ETHIO12.COM

በትግራይ ከተረጂውች ጉሮሮ ሰርቀው ከ4 ሺህ ኩንታል በላይ ስንዴ ሲዘርፉ የነበሩ ተያዙ

በትግራይ ለተፈናቀሉ ወገኖች በእርዳታ የቀረበ 4ሺህ 400 ኩንታል ስንዴ አየር በአየር ለመሸጥ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር የማነ ገሰሰው ለኢዜአ እንደገለፁት ለተፋናቃዮች የመጣ የእርዳታ እህል ሰሞኑን አየር በአየር ለመሽጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ስምንት ሰዎች ተይዘዋል። ግለሰቦቹን ለህግ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በተጠርጣሪ ግለሰቦቹ እጅ የነበረ የእርዳታ ስንዴን ለተፈናቃይ ወገኖች እንዲከፋፈል መደረጉን አመልክተዋል።

“ለተፈናቃይ ወገኖች የቀረበ  የእርዳታ  ስንዴ ዘርፎ ለግል ጥቅም ለማወዋል መሞከር  አፀያፊ ነው” ያሉት ሀላፊው፤  በእርዳታ የሚቀርብ እህል በአግባቡ ለተፈናቀሉ እንዲደርስ ሁሉም በንቃት ሊከታተል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ኢዜአይህንን ቢልም ከተረጂዎች ጉሮሮ ዘረፋ አካሂደው አየር በአየር ለመበልጸግ ሲነቀሳቀሱ የተያዙትን፣ ቀደም ብለውም በቁጥጥር ስራ የገቡትን የሚያወግዝ አካል አልተሰማም። በትግራይ ከርዳታ ስራ ጋር በተያያዘ ከ95 በመቶ በላይ ተቀጥረው የሚሰሩት የትግራይ ተወላጆች መሆናቸው ይታወሳል።

Exit mobile version