Site icon ETHIO12.COM

“ሱዳን በትርምስ ቋፍ ላይ ናት”አብደላ ሀምዶክ

ሱዳን ወደ እርስ በእርስ ጦርነት የመግባት አደጋ ጫፍ ላይ እንደምትገኝ ጠቅላይ ሚኒስትሯ አብደላ ሀምዶክ ቢቢሲ አፍሪካ ዘግቧል። ቢቢሲ በዘገባው ለሱዳን መፍረስ ዋና ምክንያት የወደቁት አልበሽር ደጋፊዎች መሆናቸውን ገልጿል። ጉዳዩ ከኢትዮጵያ ጋር ተመሳሳይ መሆኑ ነው።

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ እየመሯት ያለቸው ሱዳን ምንም አንኳን የኢኮኖሚ ሪፎርም ብትጀምርም ወደ ትርምስ እና የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ የመውደቅ አደጋ እንዳንዣበባት ሳያቅንማሙ አስታውቀዋል። አደጋውን አምጥተዋል ሲሉ ተጠያቂ ያደርጉት ደግሞ የቀድሞ ባለስልጣናት ታማኝ ያሉዋቸውን ሃይሎችን እንደሆነ አመልክተዋል።

በሱዳን መንግስት በነዳጅ ላይ የሚደረገው ድጎማ መንሳቱን ተከትሎ በአገሪቱ ስፊ ተቃውሞ እንደተነሳና ዛሬም ድረስ አገሪቱ በተቃውሞ ስጋት ውስጥ መሆኗ አይዘነጋም። እሳቸው እንዳሉት ሁሉም የሚደረገው ያለው ኢኮኖሚውን ለማሻሻል ታስቦ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዶክ የሱዳን የፀጥታ አግባብ ለመበላሸቱ በዋናነት በአብዮቱ አካላት መካከል ያለው መበታተን፣ በዚሁም ሳቢያ ለውጡን የማይደግፉ ( የገፋቸው) ጠላቶች አጋጣሚውን የመጠቀም እድል ማግኘታቸውን ገልጸዋል። አጋጣሚውን እንደተጠቀሙበት የገለጹት የቀድሞው አገዛዝ አካላት ነው።

ሱዳን ተደጋጋሚ ግጭት፣ ድርቅና የምግብ እጥረት የሚከሰትባት አገር መሆኗ ይታወቃል። አሁን እንኳን በቅርቡ በዳርፉር በየቀኑ ሰዎች የሚረግፉባት አገር ናት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግልጽ የተናገሩት ጉዳይ የኢትዮጵያን ለውጥ አላፈናፍን ብሎ ይዞት ከነበረው ሴራ ጋር ተያያዥ እንደሆነ ምክንያታቸው ያሳያል። በኢትዮጵያ ለውጡ የገፋቸውና ራሳቸውን ከልወጡ ባቡር ያራገፉ እንዲሁም ለአንድና ሁለት ወንጀለኛ ሲሉ ህዝብ ዋጋ ያስከፈሉ መኖራቸው ስም እየተጠቀሰ ሲነገር ነበር።

Exit mobile version