Site icon ETHIO12.COM

ፌስቡክ በኢትዮጵያ የሐሰት መረጃ የሚያሰራጩ ማህበራዊ ገጾችን ዘጋ

ፌስቡክ በኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ ከመጀመሩ በፊት የሀሰት መረጃ የሚያሰራጩ በርካታ ማህበራዊ ገጾችን መዝጋቱን ገልጿል፡፡

ድርጅቱ እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ አጠቃላይ አገራዊ ምርጫ ከመጀመሩ በፊት ስለ ምርጫ ዜና እና ፖለቲካ የሚለጥፉ የሐሰት ገጾችን እና ቡድኖችን ዘርዟል፡፡

በዚህም ሌሎችን ስለዓላማቸውና ማንነታቸው በማሳሳት ላይ የነበሩ 65 የፌስቡክ ገጾችን፣ 27 ቡድኖችን እና 32 የኢንስታግራም አካውንቶችን ማውረዱን ገልጿል፡፡

የፌስቡክ የደህንነት ፖሊሲ ሃላፊ ናትናኤል ግላይሸር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት “መጪውን አገራዊ ምርጫ እና በኢትዮጵያ እየታየ ያለውን ጫና ተከትሎ ቡድኖቻችን ምርመራውን ለማጠናቀቅ እና ይህን እንቅስቃሴ ለማርገብ በተቻለ ፍጥነት እየተንቀሳቀሱ ነው” ብለዋል፡፡

ፌስቡክ አሜሪካን ጨምሮ በሌሎች ሀገሮች በሚካሄዱ ምርጫዎች ወቅት የሐሰተኛ አካውንቶችን ለመዋጋት በቂ ዝግጅት ባለማድረጉ ወቀሳ እንደደረሰበት አስታውሶ፤ አሁን ማህበራዊ ገጾች ስለ ምርጫው የተሳሳተ መረጃን እና የጥላቻ ንግግሮችን የሚዋጋባቸውን መንገዶች ጨምሮ ለኢትዮጵያ ምርጫ ለመዘጋጀት እየወሰዳቸው ያሉ በርካታ እርምጃዎችን ዘርዝሯል፡፡

ድርጅቱ የሐሰት አካውንቶች በዋናነት ጠቅላይ ሚኒስትሩን፣ ገዥው ፓርቲን እንዲሁም ሌሎች ፓርቲዎችን መሰረት ያደረገ የጥላቻ ንግግርችን ያካተተ እንደሆነም ጠቁሟል፡፡

ፌስቡክ የሐሰት አካውንቶችን ከኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ፍላጎት እንዳለውም ተናግሯል፡፡

በዓለም ላይ በግምት 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን መለያዎች አንድ ወይም ከዚያ በላይ የፌስቡክ ገጾችን የሚከተሉ፣ 766 ሺህ የሚጠጉ መለያዎች ደግሞ አንድ ወይም ከዚያ በላይ ቡድኖችን የተቀላቀሉ እንዲሁም 1ሺህ 700 የሚጠጉ ሰዎች አንድ ወይም ከዚያ በላይ የኢንስታግራም መለያዎችን የሚከተሉ መሆናቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ENA

Exit mobile version