነው)
የሕዝብና የጤና ጥናት ሪፖርት በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2016 እንደሚለው ትግራይ ክልል ፆታን መሠረት አድርገው ከሚፈፀሙ ጥቃቶች በኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ይህ እንግዲህ በተለይ ወሲባዊ ጥቃቶች ሪፖርት የመደረግ አጋጣሚያቸው ዝቅተኛ መሆኑን ላየ ትክክለኛ ገጽታ የማያሳይ ነው። እንደ ሪፖርቱ ለቤተሰብ፣ ለባሎቻቸው፣ ለህክምና ባለሙያዎች፣ ለጓደኛ ወይም ለፖሊስ ጥቃት እንደደረሰባቸው የሚናገሩት ከጥቃት ሰለባዎች 7 በመቶው ብቻ ናቸው።
ለብዙ አመታት በትግራይ ክልል እየተስፋፋ በመጣውን በሴቶች ላይ የሚፈጸም አስገድዶ የመድፈር ጥቃትን በመቃወም በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጥቅምት 9 ቀን 2012 የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ አራት ወንዶችና ስምንት ሴቶች በድምሩ አስራ ሁለት አባላት ያሉት የሰልፉ አስተባባሪ ኮሜቴ ለመቐለ ከተማ አስተዳደር ጥቅምት 3 ቀን 2012 በተጻፈ ደብዳቤ ቢጠይቁም ሰልፉ ተከልክሎ ነበረ።
ከሁለት አመታት በፊት በትግራይ ክልል የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶች እጅግ አስከፊ በመሆናቸው ይህንን የሚቃወም ግንዛቤ ለመጨመር እስከ ጦርነቱ መጀመሪያ ድረስ በማሕበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ይደረግ ነበረ። የምታስታውሱ ካላችሁ “ይኾኖ” በሚል ሃሽታግ በትግራይ ወጣት ሴቶች እየተካሄደ ነበረ።
የዓዲ ዳዕሮ ከተማ ህዝብ በተለይም ሴቶች ብሶታቸውን ለማሰማት አደባባይ መውጣታቸውን የተመለከተ ነበር። የከተማይቱ ነዋሪዎች ድምጻቸውን እንዲያሰሙ ካደረጋቸው በርካታ ምክንያቶች አንዱ የሴቶች ጥቃት እና ጥቃት ተፈጽሞ በሚገኝበት ሰዓት የሚወሰደው ህጋዊ እርምጃ ዝቅተኛ መሆኑ ነው።
ከአራት ዓመት በፊት የወጣው የማእከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ እንደሚያመለክተው አስገድዶ መድፈር የጠቅላላ የትግራይ ክልል የሰነበተ ችግር መሆኑን ነው። በትግራይ ክልል 12 በመቶ ሴቶች በየዕለቱ ፆታዊ ጥቃት ያስተናግዳሉ። ሪፖርቱ እንደሚለው
“A 12.7% (117) rape prevalence was reported among women who visited Gynecologic Outpatient Departments of Selected Hospital in
Tigray region” በእ.አ.አ በ2015 ብቻ 12.7 በመቶ ወይም 117 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ጥቃት እንደደረሰባቸው በትግራይ ክልል (መቀሌ) የማህፀን ሕክምና የተመላላሽ ሕክምና ክፍልን ከጎበኙ ሴቶች ሪፖርት አድርገው ነበረ። በዚህ ወቅት የህዋሃት ባለስልጣኖች የፌዴራል መንግስትንም የትግራይ ክልልንም በሙሉ የበላይነት በሚመሩበት ወቅት የተከሰተ ቢሆንም ማንም የክልሉ ባለስልጣን ሃላፊነት ያልወሰደባቸው ወንጀሎች ነበሩ።
በትግራይ ክልል ከሚኖሩ ያገቡ ሴቶች መካከል 18.7 በመቶ ከዚህ በተጨማሪ 81 በመቶ በትግራይ ገጠር አካባቢ የሚኖሩ ሴቶች በወላጆቻቸው ወይም አሳዳጊዎቻቸው ወይም የቅርብ ሰው ከተደፈሩ በኋላ ደፋሪዎቻቸውን እንዲያገቡ ይደረጋል።

ከላይ የጠቀስኩት ጉዳይ አሁን አንዳንድ ጥያቄዎችን ያስነሳል።
በጦርነቱ ላይ የተረጋገጠ የተባለው 108 ሴቶች ላይ ጥቃት መድረሱ የአለምን ሚዲያ ሲያንቀጠቅጥ የነበረ ዜና ነበረ። አንድ የህዋሃት ደህንነት ብቻ 50 ሴቶችን አስገድዶ የደፈረ ጊዜ በዋስ የለቀቀው እንደ ከባድ ወንጀል ስላልታየ ነበረ። ከታች በተጠቀሱት ምንጮች በጥናት እንደታወቀው አስገድዶ መድፈር የክልሉ የቆየ ወንጀል እንደ ባህል የነበረ አሁን እየተባባሰ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
የጦርነት ወቅት ለግርግር ያመቻል። ለትግራይ ሴቶች በሰላም ጊዜም ሆነ በጦርነት ከጥቃት የሚያድናቸው ኖሮ አያውቅም። ትግራይ ክልል በርካታ ሴቶች የመደፈር ጥቃት እንደደረሰባቸው መንግስት ማረጋገጫ የሰጠው መንግስት ወንጀለኞቹን ስለሚያውቃቸው ሳይሆን ተጠቂዎቹ ከሰጡት መረጃ የህክምና ማስረጃ ነው።
ዋናው ጥያቄ በትግራይ ክልል ለሚነዙት የአስገድዶ መደፈር ጥፋት በስተጀርባ ምን አለ?
ከነበረው ጥልቅ የፆታዊ ጥቃት ባህርይ ምን ያህሉ ከጦርነቱ ጋር ይገናኛል?

ምንጮች ……
Bayu H, et al. Magnitude, Complication and factors Associated with Rape among Women visited Gynecologic Outpatient Departments of Selected Hospital in Tigray Region, Northern Ethiopia, 2016.

Galu SB, Gebru HB, Abebe YT, et al. Factors associated with sexual violence among female administrative staff of Mekelle University, North Ethiopia. BMC Res Notes. 2020;13:15.

Gessessew A, Mesfin M. Rape and related health problems in Adigrat Zonal Hospital, Tigray Region, Ethiopia. Ethiopia Journal of Health Dev. 2004;18(3):140–4.

Exit mobile version