በእንግሊዝ እየተካሄደ ያለው የቡድን 7 ሃገራት ስብስባ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል:: በመግለጫው የኢትዮጵያ ጉዳይም ተካቷል:: በአንቀፅ 54 ላይ የሰፈረው መግለጭ ቃል በቃል የሚከተለውን ይላል።
ትርጉም
54. “በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ እየተካሄደ ባለው ግጭት እና እየወጡ ባሉ ሪፖርቶች ምናልባት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ሁኔታ ውስጥ ሊሆኑ ስለሚችሉ የሰብአዊ አደጋዎች በጣም ያሳስበናል፡፡ የጾታ ጥቃትን ጨምሮ እየተፈፀሙ ያሉ አሰቃቂ ድርጊቶችን እናወግዛለን ፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን (OHCHR) ምርመራዎችንም በደስታ እንቀበላለን እንዲሁም በትግራይ ለተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሙሉ ተጠያቂነት እንዲሆኑና ወንጀለኞቹም ለህግ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን፡፡ ግጭት በፍጥነት እንዲቆም ፣ ያልተዳረሰ ሰብዓዊ አቅርቦት ወደ ሁሉም አካባቢዎች እንዲደርስ እና የኤርትራ ኃይሎች በፍጥነት እንዲወጡ እንጠይቃለን፡፡ ለችግሩ ብቸኛ መፍትሄ ተአማኒ የፖለቲካ ሂደት ሁሉም ወገኖች እንዲከተሉ እንጠይቃለን፡፡ በቀጣይም የኢትዮጵያ መሪዎች የሰብአዊና የፖለቲካ መብቶችን በማክበር ላይ በመመስረት ብሄራዊ እርቅ እና መግባባት እንዲፈጠር ሰፋ ያለ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲያራምዱ ጥሪ እናቀርባለን፡፡” ትርጉሙ የተወሰደው ከደጀኔ አሰፋ ነው።
በዚህ አንቀጽ መሰረት ኢትዮጵያ ያልተስማማቸው ከትህነግ ጋር ንግግር የሚባለውን ህሳብ ነው። አልተካተተም። ጥቅል የፖለቲካ ፈውስ እንደሚያስፈልግ መንግስትም አምኗል። አስቀድሞ ተናግሯል። የሚገባ ምክር ነው ተብሏል። አሜሪካ ያወጣቸው መግለጫ ሲጨመቅ አይነት ነውልል
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ ከሃምሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ገለልተኛ ወገኖች አስታውቀዋል። ጎን… Read more: የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
- ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረትዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ መገባደዱ እያመራ እንደሆነ ተገለጸ። ለውጭ አገር ሚዲያዎች… Read more: ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት
- የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀናላቸው፤ ከአገር አይወጡምየፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የትራንስፖርት ስምሪትና የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር ሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ 11 ግለሰቦች በስር ፍ/ቤት የተሰጠውን ዋስትና አፀና።… Read more: የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀናላቸው፤ ከአገር አይወጡም
- መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለየአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ ምክንያቱም “የኢትዮጵያ መንግሥት በሕገ ወጥ መንገድ የአውሮፓ ኅብረት አገራት ውስጥ የሚኖሩ… Read more: መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ
- “ሰራ ሰራ አድርጌ ቶሎ እመለሳለሁ” ሚሊየነሩ የሸኔ የ”ነጻነት” ታጋይ ወደ ጫካ ሲገባ ስንብት ላይ የተናገረውየሚነሳው ጉዳዩ ልብ ሰባሪ ነው፣ ያስቃል፣ ያዝናናል፣ ያስገርማል፣ ያሳዝናል፣ ይቀፋል፣ ያሳፍራል፣ ለማመን ያስቸግራል … አንባቢ ስም ይስጠው። እኔ ስጽፈው… Read more: “ሰራ ሰራ አድርጌ ቶሎ እመለሳለሁ” ሚሊየነሩ የሸኔ የ”ነጻነት” ታጋይ ወደ ጫካ ሲገባ ስንብት ላይ የተናገረው